>

ወንዝ የማያሻግሩ ቋንቋዎች?!? •ሰኞ ያደነቅናችሁ - ማክሰኞ እየወረዳችሁ ተቸገርን!!! (መምህር ታዬ ቦጋለ አረጋ)

ወንዝ የማያሻግሩ ቋንቋዎች?!?

ሰኞ ያደነቅናችሁ – ማክሰኞ እየወረዳችሁ ተቸገርን!!!

መምህር ታዬ ቦጋለ አረጋ
ጥላቻ አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የገባ – አመክንዮ ሳይሆን ግልብነት – ስሌት ሳይሆን ስሜት – ጠልቆ ማሰብ ሳይሆን መሰለኝና ደሳለኝ ተፈናጥጦ የሚሰግርባቸው *ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያቀዱ ፀረ-ህዝብ ፅንፈኞች የለቀቁት የሰሞኑ አሳፋሪ “ነጠላ ዜማ” – አማርኛን ‘ወንዝ የማያሻግር ቋንቋ ነው’ የሚል –  የባዶ ወና ግልብ መደዳ እንቶፈንቶ አርቲቡርቲ እና መናኛነታቸው መገለጫ የሆነ – የዘቀጠ ስብእናቸው ማመላከቻ – ተራ ልፈፋ ነው።
*
አማርኛ –  ኢትዮጵያዊ  ወገኖችን ያለልዩነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በፌዴሬሺን ምክር ቤት፣ በደቡብ 56 ‘ብሔሮች’ ብሔረሰቦችንና ‘ህዝቦችን’፣ የጋምቤላን ክልል ህዝብ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝን ክልል ህዝብ፣ የድሬዳዋን ከተማ አስተዳደር ህዝብ፣ የአዲስአበባን ከተማ አስተዳደር ህዝብ፣ በተጨባጭ መሸፈን በማይቻል ደረጃ – ከሰማንያ በላይ የኢትዮጵያን ብሔረሰቦች (አንድ ኢትዮጵያዊ ህዝብ) ያግባባል።
*
በረታውያን የኢትዮጵያን ከሰማንያ በላይ ማህበረሰቦች ንቀው ‘ከወንዝ አሳንሰው’ በመመደብ = “ወንዝ የማያሻግር” ሲሉ – ከህዝብ ለህዝብ ትስስር ይልቅ ወንዝ ልቆባቸው -ሲውተፈተፉና ተጃምለው ሲግበሰበሱ – ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸውን የበዛ ንቀት እና እየሰረሰረ ሚገድላቸው “የሙት መንፈስ” ምን ያህል እንደተጣባቸው ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
*
ኦሮምኛ የተከበረ ቋንቋ ነው። ወንዝ ሳይሆን ዓለማቀፍ ድንበር ተሻግሮ ኬንያ ውስጥ ከሚገኘው ከ100ሺህ የማይበልጥ – ከቦሌ ክፍለከተማ ህዝብ አራት ጊዜ እጥፍ ከሚያንስ የቦረና ኦሮሞ ጋር ብቻ ያገናኛል። ከዚህ አንፃር?!
*
ኩናምኛ የተከበረ ቋንቋ ነው። ወንዝ ተሻግሮ ኤርትራ ውስጥ ከመቶሺህ ካነሰ ኩናማ ጋር ብቻ ያገናኛል።
*
ትግርኛ ወንዝ ተሻግሮ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያገናኛል። የሁለታችሁን ግንኙነት – በሚገባ እናውቃለን – እንተዋወቃለን። ‘ጅብ የሚያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ’ ሲል?! ለነገሩ የቀን ጅብ ፈጣጣ ነው።
*
አኙዋክኛ ኑዌር… የተከበሩ ቋንቋዎች ናቸው። በሱዳን እርስበርስ በመዋጋት እየተላለቁ ካሉ ተመሳሳይ ቋንቋ – ወረዳ ከሚያህሉ ወገኖቹ ጋር ያገናኛል።
*
ከአፋርና ሶማሊ የበቀሉ ትንታጎች – በኢትዮጵያዊነታቸው እንደማይደራደሩና በቋንቋ ላይ ያላቸውን አቋም አስነብበውናል። ወገን ሀገር ድንበር ተሻግሮ ካለው ጎረቤት እንደሚቀርብ ያውቃሉ። በዚያ በኩል የሌላ ሀገር ጠብመንጃ ይዞ ሚንጎራደድ የራሳቸውን ቋንቋ ተናጋሪ ያያሉ። (ኤርትራዊና ትግራያዊ እንደ አይነተኛ መገለጫ)
*
