>
5:13 pm - Saturday April 19, 5180

በአማራ ስም ወንጀል ሲሰራ ዝም ብለን አናይም!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የተወጋበትን ጩቤ ልሶ ስሞ አደሩ አማራ!!!
አቻምየለህ ታምሩ
በአማራ ስም ወንጀል ሲሰራ ዝም ብለን አናይም! 
«የአማራ ባንክ» የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን ለማብሰር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ከተጋበዙት «የአማራ የክብር እንግዶች» መካከል ታምራት ላይኔ  ቀዳሚው ነበር አሉ። ታምራት ላይኔን የአማራ ባንክ ምስረታ ላይ በክብር እንግድነት መጋበዝ አዶልፍ ሒትለርን በአይሁድ ባንክ ምስረታ ላይ በክብር እንግድነት እንደመጋበዝ ነው። ታምራት ላይኔን በአማራ ባንክ ምስረታ ላይ በክብር እንግድነት የጋበዙት ሰዎች መለስ ዜናዊም  ቢኖር ኖሮ ቁጥር አንድ የክብር እንግዳ አድርገው ይጋብዙት ነበር።
ማንም ግለሰብም ይሁን ለንግድ የተቋቋመ  ቡድን የአማራ ስም ተጥቅሞ  ወንጀል እንዲሰራ ሊፈቀድለት አይገባም። አዶልፍ ሒትለርን በአይሁድ ባንክ ምስረታ ላይ መጋበዝ ወንጀል እንደሆነው ሁሉ ታምራት ላይኔንም በአማራ ባንክ ምስረታ ላይ መጋበዝ የወንጀል ወንጀል ነው። በታምራት ላይኔ መሪነት በአማራ ላይ ስለተፈጸመው ግፍና መከራ፤ የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳትና የጦር ወንጀሎች ባዕድ የሆኑ ሰዎች በምን ምክንያት ስለተጎዳው አማራ ድጋፍ ሊያደርጉ ነው በአማራ ስም ባንክ የሚያቋቁሙት? በአማራ ስም ባቋቋሙት የባንክ ምስረታ ላይ ታምራት ላይኔን በክብር እንግድነት የጋበዙ ደንታ ቢሶችን   በአማራ ስም ወንጀል ሲሰሩ ዝም ብለን ልናያቸው እንደማንችል ልንነግራቸው  ይገባል።
የአማራው ባለደም ታምራ ላይኔ  ወንጀለኛነት  የሚጀምረው የፋሽስት ወያኔ ሎሌ ሆኖ አዲስ አበባ እንደገባ ወደ ሐረር በማቅናት «ሽርጥ ለባሽ ይሏችሁኋል…በሏቸው» በማለት አማራን ሲያስፈጅ አይደለም።  ፋሽስት ወያኔን ተከትሎ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት የፋሽስት ወያኔ አማርኛ አስተርጓሚ ሆኖ በተለይም በወሎ ይንቀሳቀስ በነበረበት ወቅት በንጹሐን አማሮች  ላይ  እየፈረደ ሲያስረሽን የነበረው ታምራት ላይኔ ራሱ እንደነበር  ከታምራት ላይኔ የግድ ግድያ በተአምር የተረፉት በደርግ ዘመን የመጨረሻው  የደቡብ ወሎ የአስተዳደር አካባቢ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ተክለ ማርያም መንግሥቱ «አንድ ለመንገድ» በሚል በጻፉት መጽሐፋቸው የአይን እማኝነታቸው ሰጥተዋል። በንጹሐን ሕይወት ላይ እየፈረደ ሲያስረሽንና አማሮች በያሉበት እንዲጨፈጨፉ ሲያደርግ የነበረው ታምራት ልይኔ ጭንብል ቀይኖር ዛሬ ፓስተር ቢሆን ወንጀለኛነቱን ሊለውጠው አይችልም።
ታምራት ላይኔ አገርና መንግሥት ሲኖረን በግፍ ላስጨፈጨፋቸው አማሮች፣ በአገራቸው ውስጥ ስደተኛ እንዲሆኑ ላደረጋቸው ሚሊዮን የአማራ ተወላጆችና በአማራነታቸው ብቻ ተወንጅለው እስካሁን ድረስ መድረሻቸው ሳይታወቅ ጠፍተው ለቀሩት  የአማራ ምሁራንና አባቶቻችን ሕይወት ተጠያቂ እንዲሆን እጁ የኋሊት በመጫኛ ታስሮ እውነተኛ ችሎት ፊት ቀርቦ በአማራ ላይ ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ ከምናደርጋቸው ጸረ አማራዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።
በአማራ  ስም በተቋቋመ ባንክ ምስረታ ላይ ግንባር ቀደም የአማራ የክብር እንግዳ ሆኖ የተጋበዘው  ይህ  በአማራ ላይ ለተፈጸመ ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሚደረጉት ቀንደኛ ጸረ አማራዎች መካከል ግንባር ቀደም የሆነው ታምራት ላይኔ ነው።
ታላቁ አሊ ሑሴን ታምራት ላይኔ የክብር እንግዳ ሆኖ የተጋበዘበትን የአማራ ባንክ ምስረታ አይነት ትራጄዲን  በደልና ግፍ የሕይወቱ ገጽታ የሆነው አማራ በደሉን እየረሳ ሁሌ ጊዜ ከእንደ ታምራት ላይኔ አይነት አራጆቹ  ኋላ ሲከተል መኖሩን እንዲህ ሲሉ ገልጸውት ነበር፤
የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ ነበረ ተረቱ፣
ምነዋ ዘንድሮ ተወጊው ሲረሳ ወጊ አለመርሳቱ፤ 
ከዚያም አልፎ ተርፎ የተወጊው ጉዳይ የከበደው ነገር፣
በደሉን ረስቶ የወጋውን ጩቤ ልሶ ስሞ ማደር!
ታምራት ላይኔ በክብር እንግድነት የተጋበዘበት የአማራ ባንክ ምስረታም   በደልን ረስቶ የተወጉበትን ጩቤ ልሶ ስሞ እንደ ማደር አይነት ወንጀል ነው።
Filed in: Amharic