>

"ጡረተኛ ፖለቲከኞችና የሜንጫ አብዮተኞች!!!" ( አለባቸው ደሳለኝ አበሻ)

“ጡረተኛ ፖለቲከኞችና የሜንጫ አብዮተኞች!!!” 
 አለባቸው ደሳለኝ አበሻ 
በአንድ ወቅት ህንድን በቅኝ ገዢነት ያስተዳድሩ የነበሩት እንግሊዞች ህንድ ውስጥ ልጆቻቸው ኮብራ በተሰኘው እባብ እየተነደፉ በመቸገራቸው የኮብራውን ቁጥር ለመቆጣጠር ህንዳውያንን ሰብስበው ኮብራ እየገደሉ ሲያመጡ ባመጡት ኮብራ ልክ ገንዘብ መክፈል ጀመሩ:: ኮብራው ቁጥሩ ሲቀንስ ገንዘብም አብሮ ቀነሰ: : ኮብራ እባብ በመግደል የእንግሊዝ ፓውንድ የጣማቸው  ህዳውያን ሌላ አዲስ ብልሐት ማፈላለግ ጀመሩ ::  ህንዳውያኑ ኮብራን እባብን ማርባት ጀመሩ:: የኮብራውም ቁጥር እጅጉን በብዙ ሽህ  ጨመረ:: ይህ ያልተገመተ መዘዝ እራሳቸውን ህንዶችን እየነደፈ ፈጃቸው ::
ዛሬ በኛም ሐገር ”  በትውልዱ ላይ ክፉ የዘረኛ ፕሮፓጋንዳ የሚረጩ  የሜንጫ አብዮተኛ አክቲቪስቶች ከትግራይ ወያኔ ጡረተኛ ፓለቲከኞች ጋር በመመሳጠር የህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል  የግል ኑሯቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ  የዘረኝነት መርዛቸው እንደ ኮብራው እባብ  ያረባሉ: :
እነዚህ. ጡረተኛ ፓለቲከኞችና የሜንጫ አብዮተኞች በጥቅም ያያዛቸው ምክኒያት ምንድ ነው ብለን ስንጠይቅ ? ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ከሰፈነ ሁሉም በፈፀሙት ወንጀል በህግ ተጠያቂዎች ናቸው ::ስለዚህ ምርጫቸው ሐገሪቱን በክልል ማተራመስና ታዋቂ ፖለቲከኞችን. መግደል  የሐይማኖት ተቋሟችን ማውደም ለውጡን በተቻለ መጠን መቀልበስ ወይንም ባለበት እንዲፀና ለማድረግ ዘረኛ የሜንጫ አብዮተኛ ኮብራዎችን ማራባት  የትግራይ ጡረተኛ ወያኔ ፖለቲከኞች አዲሱ ስልት ነው : :
 የሚያናፍሱት  ፕሮፖጋንዳቸው  ሁሉ በጥናትና በዕምነት ላይ ያልተመረኮዘ፣ ፕሪንሲፕልና ፍልስፍና የጎደለው፣ ሳይንሰ-አልባ የሆነ፣ ብሄራዊ ጥቅምንና አንድነትን ከማስቀደም ይልቅ ዘረኝነትን ያስቀደመ፣ በጋራ ዓላማ ላይና ሁሉንም ሊያሰባስብ በሚችል አመለካከት ላይ ያልተገነባ፣ አገርን ከሀፍረት ለማውጣት የግዴታ ሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ግንባታ የለለው  የትግላችን መመሪያ ነው የሚሉት ከአንድነት ይልቅ መበታተንና የሚመርጥ  ሐገርን እንደ ሐገር እንዳይቀጥል ዓላማ ያደረገ፣ ለውጡን ለመቀልበስ  ሲባል ብቻ. እንደ አስፈላጊነቱ ከውጭ ኃይልም ጋር ቢሆን  በመተባበር አገርን የማተረመስ ቅስቀሳ በማድረግ ህብረተሰቡን ጤና መንሳት በመሆኑ እነዚህ ጡረተኛ ፓለቲከኞችና የሜንጫ አብዮተኞች ከህንዶቹ ኮብራ እባብ አርቢዎች ጋር ይመሳሰሉብኛል ::
