>

ኦነጋውያን የኢትዮጵያን ፊደል ለምን ይጠሉታል?  (አቻምየለህ ታምሩ)

ኦነጋውያን የኢትዮጵያን ፊደል ለምን ይጠሉታል? 
አቻምየለህ ታምሩ
ኦነጋውያን በኢትዮጵያ ፊደል እንዳይጽፍና እንዳይማር እያስገደዱት ያለው ሕዝብ  የኦሮሞ ባሕልና ቋንቋ በግድ ሳይጫንበት በኢትዮጵያ ፊደል የሚጽፍ፣ በግዕዝ የሚቀድስ፣ በሌላው የሴም ቋንቋ በአረብኛ ዱአ ያደርግ የነበረውን ክርስቲያንና ሙስሊም የነበረ ሕዝብ ነው።
ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል የሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ  ከአባ ገዳዎችና ከተወላጆቻቸው በስተቀር የተቀረው የኦሮሞ ባሕልና ቋንቋ በግድ ሳይጫንበት የሐድያ፣ የሲዳማ፣ የአማራ፣ የከምባታ፣ የትግሬ፣ የጉራጌ፣ የዝይ፣ የዳሞት፣ የጋፋት፣ የአርጎባ፣ የጋሞ፣ ወዘተ ተወላጅነት የነበረውና ሙስሊምና ክርስቲያን የነበረ ሕዝብ ነው። ይህንን ታሪክ አረቦችም አውሮፓውያኑ የጻፉት እውነት ነው።
ክርስቲያን የነበረውና በግዕዝ ይቀድስ የነበረው ይህ ሕዝብ  እስከ ጳጳስ የደረሰ የነፍስ አባት ነበረው። ለዚህም ዝቋላን፣ አዳዲ ማሪያምን፣ ዝዋይን፣ መናገሻን፣ጎላ ሚካኤልንና  ደብረሊ ባኖስን የደበረ፤ ባሊ የሚገኘውን  የላሊበላ ውቅር ገዳም  የፈለፈለ  ሕዝብ  መሆኑን እንደ አብነት ማንሳት ይቻላል። ይህ ሕዝብ ኦሮምኛ ተጭኖበት ኦሮምኛ መናገር ሳይጀምር ማንም ሳይጭንበት የራሱ የሆነውን ግዕዝን  ያውቅ የነበረ ሕዝብ ነው።
ኦነጋውያን ይህን ኦሮምኛ የተጫነበት  ሕዝብ ከኦሮምኛ በፊት ያውቅ በነበረው በኢትዮጵያ ፊደል  እንዳይጽፍና እንዳይማር እያደረጉት ያለው ሕዝብ አገር የመመስረት እቅዳቸው እንዳያጨናግፍባቸው ነው። ለዚህም ነው እድሜ ዘመናቸውን በመሳደብና የውሸት ታሪክ መፍጠርን፣ የሌለ ነገር  እንዳለ አድርጎ ማወናበድን እንደ ዋና  የፖለቲካ  አላማ አድርገው የያዙት።
ኦነጋውያን ኦሮምኛ በግድ ሳይጫንበት በኢትዮጵያ ፊደል ይጽፍና በግዕዝ ይቀድስ የነበረውን ሕዝብ በአባቶቹ ሥልጣኔ በግዕዝ እንዳይማርና እንዳይጽፍ እያስገደዱት ያለው እውነቱን ሲያውቅ በሞጋሳና ሜዲቻ ተገዶ የተጫነበት ማንነት አሽቀንጥሮ ጥሎ ወደ ቀደመ ማንነቱ ይመለሳል ከሚል ፍራቻ ነው። ግዕዝን የማያውቁት  ኦነጋውያን ሁሉ የማያውቁትን ግዕዝን  አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ እስኪሰማቸው የሚጠሉት ኦሮምኛ በግድ ሳይጫንበት በራሱ ፊደል ይጽፍና በራሱ ቋንቋ ይቀድስ የነበረው ሕዝብ  ከተቀረው ወንድሙ እኅቱ ጋር የሚገኘው ግዕዝ በሚባል የኢትዮጵያ ድልድይ ነው ብለው ስለሚያስቡ ነው።
ይህንን ድልድይ ለመስበር ነው  እንግዲህ  አባገዳዎች ገርባ አድርገውት ሲጨቁኑት የኖሩትን ሕዝብ ዛሬ ደግሞ እንዳስፈለፈሉት ጫጩት የሚቆጥሩት ኦነጋውያን ኦሮምኛ ተገዶ እንዲናገር ከመደረጉ በፊት አባቶቹ ይጽፉበትና ይቀድሱበት የነበረውን  የኢትዮጵያን ፊደል እንዳያውቅና በኢትዮጵያ ፊደል እየተጻፈ  ማንም ሳይጭነው የኢትዮጵያውያን የጋራ መግባቢያ ለመሆን የበቃውን  አማርኛን እንዳያውቅ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ያለው።
ትናንት አባገዳዎች ቋንቋውን አጥፍተው፣ ማንነቱን በተሳካ ሁኔታ ቀይረው፣ ባሕሉን ነጥቀውና ከርስቱ አልፍነው ሲጨቁኑትና ባርያ አድርገው ሲሸጡት የኖሩት አንሶ ዛሬ ደግሞ በኦነጋውያን  ዘንድ እንደስፈለፈሉት ጫጩት እየቆጠረ  ያለውና አባቶቹ ተገደው ኦሮሞ ከመደረጋቸው በፊት ይጽፍበትና ይቀድስበት በነበረው የኢትዮጵያ ፊደል እንዳይጽፍና እንዳይማር እተገደደ ያለው ሕዝባችን ፍትሕ ይገባዋል።
Filed in: Amharic