>
9:41 am - Saturday November 26, 2022

ጃዋር መሀመድ እና  አዶልፍ ሂትለር አንድ ናቸው!!! (ስዩም ተሾመ)

ጃዋር መሀመድ እና  አዶልፍ ሂትለር አንድ ናቸው!!!
ስዩም ተሾመ
ጃዋር መሀመድ የማንነት ቀውስ ውስጥ ያለ ሰው ነው። ከመንዜ አማራ እናቱ እና ከኦሮሞ አባቱ አንዱን በመምረጥ በዚያ ላይ የተመሠረተ ማንነት ለመገንባት የወሰነ ሰው ነው። በመሆኑም ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ መሆን ይቃጣዋል።
ጥቅምና ጉዳት በብሔር በሚለካበት፣ የብሔርተኝነት አመለካከት በጦዘበት ማህብረሰብ ዘንድ ከሁለት የተለያዩ ብሔሮች የተወለዱ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ጭራሽ ስለ ብሔር ማሰብና መናገር በማቆም ከራሳቸው ጋር ለመታረቅ ይሞክራሉ።
ጥቂቶች ይህን የማንነት ቀውስ በምክንያታዊነት እና ዕውቀት በመሞገትና በጥልቀት በማሰብ ከብሔርተኝነት ብቻ ሳይሆን ከዜግነት ከፍ ብለው በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረተ አመለካከት ያዳብራሉ።
የሰብዓዊነት እሳቤ ያለው “ሁሉም ሰው በሰብዓዊነቱ እኩል መብትና ነፃነት ይገባዋል” በሚል መርህ ይመራል። በዜግነት መርህ የሚመሩት ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ዜጎች በላይ ለሀገራቸው ዜጋ ያደላሉ። በአንፃሩ ብሔርተኞች ለአንድ ብሔር ተወላጆች አድሏዊና ወገንተኛ ይሆናሉ። ከሁለት የተለያዩ ብሔሮች የተወለዱ ሰዎች ከሰብዓዊነትና ዜግነት ወርደው ብሔርተኛ ከሆኑ በምድር ላይ በጣም አደገኛ ሰዎች ይሆናሉ። ከሁለቱ ብሔሮች መካከል የማንነታቸው መገለጫ አድርገው ለመረጡት ብሔር ከማንም በላይ አሳቢና ተቆርቋሪ ሆነው ለመቅረብ ይሞክራሉ።
በአንፃሩ የማንነታቸው መገለጫ መሆኑን እንዳይታወቅባቸው በሚፈልጉት ብሔር ላይ ከማንም በላይ ጥላቻና ንቀት ያድርባቸዋል። Jawar Mohammed በዚህ ምክንያት የማንነት ቀውስ ውስጥ ያለ ሰው ነው። ሁሉም ነገር በብሔር እና ብሔርተኝነት በሚቃኝበት ስርዓት ውስጥ ከመንዜ አማራ እናቱ እና ከኦሮሞ አባቱ አንዱን በመምረጥ በዚያ ላይ የተመሠረተ ማንነት ለመገንባት የወሰነ ሰው ነው። በመሆኑም ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ መሆን ይቃጣዋል። በዚያው ልክ ከማንም በላይ አማራን ይጠላል። ነገር ግን ጃዋር ኦሮሞን ከማንም አብልጦ የሚወደው ሆነ አማራን የሚጠላው ከገባበት የማንነት ቀውስ መውጣት ስለተሳነው፤ ወደ
ሰብዓዊነት ሆነ ዜግነት ከፍ ማለት ስላቃተው ነው። የጀዋርን ክፋት እና ጥላቻ መለካት ለሚሻ የናዚው አዶልፍ ሂትለርን ማየት ብቻ በቂ ነው።
 አዶልፍ ሂትለር 25% አይሁድ እንደሆነ በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት ጠቁሟል። ሂትለር ከጀርመኖች በላይ ጀርመናዊ ለመሆን ያደረገው ጥረት አይሁዶችን ከማንም በላይ ከመጥላት አልፎ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሙከራ አድርጓል።
በተመሳሳይ ጃዋር ከኦሮሞ በላቀ ኦሮሞ መሆኑን ለማስመስከር በሚያደርገው ጥረት ሂትለር በአይሁዳውያን ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋና ዘር ማጥፋት በአማራ ላይ ከመድገም ወደኋላ አይልም። ብዙዎች ጃዋር መሀመድ በእናቱ አማራ እንደሆነ ሲነገር ውሸት እንደሆነ ያስባሉ።