ውድ  ወዳጆቼ ::
ቅጥረኛ የሜንጫ አብዮተኞች ቢሆኑም በኦሮሞ ስም ከመነገድ ባለፈ እንታገልበታለን  የሚሉት  ጽንሰ-ሃሳብ በጎሳ ዘረኝነት  ክልል ውስጥ የሚሽከረከር ሲሆን፣ የመንፈስን የበላይነት ያላስቀደመና፣ በጽሞናና በውይይት ወይም ደግሞ በሳይንሳዊ ክርክር  ለማሳማን. የሚጥር ሳይሆን ጎልበትን ወይም አመጽን ያስቀደመ በሬ ወለደ  ፕሮፖጋንዳ ነው። ሊዋጥላቸው  ያልቻለው እውነት ግን የጎሣ ፓለቲካና “የጎሣ ፌደራሊዝም” በማራመድ የሕግ የበላይነት የሠፈነበትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማስፈን አይቻልም:: “የጎሣ ፌደራሊዝም” የዴሞክራሲ ፀር ነው:: የጎሣ ፓለቲካ ያልተገመቱና ያልታሰቡ መዘዞችን (unintended consequences) ይጋብዛል:: “የጎሣ ፌደራሊዝም” መፍትሄ ሳይሆን በራሱ ችግር ነው:: ማንኛውም የሰው ልጅ ኑሮ ሁሉ ከትግል ጋር የተያያዘ ቢሆንም፣ ትግል የሚባለው የኑሮ ፍልስፍና ከሽወዳ፣ ከማጭበርብር፣ ከአመጽ፣  ድርጊት ጋር የሚያያዝ ከሆነ  አንድ ቀን ጡረተኛ ፓለቲከኛችንና የሜንጫ አብዮተኞችን እንደ ኮብራ እባብ አርቢዎቹ እራሳቸውንም  እንደሚያጠፋቸው ገና እስካሁን  አልተገለጠላቸውም ::
ስለዚህ ከዚህ ዐይነቱ አጉል ዘመቻና ተስፋ ከሚያስቆርጥ አስተሳሰብ ከሚራምዱ ዘረኛ የሜንጫ ኮብራዎች  መላቀቅ ያስፈልጋል። ማንኛውም ግለሰብም ሆነ መላው ኢትዮጵያዊ ለውጡን በግማሽ ልብ ሳይሆን በሙሉ ልቡ መደገፍና በለውጡ ላይ ዕምነት እንዲኖረው ማምንና መቀበል አለበት። ሌላው አለም  የሰራውን እኛም  መስራት እችላለን ብለን  መነሳት ይኖርብናል: :  በተለይ ኢትዮጵያዊ ወጣት በቁርጠኝነት  መነሳት  አለበት።
አጉል ትልቅ ሰው እየመሰሉ. ዶክተር ፕሮፌሰር በመባባል በተለያዩ ሚዲያ የሚቀርብትን የዩቲዩብ ጡረተኛችንና  የሜንጫ  ፖለቲካ አክቲቪስት ኮብራዎችን ወጣቱ አንቅሮ ሊተፋቸው ይገባል :: የፖለቲካ ትግል ምሁራዊነት ብቻ ሳይሆን ግልጽነት የተሞላበት ብሔራዊ ስሜት  ያስፈልገዋል። ኢትዮጵያዊነት ድፈረትን ይጠይቃል።  የኢትዮጵያን  መጭ የለውጥ  እድል በትግራይ ጡረተኛ ፖለቲከኞችና በሜንጫ ኮብራዎች እንዳይቀለበስ  እንቢ ባይነትን ይጠይቃል . ::
ለዛሬው እኔም በዚሁ አበቃሁ: :
በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን 
Filed in: Amharic