የሚያሳዝነው የሚያሳቅቀውና የሚያሸማቅቀው – በአንድነታችን ላይ ያላቸውን ጥላቻ የሚያቀረሹ ፌስቡካውያን ያለልዩነት – ትፋታቸውን የለገዱት በአማርኛ ቋንቋ ነው። አማርኛ ወንዝ የማያሻግር ከሆነ – ለምን ሀሳባችሁን የራሴ ባላችሁት ቋንቋ ብቻ አትፅፉም።
*
ጀግናውንና ክቡሩን የኢትዮጵያ ህዝብ መስተጋብር – ወንዝ ተሻግሮ ከአንድ መንደር ከማውራት ጋር ስታነፃፅሩ – ለትንሽነታችሁ፣ ለሚጢጢ ስብዕናችሁ፣ ለበታችነት ፍርሀታችሁ አዘንኩ። “የበታችነት ስሜት” ህመሙ እጅግ በጣም አዳጋች ነው።
*
እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛና ዐረብኛን የምንማረው ከዓለም ህዝብ ጋር ስለሚያሰናኙን እንጂ ወንዝ ተሻግረን ወዲያውኑ ከጎረቤት ተመሳሳይ ጋር ስለሚያገናኙን አይደለም።
ኢትዮጵያውያን ያለልዩነት የምንግባባበት ቋንቋ አማርኛ ነው።
በምክክር በውይይት በጥናት በአመክንዮ ላይ ተመስርተን ልጆቻችን የሀገር ውስጥ ወገኖቻቸውን ሌሎች ቋንቋዎችና የዓለምን ቋንቋዎች በመማር ባለብዙ ልሳን ቢሆኑ አብዝተው እንደሚያተርፉ እሙን ነው።
*
ስዊዘርላንድ ውስጥ ሁሉም ዜጋ አራት ቋንቋዎችን የሚማርበት ድንቅ ተሞክሮ አለ።
*ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል – አፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ይማራሉ።
*አምስተኛና ስድስተኛ ክፍል ላይ – እንደ አማርኛ በህገመንግስት የብዙኃን መግባቢያ የሆነውን ቋንቋ ይጀምሩና እስከ መጨረሻው ይዘልቃል።
 *ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ላይ – ሰፋ ያለ ተናጋሪ ያለውን ወይም የመረጡትን ቋንቋ ይማራሉ። Ztseat Saveadna Ananya ለትግራይ ክልል ግዕዝን መርጧል። እኔ ደግሞ አፍቃሬ ወያኔ የኦሮሞ ምሁራን ትግራይ ጎራ ሲሉ እንዳይቸገሩ ብቻ ሳይሆን – የምጣኔ ሀብት ግዛታቸውን የመሠረቱበትን ኦሮሚያን -ኦሮምኛ  ቋንቋ ቢያጠኑ መርጣለሁ። (‘ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ቢሆንም’*- እኔ እንኳ ቆርቻ ቡዳ ነኝ።)
*በመጨረሻ ስዊዘርላንዶች  በእንግሊዝኛ ከዓለም ይግባባሉ።
*
አመራሮቻችን ዳርና ዳር እንደ ገመሬ ዝንጀሮ ጎፈራቸውን ነስንሰው – የቀዝቃዛው ዓለም ጦርነት ይመስል – “አንደራደርም” የሚል ለውይይት ዝግ የሆነ – ፅንፈኞችን ለማስደሰት የሚወረወር – ተራ የእብሪትና የስንፍና ቃል ለትውልዱ ከሚግቱ – ጉዳዩ ዋል አደር ብሎ ይታይ – ኦሮሞ ‘ዱቢን ሀቡልቱ’ (ነገሩ ይዋል ይደር) ይልና በጥሞና በያኣ ጉባኤ፣ በኮራ ጉባኤ እና ከፍ ብሎ በጉሚ ጋዮ (ታላቁ ምክር ቤት) ተመካክሮ ይወስናል ይላል።
‘አንደራደርም!’ – ጭብጨባ በጭበጭ በጭ በጭ
አንደራደርም)))) – ሲጀመር የስልጡን ቋንቋ አይደለም።
የቅዱስ ቁርአንና የመፅሐፍ ቅዱስ ዶግማ ይመስል “አንደራደርም ኝኝኝኝኝኝኝኝ)))) ቃሉ ራሱ ይቀፍፋል።
*
አንደራደርም” – የሚለውን የወረደ የዘቀጠ የተነወረ የቆሸሸ አገላለፅ ከዛሬ ጀምሮ ከፖለቲካ መዝገበ ቃላችሁ ሰርዙት።
ትውልዱን ምን ልታስተምሩት ነው?!
*
ሰኞ ያደነቅናችሁ – ማክሰኞ እየወረዳችሁ ተቸገርን።
ኤዲያ ሀገር ‘በአክቲቭ ቢስቶች’ ስትመራ ያስጠላል።
ቆፍጠን በሉ። ዕንቁ ሥራ እየሠራችሁ ስናደንቅ – በጎን እየተልፈሰፈሳችሁ የሀገር  ወኔ አትስለቡ!!!
*
በመጨረሻ አማርኛ ኤርትራም ጂቡቲም ሶማልያም ኬንያም ሱዳንም ተሻግሮ ይነገራል። የኤርትራውም የጂቡቲውም ፕሬዚደንት አቀላጥፈው ይጠበቡበታል።
Filed in: Amharic