>

“ተከበሃል!!!” አለ አሳምነው ጽጌ! (ዘመድኩን በቀለ) 

“ተከበሃል!!!” አለ አሳምነው ጽጌ!
ዘመድኩን በቀለ 
* የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድና የመከላከያ ሚንስትሩ የለማ መገርሳ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተጨማሪ 32ሺህ ልዩ ኃይልና 19 ሺህ የፖሊስ ኃይል አስመርቋል
• “ ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም።
• ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፤ በኃይሉም ብዛት አያመልጥም።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በምሕረቱም ወደሚታመኑ፥ መዝ 33፣ 16-18
 ~ አልሸባብም በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ እጀምራለሁ ብሏል አሉ።   ቪኦኤ ነው የዘገበው።
•••
አንዱ እኮ ነው ዘመዴ አለኝ። ዘመዴ “በእንብርክክህ ዳዴ ብለህ በጉልበትህም ድኸህ፤ ድንጋይ ተሸክመህ የአሳምነው ፅጌ መቃብር ላይ ተደፍተህ ይቅር በለኝ የምትልበት ዘመን ይመጣል” አላለኝም።
★ ይኸው ወፈፌ ጎዶኛዬ አከል አድርጎም “ የሀገሪቱ ጦር ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንም” ለምን እንደተገደለ ውሎ ሲያድር ይገባሃልም ብሎኛል ይኸው ጓደኛዬ።
★ ኢትዮጵያ አለባት የተባለውን 1.5 ትሪሊዮን ብር እዳስ ማነው የሚከፍለው? ብሎ ጠይቆ ሲያበቃ ቀጥሎም “በኢትዮጵያ ስም እየተበደርክ ሠራዊትህንና ራስህን ትገነባለህ” አይለኝ መሰላችሁ። ምን ማለቱ እንደሆነ እስከአሁን አልገባህ እንዳለኝ አለሁ።
•••
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድና የኢትዮጵያው መከላከያ ሚንስትር የለማ መገርሳዋ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልልዋዊ መንግሥት ተጨማሪ 32ሺህ ልዩ ኃይል፣ 19 ሺህ የፖሊስ ኃይል አስመርቋል የሚል ዜና ታይቷል። በአጠቃላይ 51 ሺ የኦሮሞ ሠራዊት በኢትዮጵያ በጀት ሰልጥኗል። ማንን ለመውጋት እንደሚሰለጥን መድኃኔዓለም ይወቅ።
•••
ባለፈው ጊዜ ዐቢይ አህመድ ደሴ ይሄድና ወለዬዎቹ በአካባቢያቸው ምንም ዓይነት ልማት አለመልማቱን እና መንግሥታቸው በምህረት ዐይኑ እንዲመለከታቸው ይጠይቁታል። አቢቹም አለ። በየት በኩል ትለማላችሁ? እኛ የምንሰጣችሁን በጀት ሚኒሻ ነው የሚሰለጥንበት። ይሄ እስካልቆመ ድረስ በየት በኩል ሆስፒታል፣ ፋብሪካ፣ ትምህርት ቤት ይሠራላችኋል በማለት መለሰ። በሳምንቱም የክልሉ ባለሥልጣናት ተረሸኑ። ሲገደሉ የሚኒሻ አሰልጣኞችም አልቀሩ። ነፍስ ይማር።
•••
ታዲያ በዚያ ሰሞን የኦሮሞ አክቲቪስቶች በሙሉ፣ የገሌ ፓርቲ ወዶ ገቦቹ ኢዜማዎችም ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል በአሳምነው ጽጌ ላይ እርምጃ ካልተወሰደ ብለው ወተወቱ። የዐማራ ልዩ ኃይልም ይፍረስ ብለው እሪሪሪ አሉ። በቃላቸውም መሠረት ተደረገላቸው። መሪዎቹ ተገደሉ። ልዩ ኃይሉም ተበተነ። የቀረውም ተረሸነ፣ ታሰረ። ለፖሊስ ኃይሉም የአምቦው ልጅ የግንቦት 7ቱ አበረ አዳሙ የበላይ ተደርጎ ለዐማራ ተሾመ።
•••
ዛሬ ደግሞ ይህን የኦሮሞ ሠራዊት ስልጠናና ምረቃ አይቼ የኦሮሞዎቹ አክቲቪስቶች እንኳ እሺ ይቅር እንዲያው ኢዜማዎች ምን ይሉ ይሆን ብዬ ብጠብቅ፣ ብጠብቅ፣ በፌስ ቡክ መንደር ብዞር ብንከራተት ወፍ የለም። ወፍ የለም አልኩህ። የሆነማ የሚወረር፣ የሚመሰረት ሀገርማ አለ። አባቴ ይሙት የሆነ ነገርማ አለ።
•••
ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ በአሁኑ ጊዜ የየክልሎቹ ልዩ ኃይል በንፅፅር ምን እንደሚመስል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሕብረት በፌስቡክ ገፁ ያሰፈረውን እንመልከት።
• ትግራይ 240 ሺህ ልዩ ኃይል በመደበኛ ሠራዊት ቁመና ከነ ሙሉ ትጥቁ አዘጋጅታ በተጠንቀቅ አለች።
• ኦሮምያ 160 ሺህ ልዩ ኃይል የቡድን መሳሪያ ጨምሮ ከባድ መሳሪያ በሚገባ የታጠቀ ሠራዊት አዘጋጅታ በተጠንቀቅ አለች።
• ዐማራ 8 ሺህ ልዩ ኃይል ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላዩ ምንም ትጥቅ ያልተሰጠው፣ ከዚያም ብሶ በሚደርስበት ወከባ እየተማረረ ያለና በብዛት መልቀቂያ አስገብቶ እየተበተነ ያለ የፈረሰ ልዩ ኃይል አለው ይላል ጦማሪው። [ ለዐማራ ከእግዚአብሔር ሠራዊት በቀር የሚረዳው ምድራዊ ኃይል የለም ] ።
•••
ስለ ደቡብ፣ ስለ ሱማሌ፣ ስለ ቤኒሻንጉል የተባለ አንዳችም ነገር የለም። ለማንኛውም መልካም ስልጠና፣ መልካም ምረቃ። ወረራና ግድያው ውጊያውም በየት በኩል እንደሚጀመር ቀደም ብሎ ቢታወቅ መልካም ነበር። ወሎን ኬኛ በላይ ዘለቀ [ ቂልጡ ] ኦሮሞ ነው። ጎንደርን ኦሮሞ ነው የገነባው፣ አክሱም አከሱማ የሚለው ፅንፈኛ ከሆነ ግን እየሰለጠነ አያሰለጠነም ያለው ጉድ መፍላቱ ነው።
•••
ሻሎም !  ሰላም !  
ነሐሴ 14/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic