>
5:14 pm - Wednesday April 20, 0659

አታቃጥሉን፣ አታንድዱን፣ አትረዱን የሚል መልእክት ለሰይጣንም ለመንግሥትም ይተላለፍ!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

አታቃጥሉን፣ አታንድዱን፣ አትረዱን የሚል መልእክት ለሰይጣንም ለመንግሥትም ይተላለፍ!!! 
    ዘመድኩን በቀለ
 ውግዘት፣ ሕግ ማስከበር እና ሀገር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግን በተመለከተ የምለው አለኝ።  
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ 
• ለኦህዴድ/ኢህአዴግ መንግሥትና 
• ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ምእመናን በሙሉ በያላችሁበት።  
•••
ሰሞኑን እኔም እንደማንኛውም ዜጋ ነገሮችን ከዳር ሆኜ በማየት ጊዜዬን እያሳለፍኩ ነው። በዚሁ መልኩም እቀጥላለሁ። በቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችና በምእመናን ልጆቿም በኩል የሆነ መነቃቃት ያለም ይመስላል። እናም “ ከእንግዲህ ስንሞት፣ ስንገደል፣ ስንቃጠል አታገኙንም” የሚለው ድምጽ መንግሥቱን የረበሸው ይመስላል።
•••
ኮሪያን ለመጎብኘት ወደ ሴኡል ያቀናው አቢይ አህመድም እንደመሪ የሚቀበለው የመንግሥት ባለ ሥልጣን አጥቶ እሱ ተዋርዶ ሀገሪቱንም አዋርዶ ከማሸማቀቁም በላይ በዚያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞም ገጥሞታል። በቤተ ክርስቲያን ላይ በኢትዮጵያም ላይ ዘብቷል አቃሎናልናም ቅሌትን በቁሙ ይጨልጣታል።
•••
በተለይ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ስላለው ነገር ገና ከቤተ ክርስቲያን አምላክ ፍርዱን ይቀበላታል። አሁንም በኮሪያ ተቃውሞ ስላቀረቡበት ጉዳዩ በዓለም አቀፍ መድረክ መነሳቱ ሰውየውን አዲስ አበባ ደውሎ የሰላም ሚንስትሯን ወደ ቤተ ክህነት እንድትሄድና የማድበስበስ፣ የማደንዘዝ ሥራ እንድትሠራም አስገድዶታል። ልብ በሉ እስከ አሁን መንግሥት በሲዳማ ለደረሰው የቤተ ክርስቲያን ውድመት ምንም ትንፍሽ ያለው ነገር የለም።
•••
አሁንም የእኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕጋዊ መልኩ ባለ ሀገርነቷን፣ ባለ ቤትነቷን በሚገባ በገሃድ በማያሻማ መልኩ ማሳየት አለባት።  የማንም የግብፅና የዐረብ ተላላኪ ባንዳ ወሃቢያ አሸበርቲ ሁላ ከመሬት ተነስቶ አፉን ሲከፍት፣ በጡሩንባ ተጠራርቶ አንድ ቦታ ሲሰግድ ብዙ የሆነ እየመሰለው ሲንበጫበጭ፣ በዚህም ተገፋፍቶ ከመሬት ተነስቶ ጥሬ ካካውን ካልተጸዳዳሁባችሁ የሚለውን፣ እሳት በኪሱ፣ ሰይፍም በጎኑ ይዞ ምቹ ጊዜ እየጠበቀ ሊያቃጥለንና ሊያርደን የሚዞረውን አሸበርቲ ሁላ በሕግ አግባብ ልታስተነፍሰው ይገባል። ይሄ ተፈጥሮአዊም ሕገ መንግሥታዊም መብት ነው። ሰጪም ነሺም የለውም።
•••
የሚወገዙ ይወገዙ። በሕግ አግባብ የሚጠየቁት ይጠየቁ። ሀገር አቀፍ ዓለሙ ሁሉ የሚያየው የሚታዘበውም ሰላማዊ ሰልፍም ይካሄድ። ያኔ ብዛት የሚለው ትርጉም ለሁሉም ይገባዋል። እንዲህ ይደረግ። በኢትዮጵያም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣው መከራ ባይቀርም መኖራችንን ማሳየቱ ግድ ነው። እናም በግድ ይደረግ።
