>
4:38 pm - Monday December 2, 2858

እኔ ነኝ። ደጋግሜ እኔ እኔ እኔ እላለሁ። ምክንያቱም እኔ ነኝ እንጂ እሱ እሷ እነሱ እነኛ አንተ አንቺ አይደለሁም። (መምህር ታዬ ቦጋለ አረጋ)

እኔ ነኝ። ደጋግሜ እኔ እኔ እኔ እላለሁ። ምክንያቱም እኔ ነኝ እንጂ እሱ እሷ እነሱ እነኛ አንተ አንቺ አይደለሁም። እ ኔ ነ ኝ።

መምህር  ታዬ ቦጋለ አረጋ
 
* አርቲስት ኤቢሳ አዱኛን ከነህይወቱ ከመኪና ኋላ የጎተተች ትህነግ፤ ነቀምት እናትን ልጇ አስከሬን ላይ ያስቀመጠች ትህነግ፣ ኦሮሞን 27 ዓመት የጨፈጨፈች ትህነግ፣ የገረፈች ያኮላሸች ታሪክ ለማርከስ የሰራች ትህነግ፣ ምሁራንን እንደውሻ በሰንሰለት ያሰረች ትህነግ፣ ለሠራቸው ግፍ የግፍ-ግፍ እውቅና ለመስጠት መቀሌ የምልከሰከስ አይደለሁም!!!
*ምሁር አይደለሁም – መምህር ነኝ። (በርግጥ ከመምህር በላይ ምሁር እንደሌለ አውቃለሁ።) *ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር አይደለሁም። (“የማደንቀው ጨረቃ ላይ የወጣውን ሳይንቲስት ሳይሆን – ሳይንቲስቱ ጨረቃ ላይ እንዲወጣ ያደረገውን መምህር ነው።” ያለ ጥበበኛ አውቃለሁ።” ደግሞም ያልተማሩ ምሁራን ያቆይዋትን ሀገር – የተማሩ ማይማን አያፈርሷትም ብያለሁ። መምህር ነኝ።)
*መምህር ነኝ – ዋሽቼ የማጣላ ሳልሆን – መዝኜ የማስታርቅ ታናሽ ሰው ነኝ። ሰው ነኝና ወገንን ሳከብር – ምን ታናሽ ብሆን ፈጣሪ ያከብረኛል።)
*ለዘረኞች = ልቦለድ እየፈጠረ የሚግተውና አንድ አጣቃሽ የሌለው ሀሰት – በመርዝ መልክ የሚግተው – ኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረእባብ (ግብረእባብ) ኦሮሞ ነው። “የገመቹ ለታ የልጅ ልጅ እና የደሱ ኦዳ ልጅ አማራ ነው።” = ዘረኝነት እስከዚህ ድረስ የሚያደነቁር በሽታ ነው። የአማርኛ መምህሩ ገብረኪዳን ደስታ (የታሪክ ምሁር) ሲባል ያልጎፈነነው = የእኔ ምሁር መባል የሚያመው ብዙ ነው። ምሁር ነኝ ብዬ አላውቅም መምህር ነኝ። ወገን በተለያዩ ማዕረጎች ፍቅሩን ለመግለፅ በከበሩ ስሞች ይጠራኛል። ጥሩኝ አላልኩም። ማእረጌ ክብሬ ኩራቴ መምህር ነው።
ለምሳሌ፦ የቦረናው እንቁ አርቲስት አቡሽ ዘለቀ = “ኦሮምኛና የኬንያን ጨምሮ ሌሎችን ቋንቋዎች ሲያቀነቅን ለእነርሱ  ጀግና ነበር። አሁን አማርኛን ስለዘፈነ “ጠላታችን ነው” አሉ። ሠፊ ዘመቻም ከፈቱበት። አቡሽ ዘለቀን የፈጠረው ፍቅርን የሚያመነጨው የቦረና ኦሮሞ መሆኑን አስተምራለሁ። መምህር ነኝ።
*መምህር ነኝ። = አርቲስት ኤቢሳ አዱኛን ከነህይወቱ ከመኪና ኋላ የጎተተች ትህነግ፤ ነቀምት እናትን ልጇ አስከሬን ላይ ያስቀመጠች ትህነግ፣ ኦሮሞን 27 ዓመት የጨፈጨፈች ትህነግ፣ የገረፈች ያኮላሸች ታሪክ ለማርከስ የሰራች ትህነግ፣ ምሁራንን እንደውሻ በሰንሰለት ያሰረች ትህነግ፣ ለሠራቸው ግፍ የግፍ-ግፍ እውቅና ለመስጠት መቀሌ የምልከሰከስ አይደለሁም። “የፈሰሰው የኦሮሞ ደም የኔ ነው። ፍትህ ለኦሮሞ ህዝብ!” ብሎ መስዋዕትነት የከፈለልኝ ወገኔ ዘንድ ባህርዳር ሄጃለሁ = ምክንያቱም መምህር ነኝ።
(ለፅንፈኞች ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ ኦሮሞ አይደለም። ተስፋዬ ግብረእባብ ኦሮሞ ነው። ፅንፈኝነት እስከዚህ ድረስ ይዘቅጣል። – የኦሮሞን ስነልቡና ፈፅሞ አታውቁትም።)