 ነገር ግን በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ OMN በሂልተን ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ጃዋር ራሱ “እኔ በእናቴ አማራ በአባቴ ደግሞ ኦሮሞ ነኝ!” ማለቱ ውሸት ከሆነ በቀሪ ህይወቴ እውነት መናገር አልሻም። በዚህ ጉዳይ ከዋሸሁ በቀሪ እድሜዬ ማንም ሰው የምናገረውን ሆነ የምፅፈውን አምኖ መቀበል እንደሌለበት እማፀነዋለሁ። በአጠቃላይ ጃዋርን ከሂትለር የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም ብሔርተኛ ለመሆን በሚያደርጉት ጥረት የማንነታቸው አካል የሆነውን ወገን ከምድረ ገፅ ከማጥፋት የማይመለሱ መሆናቸው ነው። ስለዚህ ሂትለር በአይሁዳውያን ላይ ያደረገውን ጃዋር በአማራ ሊደግመው ይቻላል ብሎ ማሰብ ስህተት የመሆን እድሉ ከአስር እጅ አንድ ነው።
ነገሩን እጅግ አደገኛ የሚያደርገው ደግሞ በፌደራል ሆነ በክልል ደረጃ የሚገኙ የመንግሥት ሃላፊዎች እና የፖለቲካ ልሂቃን የጀዋርን እብደት ትክክል ብለው መቀበላቸው ነው። ጀዋር መሃመድ ኦሮሞ ነው፣ ኢትዮጵያዊ ወይም ሰው ነው ከማለት ይልቅ እንደ አዶልፍ ሂትለር እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው እብድ
ነው ብሎ ማሰብ የተሻለ ይመስለኛል። የእሱን እብደት አውቆ መጠንቀቅ ሊደርስ የሚችለውን እልቂት ማስቀረት እንኳን ባይቻል ጉዳቱን መቀነስ የሚቻል ይመስለኛል።
የጥበት መጨረሻው ከራሱ ጋር ብቻ ማውራት ነው! 
“በኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አማርኛ ሊማሩ ነው” መባሉ አያቶላህ Jawar Mohammedን ክፉኛ አስቆጥቷል። ነገር ግን አማርኛን አቀላጥፎ መናገር ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ለማወቅ ራሱ ጀዋርን ማየት ብቻ በቂ ነው። ጃዋር መሀመድ ከኦሮሚያ አልፎ በመላ ሀገሪቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለው ከኦሮምኛ በተጨማሪ #አማርኛን አቀላጥፎ መናገር በመቻሉ ነው። በእርግጥ ጃዋር እንግሊዘኛ መናገር የሚችል ቢሆንም ቋንቋው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ፋይዳ ቢስ ነው ማለት ይቻላል። በእርግጥ ኦሮምኛ ብቻ ተናጋሪ መሆን በራሱ ችግር የለውም። ነገር ግን ኦሮምኛ ብቻ ተናጋሪ መሆን ተፅዕኖ የመፍጠር አቅምን ኦሮሚያ ውስጥ ብቻ እንደ መገደብ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አማራ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች የመስራት እድልን ማጥበብ ነው። በሌሎች የሀገሪቱ አከባቢዎች በኦሮምኛ እግባባለሁ ብሎ ለማለት አሁን አማርኛን ማስተማር ከባድ የሆነውን ያህል ፈታኝ ነው። በመሠረቱ ኦሮምኛ የፌደራል ቋንቋ ይሁን ማለት መብት ነው። ሆኖም ግን “ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች አማርኛ መማር የለባቸውም” ማለት ጥበት ነው። ይህን የተናገረው ደግሞ ሌላ ሳይሆን አማርኛ አቀላጥፎ በመናገሩ ምክንያት ሀገር አቀፍ እውቅና እና ተደማጭነት ያተረፈው ጀዋር መሆኑ ሲታሰብ ነገሩ ከጥበትም አልፎ የመለስ ዜናዊ ዓይነት ክፋትና ምቀኝነት የተሞላ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በመጨረሻም ጃዋር “የኦሮሞ ልጆች አማርኛ መማር የለባቸውም” ለማለቱ ትክክለኛው የአፀፋ ምላሽ ራሱ በአማርኛ እንዳይናገር ማድረግ ነው።
 ስለዚህ ጃዋር በአማርኛ ሲናገር አለማዳመጥ፣ በአማርኛ ሲፅፍ አለማንበብ ወይም ምላሽ አለመስጠት ተገቢ ነው። በእርግጥ የኦሮሞ ልጆች እንዲናገሩት ሆነ እንዲያውቁት በማይፈልገው ቋንቋ ሲናገር ሆነ ሲፅፍ በሚጠላው ቋንቋ ለሚጠላው ወገን ያስተላለፈው መልዕክት እንደመሆኑ መጠን ፌስቡክ ላይ ከሆነ ለፌስቡክ፣ በዩቲዩብ ወይም ቲዊተር ላይ ከሆነ ደግሞ ለእነዚህ ማህበራዊ ሚዲያዎች የጃዋር ንግግር ወይም ፅሁፍን “የጥላቻ ንግግር” መሆኑን በመጥቀስ ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል። በእርግጥ የጥበት መጨረሻው ከራስ ጋር ብቻ ማውራት ነው። የጃዋርም መጨረሻ ይሄው ነው።
Filed in: Amharic