>

በሚሊኒየም አዳራሽ ታሪክ ሰራ! " ልጆቻችን ፍቱ!" ታላቅና አስፈሪ የህዝቡ ድምጽ!...

በሚሊኒየም አዳራሽ ታሪክ ሰራ!
” ልጆቻችን ፍቱ!” ታላቅና አስፈሪ የህዝቡ ድምጽ!!!
ሰለሞን ይግዛው
√• በእለተ ሰንበት በሚሊኒየም አዳራሽ የተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን የታሰሩ ሁሉ እንዲፈቱ በአንድ ድምፅ ፣በታላቅ ቁጣ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።
√• ባንድ ስትቆም እንኳንስ ጠላት፣ ይርዳል መሬት ።  ሀቅ በእግሯ ሄደች።  ሞተዋል አሸማቀናቸዋል አስረናቸዋል ብለው ተስፋ የጣሉብን እነ አብይ ይህን ዜና ሲሰሙ አማራ የሞት ፅዋ እንደማይገው ይረዳሉ 1000 አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች መፈጠሩን በሚገባ ይረዳሉ፡፡
“ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ፣ ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል አማራን እያሸበሩ ነው!” – ከተቃውሞ ድምጾች የተወሰደ
 የሚሊንየም አደራሽ ተቃውሞ ዝርዝር መረጃ
—-
…. መድረክ አስተዋዋቂዋ መድረኩን ለአዲስ አበባ አማራ ሴቶች ማህበር ሰጠች። የአማራ ሴቶች ማህበር ሰብሳቢዋ ረዘም ያለና አሰልች የሚባል ንግግር አደረጉ። እሳቸውም ለአማራ ክልል ኘሬዝዳንት ለአቶ ተመስገን ጥሩነህ አስተላለፉ።
አቶ ተመስገን ገና ስማቸው ተጠርቶ ወደ አትሮኖሱ እንደ ደረሱ ተቃውሞው ተጀመረ። የአማራ ጀግኖቻች ይፈቱ፣ የአማራ ብሄርተኝነት አዳኛችን ነው፣ እርሰዎ አማራን ለማገልገል ሳይሆን ኦነግን ወክለው ነው ወደ ክልሉ የመጡት .. እና መሰል ድምፆች ተሰሙ።
ቀጥለው ኢንጂነር ታከለ መድረኩን ያዙ። እሳቸውም መሰል ተቃውሞ አስተናገዱ። የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶችን እያሰሩ ነው፣ እርሰዎ ለኦነግ እንጂ ለመላው የከተማዋ ህዝብ አልቆሙም፣ የአብን አመራሮችን አሳስረሃል፣ የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞችን አስረሃል … የሚሉ ትችቶችም ከፍ ብለው ተሰሙ።
ከዚህ ከቀጠለ ተቃውሞው በርትቶ ኘሮግራሙን ያበላሻል በሚል አንድ መፍትሄ ተቀመጠ። ምክንያቱም በኘሮግራሙ ንግግር ያደርጋሉ ተብለው ከተጠቀሱት አካላት ገና “የባህል ሚንስትሯ እና የክብር እንግዳዋ ኘሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ” ንግግር አላደረጉምና ነው።
በዚህም ታዳሚው የአቶ ዮሐንስ ቧያለው ምስል በእስክሪኑ ሲታይ “የአማራ መሪ ዮሐንስ ነው፣ አቶ ተመስገን ጠላታችን ነው” የሚል ተቃውሞ ስለነበር አቶ ዮሐንስ ንግግር እንዲያደርጉና እንዲያረጋጉ ተጋበዙ።
አቶ ዮንስም “ለንግግር ሳይዘጋጁ፣ ምንም አይነት ¨ስፒች¨ ሳይዙ” ከመቀመጫቸው ተነስተው ንግግር አደረጉ። ጭብጨባው ደራላቸው፣ የእኛ መሪ፣ ጀግና፣ ደፋር … የሚሉ ሙገሳዎችም ተቸራቸው። እርሳቸውም በድጋፍ ጩኸቱ ንግግራቸውን ያቋርጡ ነበር። በተደጋጋሚም “አመሰግናለሁ፣ ክብር ይስጥልኝ” እያሉ ምስጋና ያቀርቡም ነበር።
በመቀጠልም ትንሽ ሲረጋጋ የባህል ሚንስትሯ ለመስማት የሚከብድ፣ የተቆራረጠና እጅ እጅ የሚል ንግግር አደረጉ። በዚህም በዮሐንስ ንግግር ቁሞ የነበረው ተቃውሞና ጩኸት፣ የእርሳቸውን ንግግር በመተው “ጀግኖቻችን ይፈቱ” እና መሰል ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጠለ። በመጨረሻም ሚንስትሯ ኘሬዘዳንቷን ጋበዙ።
ኘሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር ሲጀምሩም ተቃውሞው ቀጠለ። ኘሬዝዳንቷ ቢጨንቃቸው “አንድ ጊዜ አዳምጡኝ” በማለት ተማፅነዋል ሰሚ ባያገኙም።
~~~~~
በአጠቃላይ ተቃውሞው ሰዎኛ ነው፣ ይጠበቃልም። አዲስ አበባና ባህርዳር ከትህነግ የተረፈው የአማራ ወጣት ያለ ምክንያት ዘብጥያ እየወረደ ነው። እየተሳደደና እየተንቋሸሸም ነው። እናም በሁለቱ ሰዎች የደረሰባቸው ተቃውሞ ጥሩ lesson የሰጠ ነበር።
የሁለቱ መሪዎች የተቃውሞ መነሻም በአጭሩ “ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ፣ ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል አማራን እያሸበሩ ነው” የሚል ነበር።
Filed in: Amharic