*27 ዓመት በዐይኔ በብረቱ ያየሁትን የቴሌቪዢን ሰቆቃ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ተጠቂዎችን በአካል አግኝቼ የሰማሁትን የግፍ እውነት = “ይህንን እንርሳው!” ብዬ ዘግቼ = ከዛሬ 130 ዓመት በፊት የተፈጠረን ትርክት “አልረሳውም” ብዬ የጥላቻዬን ጥግ የማሳይ ከንቱ አይደለሁም። መምህር ነኝ።
* ለትላንት ታሪክ ከሳሽ ተከሳሽ ዳኛ ፈራጅ ምስክር በሌለበት የትውልዱን ህይወት ለማበላሸት የምጥር የማናክስ የማጋድል አይደለሁም። መምህር ነኝ።
‘ትላንት ያላችሁት ታሪክ ሆነ ብለን’ እንውሰድ – ዛሬ ደጋግማችሁ የምታነሱበት ዓላማ ምንድነው?! ቢባል ምን ይሉ ይሆን?! = መነሻቸው ወገን በማናከስ ትርፍ ማግበስበስ ነው።
*ለሆዴና ለፍርፋሪ አድሬ ሀገር አልሸጥም። መምህር ነኝ።
*
*ምሁር አይደለሁም። ለ30 ዓመታት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ አስተምሬያለሁ። ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ዳይሬክተር ሆኜ አገልግያለሁ። ምሁር አይደለሁም – መምህር ነኝ። * መራራ እውነት በኢትዮጵያ ታሪክ = የሚል የምርምር ሥራዬን የሚገልፅ መፅሐፍ ፅፌ ለወገን አበርክቻለሁ። የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ገዳና ዋቄፈና፣ መፅሐፈ ነገሥት፣ ልጇ አፋርና ኢትዮጵያ፣ የቦረና እና የጉጂ ያልተነገሩ ትውፊቶች))) የተሰኙ የምርምር ሥራዎቼ ተገባድደው ለህትመት ተቃርበዋል። ምሁር አይደለሁም = የያዝሁትን ለመወርወር ያላመነታሁ መምህር ነኝ።
* በሠራሁባቸው ሥፍራዎች በሙሉ ሽልማት ኖሮ ያላለፈኝ፣ ቤተሰቦቼን የሙያ ባልደረቦቼን የሠፈሬን ወገንና መላውን ኢትዮጵያ ያለልዩነት የምወድ የማከብር ለሀገሬ ራሴን የሰጠሁ መምህር ነኝ። ሀገር አልሸጥም፣ በፍቅረ ንዋይ አልገዛም፣ አልረክስም፣ ወዘተርፈ
*የትኛውም ዘመቻ በፅንፈኞች ቢከፈትብኝና የእንጭራሪት ጭርጭርታና የእንቁራሪት ቁርቁርታቸው ከአስቀያሚ አፋቸው ጋር ቢከፈት የማልበገር መምህር ነኝ።
*ተስፋዬ ግብረእባብ = ስሜን እየጠቀሰ በመደበኛና በበርካታ የፌስቡክ አካውንቶቹ ስም የማጠልሸት ዘመቻ ከፍቷል – ዐይታችሁታል። ፀጋዬ ረጋሳ አራርሳ ስሜን አየጠቀሰ የተለያዩ አርቲ ቡርቲዎች ከትቧል። በፌክ አካውንቶቹም ዘምቶብኛል። ወያኔዎች ሌት ተቀን ስሜን በማጠልሸት ተጠምደዋል። ፅንፈኞች ያለማቋረጥ መጠነ ሠፊ ዘመቻ ከፍተውብኛል። የተዘመተብኝ ኢትዮጵያዊነትን በማቀንቀኔና የሀሰት ትርክታቸውን መናድ በመጀመሬ ነው። በተረፈ ሀገር ውስጥ ፊታቸው ላይ ነበርሁ። በግብሬም ቀና ብዬ የምራመድ ነኝ = ያውም ከ1990 እስከዛሬ 2011 በኖርሁበት ቦሌ ክፍለ ከተማ – ዐዲስ አበባ።
 ሆኖም ብዙ ቢመስሉ ቀርቶ የእውነትም መአት ቢሆኑ – ባንዳ ባንዳነቱን አይስትምና አያስጨንቀኝም። ኢትዮጵያዊ መምህር ነኝ = ከጣሊያን ካበሩ ሺህ ባንዳዎች ጋር የተፋለሙ የነጃገማ ኬሎ፣ አቢቹ፣ በላይ ዘለቀ፣ አብዲሳ አጋ፣ ሸዋረገድ ገድሌ፣ አበበ አረጋይ፣ ደስታ ዳምጠው = የአርበኞችና የነፍጠኞች ልጅ ነኝ።
*
ከነርሱ ጫጫታ ይልቅ = በዝምታ ውስጥ ያለው መቶሚሊየን ኢትዮጵያዊ ከጎኔ ነውና አንዳች የማልፈራ መምህር ነኝ። መምህር መሆኔን ተማሪዎቼና የሥራ ባልደረቦቼ ይመሠክራሉ። የመምህርነት ትርጉሙ ሠፊ ነው። ምሁር አይደለሁም = ምሁራንን ያፈራሁ መምህር ነኝ። አዎ የሆንኩትን መምህር ብላችሁ ጥሩኝ። ኩራቴ ደስታዬ ሙያዬ የማላፍርበት መምህርነት ነው።  ስለሆነም መምህር ብላችሁ ጥሩኝ። እኔ ነኝ። ደጋግሜ እኔ እኔ እኔ እላለሁ። ምክንያቱም እኔ ነኝ እንጂ እሱ እሷ እነሱ እነኛ አንተ አንቺ አይደለሁም። እ ኔ ነ ኝ።
Filed in: Amharic