>

በኦ.ዲ.ፒ ስፖንሰር አድራጊነት - በኦሮሞ ባህል ማእከል ቤተ ክርስቲያንን የመሰንጠቅ ሴራው ሊጎነጎን ቀን ተቆርጦለታል!!! (ታደለ ጥበቡ)

በኦ.ዲ.ፒ ስፖንሰር አድራጊነት – በኦሮሞ ባህል ማእከል ቤተ ክርስቲያንን የመሰንጠቅ ሴራው ሊጎነጎን ቀን ተቆርጦለታል!!!
ታደለ ጥበቡ
 
  * ጃዋር ፈረሱ ቀሲስ በላይ መኮንን “የኦሮሞ ኦርቶዶክስ” ቤተክርስቲያን ለማቋቋም መግለጫ እንሰጣለን እያለ ነው!!! 
*አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አንድ ጠቅላይ ቤተክህነት፣ አንዲት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እንጂ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አትከፈልም። ነገር ግን የኦነግ ሰዎች “የኦሮሞ ኦርቶዶክስ” እንመሰርታለን ብለው መግለጫ ለመስጠት ደብዳቤ ለሚዲያዎች ጽፈዋል።
   የጃዋር አህመዱ አድራሽ ፈረሱ የወሮ በላው የበላይ መኮንን  ደብዳቤ በአፋን ኦሮሞም በአፋን አማራው በአፋን ሲዳማ የተጻፈው ደብዳቤ ደርሶኛል። እናንት ደብዳቤውን የጠየቃችሁኝ ወሳኝ አካላት ይኸው ውሰዱና የሚሆነውን አድርጉ። ይኸው ነው።
*የዚህ ሁሉ ድራማ ዋና ተዋናዩ የጃዋር ፈረስ ቄስ በላይ የሚባል ግለሰብ ነው።ሰውየው በ2002  ኢህአዴግን   ወክሎ   የፓርላማ   ተመራጭ ነበረ።በ2009 በሰላሌ የመንግስት  ኮሙኒኬሽን  ኃላፊ ፥ አስገራፊ ፥ አሳሳሪ እንዲሁም በ2010 የተሃድሶ መናፍቃን የኦሮሚያ   ክንፍ  አስተባባሪ እና በ2011 የኢሬቻ (ዋቄፈቻ ) በአል   አዘጋጅ   ኮሚቴ   እና  አስተባባሪ  የነበረ ሰው ነው።
*አሁን ደግሞ  የጃ  War እኩይ አላማ ለማስፈጸም የኦርቶዶክስ   ተዋህዶ  ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል የኦሮሚያ   ቤተክርስቲያን   መስራች   ነኝ ብሎ መጥቷል። እነዚህን የሥልጣን ጥመኛ ካህን መሳይ ፓለቲከኞች ሁላችንም ልንታገላቸው ይገባል።
•••
ሌላው ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ በሙሉ የእነ ጃዋር ፈረሱ ቀሲስ በላይ መኮንን በጠራው በዚህ ጉባኤ ላይ ሁላችሁም ተገኝታችሁ ጥያቄ ብታቀርቡለት መልካም ነው። ከደፈረና ሃሳብ ካልቀየረ ማለት ነው።
•••
መግለጫው የሚሰጠው ለገሃር በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማእከል በሆነው በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ መሆኑንም እንዳትረሱ። ይሄን ይሄን ስታዩ የአቶ ሽመልስ አብዲሳው መንግሥት የአደራጅ ኮሚቴው ስፖንሰር መሆኑ ይገለጽልሃል።
Filed in: Amharic