ሀ፤ ፦ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመጀመሪያ ከሁሉ አስቀድሞ ይሄን የስመ “ቄስ” #በላይ_መኮንን የተባለው ጆቢራ የጃዋር ቡችላ፣ የበላበትን ወጪት ሰባሪ ግለሰብ በቶሎ፦ 
• ይወገዝ
• ከክህነቱም ይሻር
• በሕግም ይጠየቅ
•• ይህ ግለሰብ ሲበዛ ነውረኛ ነው። ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአደባባይ አዋርዷታል። ሰድቦ ለሰዳቢም ሰጥቷታል። የክርስቶስን ሥጋና ደም በፈተተበት እጆቹ ኢሬቻ ሄዶ ለቦረንትቻ፣ ለጣኦት የተሰዋ የበሬ ደም ግንባሩን ተለቅልቆ ሰማያዊና የከበረች ክህነቱን በአደባባይ ጥሏታል። ለቆሪጥ ሰግዷል። ከወሃቢያ እስላሞች ጋርም ገጥሞ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ከፍተኛ ደባ ፈጽሟል። በታቦት ላይ ቀልዷል።
•••
በእነ ጃዋርና በእነ ፀጋዬ አራርሳ መንፈስ ተመልቶ ሰሜነኞቹ ያላቸውን ነገዶች ዐማራንና ትግሬን በግልጽ ጠቅሶ ወራሪና ሌባ፣ ለማኝም ናቸው በሎ ተሳድቧል። በዚህም ድርጊቱ የንስሐ ልጆቹንም ቤተ ክርስቲያንንም አሳዝኗልና ይሄን ነውረኛና በሌብነቱ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተባረረን ግለሰብ ቅዱስ ሲኖዶሱ በእውነት በህይወት ካለ በአስቸኳይ ተሰብስቦ ክህነቱን ይያዝበት። ይወገዝ። ከክርስቲያኖችም ኅብረት ይወገድ። ይሄ ቦረንትቻም የሆነ ቂዥቢ እነ ጃዋር ክህነቱን በቄሮ ዱላ ሲያስመልሱለት እስቲ እናያለን።
•••
እደግመዋለሁ ቅዱስ ሲኖዶሱ በአስቸኳይ ይሰብሰብ፣ ይወስንም፣ ያውግዘውም። ሲኖዶሱ ጥርስ ያውጣ። መንከስም ይጀምር። የኢትዮጵያ እንጂ የኦሮሞ፣ የዐማራ፣ የጉራጌ፣ የትግሬ፣ የደቡብ የሚባል ሲኖዶስ የለንም። የእሜቴ ግብፅ የአጅሪት ካይሮ ሴራም የሚከሽፈው እንደ ቄስ በላይ ዓይነቱ ጆቢራ ሌባ አጭበርበርቲ ግለሰብ ልክ ሲገባ ነው። ቆቡን ያውልቅ፣ መስቀሉንም ይመልስ። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም በየ ቦታው ተደንስሮ የሚቀባዥረውንም ቅዠት እንዲያቆም በሕግ ይከልከል።  አከተመ።
ሁ፤ የኢህአዴግ/ኦህዴድኦነግ መንግሥት በአስቸኳይ የደቡብ ክልሉን ፕሬዘዳንት አቶ ሚሊዮን ማትያስን፦  
• ይታገድ [ ታግዷል ]
• ይታሰር
• አብዲ ኢሌም የገባበት ጉድጓድ ገብቶም ይጠየቅ።
•••
ሚሊዮን ማትያስ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪና በሃይማኖቱም ልክ እንደነ አቢይ፣ ለማ፣ ሽመልስ፣ ታከለ፣ የጃዋር ሚስት ጴንጤ የሆነ ግለሰብ ነው። አብዲ ኢሌ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ነበረ። አምና በቁጥር 10 የሚደርሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን እንደጧፍ እንዲነድዱ ያደረገ፤ ምክንያትም የሆነ ግለሰብ ነው ተብሎ ተወንጅሎ የታሰረም ግለሰብ ነው።
•••
ሚልዮንም እንደ አብዲ ኢሌ ነው መጠየቅ ያለበት። በእሱ አመራር ሰጪነት ወደ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት በሲዳማ ዞን እንደ ችቦ ነድደዋል። አመድም ሆነዋል። ሃሌ ሉያ እያሉ እየዘመሩ ጉራጌ፣ ወላይታና ዐማራን አሳርዷል። ጊዜው የጴንጤ ነው ተብሎ ዝም ችላም ካልተባለ በቀር አቶ ሚልዮንም አብዲ ኢሌ የገባበት ጉድጓድ ሊገባት ግድ ይለዋል።
•••
