>

ዶ/ር አብይ አሕመድ የኢትዬጵያ አንድነትን ያስቀጥሉ ይሆን???  (በታምሩ ገዳ - ህብር ራዲዬ)

ዶ/ር አብይ አሕመድ የኢትዬጵያ አንድነትን ያስቀጥሉ ይሆን???
 ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዬ
 
በኢትዬጵያ ውስጥ ባለፉት አንድ አመት ከስድስት ወራት ጀምሮ  የታዩት እና እይታዩ የሚገኙት የፖለቲካዊ፣ኢኮነሚያዊ እና ማህበራዊ ክንውኖች    እውንታዊ  ወይም አሉታዊ  ለውጦች ከአትዬጵያኖች አልፎ የባእዳኖችን ትኩረቶች ፣አግራሞት  እና ስጋቶችን ጭምር መሳባቸው  አልቀረም።
በለንደን/እንግሊዝ ውስጥ በእየ ሶስት ወራት ለንባብ የሚበቃው    ኒው አፍሪካ (አዲሲቷ አፍሪካ) የተሰኘው መጽሔትም በሳምንቱ ማብቂያ ባወጣው(የ ወረሐ ነሐሴ እና መስከረም) እትሙ የፊት ገጹ ላይ “ጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ  ኢትዬጵያን/ኢትዬጵያኖችን በአንድነት እንዲቀጥሉ ያደርጉ ዘንድ ይቻላቸዋል?” ሲል እንባቢዎቹን ጠይቋል።
 በለፈው አንድ አመት ውስጥ  የፖለቲካ ምህዳር በከፊልም ቢሆን እየተፍታታ እንደነበር ያወሳው   የመጽሔቱ መግቢያ ጽሁፍ  ባለፈው ሰኔ ወር በባሕር ዳር እና በአ/አ ከተሞች ውስጥ የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት  በተመሳሳይ ሰአታት የተገደሉበት  አጋጣሚ  በርካታ ታዛቢዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ ክስተት  ብሎታል።
በኢትዬጵያ ውስጥ የሚታየው ተቃርኖዎች እና አመጻዎች መንሴአቸው ምንድን ነው?፣ በአለም በጎሳ ላይ በተመሰረተ የፌደራላዊ መንግስት  የምትመራ ብቸኛ አገር በሆነችው ኢትዬጵያ ውስጥ  በ ጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ አስተዳደር ተጀመሯል የተባለው ለውጥ ምናልባት ፈጥኖ  ይሆን ወይ ?ሲል የጠየቀው  የመጽሔቱ የትንታኔ  መንደርደሪያ ከዚህ እና ከተዛማጅ ጉዳዬች  አኳያ  የጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ  አስተዳደር ኢትዬጵዬጵያን እና ሕዝቦቿን በአንድነት ጥላ ስር የማቆየት ክህለሎቱ እና  ብቃቱ ይኖረው ይሆን?ሲል  ነጻ የሀሳብ ውይይት መድረኩን ለሁሉም ወገኖች ከፍቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ የእርሶስ አመለካከትን  እንዴት ይገልጹታል?።  እንደምናያቸው  ፣እንደምናነባቸው እና እንደምንሰማቸው  የኢትዬጵያ አንድነትን በዘላቂነት  ለማስቀጠል ምን ቢደረግ  ይበጃል  ይላሉ?። ከስሜታዊነት የጸዳ ትችት ሆነ አስተያየት በማወቅም ይሁን ባለማውቅ ያንቀላፋውን  ይቀሰቅሳል፣ እገርን ከጥፋት ፣ህዝብንም ከጭንቀት ያድናል።
Filed in: Amharic