>

ገራፊያቸው ህወሃት ከስልጣን ወርዶ እንኳ ተገራፊዎቹ ዛሬም ታማኝ ካዳሚዎቹ ናቸው!!! (መስከረም አበራ)

ገራፊያቸው ህወሃት ከስልጣን ወርዶ እንኳ ተገራፊዎቹ ዛሬም ታማኝ ካዳሚዎቹ ናቸው!!!
መስከረም አበራ
*  እነ አባ ዱላኮ እዛው ደደቢት ቁጭ ብለው ነበር ምን የመሰለ ዳቦ ሲጋግሩ ውለው እሱ ሲያልቅ ደሞ ወደ ወደ ምሽግ ቁፈራ ይሰማሩ የነበረው። ስራን መስራት እንዲህ ቀልብን ሰብስቦ አንድ ቦታ ተቀምጦ ነው ¡ እነዚህ ሰዎች ወደ መቀሌ የሚጓጓዙት የህወሃት ዱላ እና ሃይላንድ ናፍቋቸው ከሆነም ወደ ባዶ ስድስት መከተም ነው፤ ምን መመላለስ ያስፈልጋል!!!
በምድር ላይ እንደ ህወሃቶች እና የኦሮሞ ብሄርተኞች የሚገርመኝ ሰው የለም። ህወሃቶች ለምን ይገርሙሻል የሚለኝ የለም መቼም! የሚል አይጠፋም ከተባለም ከሌብነታቸው ድርቅናቸው ፣ከዘረኝነታቸው ጭካኔያቸው ፣ከአልጠግብ ባይነታቸው አልሸነፍ ባይነታቸው እየተሽቀዳደሙ ያስገርሙኛል።
 የኦሮሞ ብሄርተኞች የዘወትር አድሮቃሪያነት፣ ሁል ጊዜ በአንድ ዜማ ማልቀስ(ምኒልክ የሚል አዝማች ባለው)፣ ሁሉን ነገር የእኔ ሲሉ አድማጭ ይሰለቸን (ነው ይታዘበን?)ይሆን ለማለት አፍታ የማያባክኑ መሆናቸው፣ የተማሩት በተለይ ስለዘራቸው ፖለቲካ ማውራት በጀመሩበት ቅፅበት ምሁራዊ ሚዛናዊነት ለድንገቴ ንዴት ብቻ ሳይሆን የውሸት ተረክ አስረክቧቸው የሚሸሻቸው ነገር የሁልጊዜ ግርምቶቼ ምክንያቶች ናቸው።
 ከነዚህ በላይ እጅግ የሚደንቁኝ ደግሞ የቀድሞ ገራፊያቸው ህወሃት ከስልጣን ወርዶ ውቃቢ ርቆት እንኳን በደጀ ሰላሙ ሊሳለሙ የሚሄዱት የቀድሞ ተገራፊዎቹ የአሁን ከዳሚዎቹ ናቸው።
 የእነዚህ ሰዎች የመቀሌ ጉዞ በህፃንነቴ እናቴ አጓጉል ስቀብጥባት  “ዱላ አማረሽ?” የምትለኝን ነገር ያስታውሰኛል። መቼም የህወሃት ደጀሰላም የሚሄዱት ዛሬም እንደ ድሮው ፈርተውት አይሆንም። ከህወሃት ጋር መክረው ሃገር ሊገነቡ ነው የሚልም አይኖርም ፨ሃገር ለማፍረስ ከሆነ ደግሞመቀሌ ተቀምጠው እንደነ አባዱላ እንደ ድሮው ለአዲሱ የህወሃት ሰራዊት ዳቦ መጋገር እንጅ ወደ መሃል አገር እንደ ዘሃ ዘጊ መመላለስ አያስፈልግም ነበር።
 እነ አባ ዱላኮ እዛው ደደቢት ቁጭ ብለው ነበር ምን የመሰለ ዳቦ ሲጋግሩ ውለው እሱ ሲያልቅ ደሞ ወደ ወደ ምሽግ ቁፈራ ይሰማሩ የነበረው። ስራን መስራት እንዲህ ቀልብን ሰብስቦ አንድ ቦታ ተቀምጦ ነው ¡ እነዚህ ሰዎች ወደ መቀሌ የሚጓጓዙት የህወሃት ዱላ እና ሃይላንድ ናፍቋቸው ከሆነም ወደ ባዶ ስድስት መከተም ነው፤ መመላለስ አያስፈልግም።
ትህነግ ዘርፎአል፣ገድሏል፣አሰቃይቶ አፈናቅሏል። ይህ ከሰራቸው መጥፎ ስራዎች ውስጥ በጣም ትንሹ ክፍል ነው።
የቀድሞው አለቆቻቸው የወንበዴው ቡድን መሪዎችና አሽቃባጮች በደረሰባቸው ሕዝባዊ ግፊትና ተቃውሞ ሳቢያ ጭራቸውን ወሽቀው ወደ መቐለ ፈርጥጠዋል።
ለስልጣን ያበቃቸው የትግራይ ሕዝብ ነው። የሚፈልጉትን ስልጣን ሲያገኙ ሸውደውታል። እስከ መኖሩ ተዘናግተው ስልጣን የሰጣቸውን ጸጋ ሲያጣጥሙ ከርመው ቀን ሲከዳቸው የፈረጠጡት ወደእዚያው መከረኛ ሕዝብ ነው።
ዛሬም በስሙ ይነግዳሉ። በደልተኝነት ይሰማው ዘንድ ነጋ ጠባ ይወተውቱታል።በትግራይ የዴሞክራሲ ጭላንጭል የለም።ዜጎች በአሰቃቂ እስር ቤቶች በግፍ ይታሰራሉ።ለተቃውሞ ጨርሶ ቦታ አይሰጡም።ለስልጣናቸው አስፈሪ የመሰላቸውን ሁሉ በጭካኔ ይቀጣሉ።ይህ አረመናዊ ተግባራቸውን ለማስፈጸም በደህንነት ሰራተኞቻቸው መርዝ እስከ ማጋት ድረስ ርቀው ሄደዋል።
እነዚህ አንባገነኖች ዛሬ በመሃሉ ሐገር ያለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት የጨለመውን ተስፋቸው በውስጣቸው እንዲንሰራራ አድርጎታል።ዛሬ ብዙ ያኮረፍ የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኞች እዚህም እዚያም ተበትነው ይገኛሉ።ለሹመትና ለቆረጣ ብልጽግና አሰፍስፈው ነበር ይህ የተሳካላቸው አይመስልም።
ለትህነግ ይህ መልካም አጋጣሚ ነው።በቅርቡ በቀለ ገርባና እዝቅኤል ጋቢሳ በመቐሌ የተገኙት እንዲያው ዝም ብሎ የተደረገ የአካዳሚ ጉብኝት አይደለም።
እጅግ የረቀቀ ተልእኮ ያለው የፖለቲካ ስራ ነው። ትህነግና ኦነጎች መቼም ኢትዬጵያዊ ሆነው አያውቁም። ለእዚህ ዓላማቸው ልፍስፍሱ የአብይ አስተዳደር እንቅፋት ሆኖባቸዋል።ስለእዚህ በአንዳች ሤራ ሆነ በምርጫም ጭምር ቢሆን መወገድ አለበት!።ይህ ደግሞ የጨካኝ ብሔረተኞችን ስምምነት ይጠይቃል።
ስለ እዚህም ትህነግ፣ ኦነግ እንዲሁም በቀለ ገርባን የመሰሉ አደገኛ አክራሪዎች ተገናኝተው አንዳች ነገር ማድረግ የግድ ይላቸዋል!።
ትግሉ ቀጥሏል!። ወያኔ ዳግም ወደ ምኒልክ ቤተ መንግስት ለመመለስ እየተራወጠች ነው።ይሳካል!?። ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።
Filed in: Amharic