ባለፉት ወራት ይሄንኑ አጀንዳ ይዘን ይሄ ሰውም ልክ እንደ አብዲ ኢሌ ለምን አይጠየቅም? አይታሰርምም? ብለን ጮኸናል። ኢጄቶን አደራጅተው ወላይታዎችን በአደባባይ ቤንዚን ጭሮ ሲያነድ የነበረው አቶ ቴዎድሮስ ጭራሽ ሥልጣን ተሰጥቶት ቆይቶ ገና ሰሞኑን ነው ግፊቱ ሲበዛ ጊዜ ያዝነው፣ በቁጥጥር ስርም አዋልነው ያሉት።
•••
አሁን አቶ ሚሊዮን ከፓርቲው መታገዱ ተሰምቷል። መታገድ ብቻውን በቂ አይደለም። እንዲያም ብሎም ነገር የለም። አብዲ ኢሌ የገባበት ጉድጓድ መግባት ነው ያለበት። በኢትዮጵያም ሆነ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ከሚመጣው መከራ የሚያድነን አንዳች ኃይል ባይኖርም እንኳ መከራው እስኪመጣም ቢሆን እንዲህና እንዲያ እያልን እየተሟገትን መቆየቱ አይከፋም።
★ ረሃብና ሰይፍ አይቀሬ ነው ይላሉ በረኸኞቹ። ንስሐ እንግባ። ሊመጣ ያለውን ሰማዕትነት ተዘጋጅተንም እንጠብቅ። ዝርዝሩን እመለስበታለሁ። ይቆየን።
•••
ሂ፤ ፦ ጃዋር መሃመድ 
የእሱ ዘመኑ አልተፈፀመም። እህል ውኃውም አላለቀም። አሁን እሱ ተቆጪም፣ ገልማጭም እንዳይኖረው ተደርጓል።  እስከ ጊዜው ድረስ ይፈንጭ። ፀሐይ እስክትወጣ ይራወጥ። ግን ነገሮች ሁሉ በዚህ መልኩ አይቀጥሉም። ሄሮድስን የነካው የጌታ መልአክ ይነካዋል። በስብሶና ተልቶም ይወገዳል። በቁሙ ሲኦልን አይቶ ይሄዳል። የቤተ ክርስቲያን አምላክ ፍርዱን ሁሉም እያየ ይሰጠዋል። ቱ ምን አለ ዘመዴ በሉኝ። የዐቢይ አህመድ መንግሥት እንዲናቅ፣ እንዲጠላ ሊያደርግ የተላከም መልእክተኛ ነውና እስከ ጊዜው ድረስ፣ እርስ በራሳቸው እስኪበላሉ ድረስ ይቀመጥ።
•••
ሃ፤ ፦ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ወጣቶች በሙሉ
 ከመጪው የመስቀል በዓል በፊት ሀገር አቀፍ ሰልፍ ብታዘጋጁ መልካም ነው ባይ ነኝ። በሰላማዊ መንገድ መብትን የሚጠይቅ፣ አታቃጥሉን፣ አታንድዱን፣ አትረዱን የሚል መልእክት ለሰይጣንም ለመንግሥትም በያሉበት እንዲደርሳቸው የሚያደርግ መስቀለኛ ሀገር አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ ቢዘጋጅ መልካም ነው። በሰለማዊ መንገድ ለመንግሥት ጥያቄ የሚቀርብበትን መንገድ ፈልጉ።
•••
መቼም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰልፍ ለማዘጋጀት ከኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አታንስም። የኢትዮጵያ ቡናም ሆነ የጊዮርጊስ ደጋፊዎች በአብዛኛው ልጆቿ ናቸው። ከታከለ እና ከአቢይ ስር የሚያዘጠዝጡት አብዛኛዎቹም ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። እናም ሰላማዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ቡና ልጆች አታንስምና በጨዋ ደንብ ተዘጋጅቶ በጨዋ ደንብ የሚጠናቀቅ ሀገር አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በቶሎ።
•••
የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ፣ የከንቲባው ጽ/ቤት፣ የእስልምና ጉባኤ፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ድርጅቶች፣ ኢቲቪ፣ ራዲዮ ፋናና ሸገር፣ ዋልታም አዲስ ዘመንም የማይዘግቡትን በደላችንን ዓለሙ ሁሉ ይስማው። ይመልከተውም። ይኸው ነው። ከነሙ ጋ ዱቢን።
•••
ሻሎም !   ሰላም !   
ነሐሴ 21/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic