>

የቋሚ ሲኖዶሱ ወቅታዊ መረጃ - እነ ኃይሌ ገብረሥላሴ ፓትርያሪኩን አታለዋል!! (ዘመድኩን በቀለ)

የቋሚ ሲኖዶሱን ወቅታዊ መረጃ እንካችሁ… 
ዘመድኩን በቀለ
* ሌላ ትኩሳት ፦
“ የኢየሩሳሌም ገዳማትን ያሠሩት አፄ ዮሐንስ ናቸው። አፄ ዮሐንስ ደግሞ ትግሬ ናቸው። እናም የኢየሩሳሌም ገዳማትን ማስተዳደር ያለበት አጋዝያኖች ነን። ትግርኛ ተናጋሪ የሆንን እኛ ኤርትራውያንና ትግራዋዮች ነን ” 
ቀውስ በላይ መኮንን መንግሥት ይሁነኝ ብሎ ከጀርባ እንደሚደግፋቸውም ታይቷል።
 የ OMN, ADDIS TV, እና የETV, በሲኖዶሱ መግለጫ ላይ ሳይገኙ በዚህ ሕገወጥ ሰው ስብሰባ ላይ መገኘትና አፍራሽ ዓላማውን ማራገብም ከሰውየው ጀርባ የመንግሥትን ፈርጣማ እጅ ለማየት ተችሏል!!!
 የትናንቱን የቋሚ ሲኖዶስ ውሎን በተመለከተና ሌሎችም ጉዳዮችን በተመለከተ እውነት እውነት የሆነውን ብቻ እየመራረጥኩ እነሆ እላለሁ፦
•••
 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዚህ ዘመን በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ መንግሥትን በተመለከተ ቋሚ ሲኖዶሱ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ስብሰባ እንዳካሄደ ነው የውስጥ መረጃዎቹ የሚያሳዩት።
•••
የትናንቱ የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ በመጀመሪያ አስቸኳይ መሆኑ፣ ተሰብሳቢዎቹም ረቡዕና አርብን ሳይጠብቁ በዕለተ ሰኞ ነበር የተሰበሰቡት። እነ ቀውስ በላይ መኮንን የቅዱስ ሲኖዶሱን ውግዘት ጥሰው በኦሮሚያ መንግሥት ይሁንቷ፣ በመንግሥታዊው የእንባ ጠባቂ ተቋም ውስጥ ተሰብስበው መደንፋትም ሁሉን አስቆጥቶም ነበር። እናም እነ ቀውስ በላይ መኮንን መንግሥት ይሁነኝ ብሎ ከጀርባ እንደሚደግፋቸውም ታይቷል።
 የ OMN, ADDIS TV, እና የETV, በሲኖዶሱ መግለጫ ላይ ሳይገኙ በዚህ ሕገወጥ ሰው ስብሰባ ላይ መገኘትና አፍራሽ ዓላማውን ማራገብም ከሰውየው ጀርባ የመንግሥትን ፈርጣማ እጅ ለማየት ተችሏል። ስለዚህ አጀንዳው ፖለቲካዊ አጀንዳና በመንግሥቱ የሚደገፍ መሆኖ ግልጽ ሆኗል።
•••
በኦሮሚያ በኦሮምኛ ቋንቋ ይቀደሳል፣ ይዘመራል፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ተተርጉመው ተሰራጭተዋል። ለኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን የሚከራከሩት ግን ያልተጠመቁት የኦሮሞ የወሃቢይ እስላሞች፣ ከቤተ ክርስቲያን የኮበለሉ የፕሮቴስታንት አማኞች መሆናቸው ሲታይ ይሄም ገራሚ ያደርገዋል። እነሱ አያስቀድሱ፣ አይቆርቡ፣ አይጠመቁ፣ አይዘምሩ፣ በሰዓታት፣ በማኅሌቱ አይሳተፉ፣ በኪዳኑ ጸሎት አይሳተፉ። መስጊድና አዳራሽ ተቀምጠው በማያውቁትና በማያዩት የሰው ጉዳይ ገብተው መፍተፍቱ ግን የተደበቀ አጀንዳ እንዳለ ገላጭ ምልክት ነው።
•••
ይሄንና ይሄን የመሰሉ ድርጊቶች ላይ ለመነጋገርም ነበር ወደ ስብሰባው አዳራሽ የተገባው። ስብሰባው ተጀመረ። ቅድሚያ በአጀንዳነት የተያዘው ግን ባለፈው ጊዜ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳምን በበጠበጡት የህወሓት ካድሬዎች ጉዳይ ላይና ካድሬ መነኮሳቱ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስን ብፁዕ አቡነ ያዕቆብን ስለደበደቡት ወሮበላ መነኮሳት ጉዳይ ነበር።
•••
ቋሚ ሲኖዶሱ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን እና የአውስትራሊያውን ሊቀጳጳስም አጣሪ አድርጎ ልኮ ነበር። እናም እነሱ አጣርተው ጨርሰው ተመልሰዋል። የማኅበረ መነኮሳቱንም፣ የምእመናኑንም ጥያቄ ይዘው መመለሳቸው ነበር የተነገረው። ሆኖም ግን ባለፈው ቅዳሜ ከስብሰባ መልስ በኢየሩሳሌም ችግር ተፈጥሮ ነበር። የችግሩም ፈጣሪዎች አስቀድመው የተደራጁ ትግርኛ ተናጋሪዎች ነበሩ።
•••
ስብሰባው አልቆ ሁሉም ወደየቤታቸው ከሄዱ በኋላ እነዚህ ትግርኛ ተናጋሪዎች ጥያቄ ስላለን ጥቂት ብትሆኑም አናግሩን ይላሉ። የቀሩት ምእመናንም መልካም ብለው ይቆያሉ። ጥያቄ የተባለው መቅረብ ጀመረ። “ የኢየሩሳሌም ገዳማትን ያሠሩት አፄ ዮሐንስ ናቸው። አፄ ዮሐንስ ደግሞ ትግሬ ናቸው። እናም የኢየሩሳሌም ገዳማትን ማስተዳደር ያለበት አጋዝያኖች ነን። ትግርኛ ተናጋሪ የሆንን እኛ ኤርትራውያንና ትግራዋዮች ነን ” ብለው ያርፋሉ። ነገሩ ከድሮ ጀምሮ በድብቅ ይሠራበት እንደነበረ ቢታወቅም እንዲህ በግልጽ አፍጥጦ ይወጣል ብሎ የጠበቀ ሰው አልነበረምና በሁሉም ዘንድ አግርሞትን ይፈጥራል።
•••
ወዲያው የቀሩት ጥቂት ኢትዮጵያውያን ጥያቄውን መቅረጽ ይጀምራሉ። በዚህን ጊዜ ጠያቂዎቹ ኤርትራውያንና ትግራዋይ ነን ያሉት ሰዎች የኢትዮጵያውያኑን በቁጥር ማነስ ሲመለከቱ ወደ ድብደባ ይገባሉ። ኢትዮጵያውያኑም የዋዛ አልነበሩምና መንጋዎቹን በበቂ ሁኔታ ይመክታሉ። የአቡነ ጳውሎስ ጋርድ የተባለ መነኩሴ ግን በጩቤ ሁሉ ለመደባደብ መመኮሩ ነው የተገለጠው። በመጨረሻም ፖሊስ ደርሶ የሁሉንም አሸበርቲ ትግርኛ ተናጋሪ ነን ባይ ማፍያዎች ፓስፖርት ነጥቆ ወደ ማረፊያ ቤት እንደወሰዳቸው ነው የተነገረው። የገዳሙ ካሜራ ማን ካሜራቸውን ለመስበርና የተቀረጸውን ፊልም ለመውሰድ የተሞከረውም ሙከራ አልተሳካም ተብሏል። ተጎጂዎቹ ግን በእስራኤል ሕግ መሠረት ክስ መስርተዋል።
•••
ቋሚ ሲኖዶሱ ይሄን ለማየት ነበር ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ የተሰበሰበው። ነገር ግን በመሃል የሶማሌ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃሬዎስ ጣልቃ በመግባት ብፁዓን አባቶችን ይቅርታ በመጠየቅ ከዚህ ይልቅ በቅድሚያ አሁን አንገብጋቢ ሁኔታ ስለሆነው ስለ እነ ቀውስ በላይ መኮንን መነጋገሩ ይሻለናል። ይሄ ይደርሳል። ቅድሚያ ስለሱ እንነጋገር ብለው ሃሳብ ያቀርባሉ። አሁን እዚህ ቦታ ስማቸውን መግለጽ የማልፈልገው አንድ አባት አጀንዳውን በተራው እንየው ለማለት ቢሞክሩም አቡነ መቃርዮስን ተከትለው አቡነ ዮሴፍም “ ከህዝቡ እየመጣ ያለው ጥያቄ አስጨናቂ ስለሆነ ቅድሚያ በእሱ ላይ እንነጋገር ተብሎ ከስምምነት ላይ ስለተደረሰ በጉዳዩ ላይ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ተወያይተዋል።
•••
በውይይቱም ወቅት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እነሱ ሲፈልጉን በየትኛውም ሰዓት ያገኙናል። በራችን ክፍት ነው። እኛ ስንፈልጋቸው ግን አናገኛቸውም። በስንት መከራ ተፈልገው ሲገኙም ዋሽተውና አጭበርብረውን ከመሄድ በቀር የፈየዱልን ነገር የለም። ቤተ ክርስቲያኗን ለማፍረስ መንግሥት ራሱ ከጀርባ ሆኖ ድጋፍ እንደሚሰጥ እያየን ነው። በሚዲያ፣ በማደራጀት፣ በፋይናንስ ጭምር ተቃዋሚዎችን እየረዳቸውና እያገዛቸው ጭምር ነው የሚታየው። ምእመናን ደግሞ የእኛን ውሳኔ ብቻ ነው እየጠበቁ ያሉት። ስንቃጠል፣ ስንታረድ የሚደርስልን መንግሥት አጥተናል። እናም አንድ ነገር መወሰን አለብን። ውሳኔዎቹም ጠንከር ያሉ መሆን አለባቸው። በማለት ተወያይተዋል።
•••
በዚህም መሠረት በቅርቡ ከጠቅላዩ ጋር ኮምጨጭ ያለ ውይይት ማካሄድ፣ ከመንግሥት ጋር ያለንን ግኑኝነት እስከሟቋረጥ ድረስ የሚደርስ አቋም መውሰድ፣ ለምእመናንም ሁኔታውን ገልጦ በያለበት በጸሎት፣ በጾም ተወስኖ ራሱንና ቤተ ክርስቲያንን ከመሰል ውድመቶች እንዲከላከል ማድርግ፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ከጥቅምቱ የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ መወያየትና አቋም መያዝ የሚል ውይይት ማድረጋቸው ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያሳየው። የቋሚ ሲኖዶሱ አጀንዳ ያዥ መምህር አብርሃም ለመመንኮስ ደብረ ሊባኖስ በመሄዱ አጀንዳ ያዡም አዲስ ስለሆነ መቸገሩንም የመረጃ ምንጮቼ ይናገራሉ።
•••
የሆነው ይሄው ነው። ስብሰባው ፍፁም ፍርሃትና አድርባይነት የሌለበት ስብሰባ እንደነበር፣ የአባቶች አቋምና የተወያዩበት አጀንዳም ከመዘበራረቁ በቀር ግሩም እንደነበር ነው የተነገረው።
★ ከስብሰባው በኋላ ምን ተወራ? 
•••
ስብሰባው ካለቀ በኋላ አባቶች መግለጫ ሊሰጡ ሲሉ በደኅንነቶች ማስፈራሪያ ደርሶባቸው መግለጫ እንዲሰጡ ተደርጓል የተባለው ፍፁም ሐሰት ነው። የተወራው የደኅንነቶች ጋጋታና አባቶችን አስፈራሩ  ተባለው ከእውነት የራቀም ነው ነው ያሉኝ የመረጃ ምንጮቼ። በግል ስልካቸው ላይ ተደውሎላቸው ማስፈራሪያ ተደርጎባቸው ከሆነም የምናውቀው የለም። ከአባቶች ግን የመጣ መረጃ የለም። ደግሞም ቢመጣም በአብዛኛው ለሰማእትነት የተዘጋጁ ናቸውም ብለውኛል የመረጃ ምንጮቼ።
••• ሁለተኛው ወሬ ኃይሌ ገብረሥላሴና የሰንሻይን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ፓትሪያርኩ ጋር ከጓደኞቹ ጋር ለሽምግልና ቤተ ክህነት ሄደዋል የተባለውም ጉዳይና፣
• መስከረም 4 አለ ስለተባለውም ሰልፍ እውነት መሆኑንና አለመሆኑን ጉዳይ፣
• የፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ በአቡነ መልከጸዴቅ በኩል የጳጉሜ 3 የኩራት ቀንን በተመለከተ ቀረበ ስለተባለው ደብዳቤና እሱን ተከትሎ ስለተነሳው ውዝግብም።
• የሁለት ሊቃነ ጳጳሳትን አደገኛ አካሄድ፣ አንድ አጭበርባሪ ደኅንነት ነኝ ባይ ሰባኪን፣ የሩፋኤል አቡና የኤልያስ ተጫነም ከአቡነ መልከጸዴቅ ጋር ስለሚሠሩት ፀያፍ ተግባር  በተመለከተ… ከፈረሱ አፍ ስቃርም ነውና የዋልኩት ትንሽ አረፍ ብዬ ከድካሜ ስበረታ የጠሩ መረጃዎች እጄ ላይ ተሰባስበው ስለገቡም እነሱኑ አጠናቅሬ በቀጣይ እጽፍላችኋለሁ።
•••
ሃሎ ጓደኞቼ ሐሰትን እንጠየፍ። በሐሰት ወሬ አንደናበር። ሐሰት ፈጣሪዋ ዲያብሎስ ነው። በሐሰት የሚደረግ አሸናፊ ትግል የለም። ያልተረጋገጠና አሳማኝ ያልሆነ የሐሰት ወሬ አንንዛ። እውነት ብቻውን በቂ ናት፣ ኃያል ናት። አሸናፊ ክንደ ብርቱ ናት። ትሪሊዮን ውሸቶች አንዲቷን እውነት አያሸንፉም።  እናም እውነትን ብቻ ይዘን እንታገል። ሌላ ድሪቶ አያስፈልግም። ሰዉንም ባልተረጋገጠ ወሬ አናደናብር። ከኑማ ጋ ዱቢን። አከተመ።
•••
★ እኔ ዘመዴ ግን ከእውነት ጋር ላልፋታ ቆርቤ የተጋባሁ ሰው ነኝ። የምጽፈው ለማዕተቤ ነው። እሾም እሸለም ብዬ አልጽፍም። ገንዘብና ሀብት ፈልጌም አልጽፍም። ለመታወቅ ለዝናም ብዬ አልጽፍም። እንደ ዜጋ ስለ ሀገሬ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ህዝቦቿ፣ እንደ አማኝ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ እጮሃለሁ፣ እሟገታለሁ። ይኸው ነው።
እነ ኃይሌ ገብረሥላሴ ፓትርያሪኩን አታለዋል!!!
•••
••• ሁለተኛው ወሬ ደግሞ ኃይሌ ገብረሥላሴና የሰንሻይን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ከመንግሥት ተልከው ሊያሸማግሉ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ጋር ከጓደኞቹ ጋር ለሽምግልና ቤተ ክህነት ሄደዋል ተብሎ የተወራውን ወሬ ይመለከታል።
•••
ይህንንም ለማጣራት ከዚሁ ከራየን ወንዝ ማዶ ቀበና ወንዝ ማዶ ወደሚገኙት የመረጃ ምንጮቼ ጋር ደውዬ አውርቼያቸዋለሁ። የሆነው እንዲህ ነው። እርግጥ ነው ኃይሌና የሰንሻይን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ቤተ ክህነት መጥተዋል። ከቅዱስ ፓትርያርኩም ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው ግን በፌስቡክ እንደተወራው ዓይነት አይደለም።
•••
እነ ኃይሌ የመጡት ባለፈው ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳንና በቤተ ክህነቱ በኩል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት ሲባል የተቋቋመው የሽምግልና ሥራ ሲሠራ የቆየው ቡድን ያ የተጀመረውና በቅዱስ ሲኖዶስም ይሁንታ አግኝቶ የነበረውና የኦዲት የማጣራት ሥራ ይሠራ የተባለው ውሳኔ ከምን እንደደረሰና ጉዳዩንም በአጭር ቋጭቶ ተልእኮአቸውንም ለመቋጨት አስበው እንደመጡ ነው የተነገረው።
•••
ቅዱስ ፓትርያርኩም ለእነ ኃይሌ እንዲህ ማለታቸውም ተሰምቷል። እርግጥ ነው ጉዳዩ ተይዟል። ነገር ግን እንደምትመለከቱት የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተና ዕለት በዕለት እየተደራረበ በሌላ ተግባር እየተወጠርን ተቸግረናል። እናም በተባለው መሠረት በተገቢው መንገድ የእናንተን ጉዳይ አልተመለከትነውም። እንግዲህ ወደፊት ስንረጋጋ እንመለከተዋለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል።
•••
በመጨረሻም እነ ኃይሌ ከቅዱስነታቸው ጋር የነበራቸውን ጉዳይ ጨርሰው ሊሰነባበቱ ሲሉ እንደ ድንገት አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችበት ችግርም አብሮ ተነስቶ ተወያይተዋል። እነ ኃይሌም በዚሁ አጋጣሚ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚገኝበት አንድ ስብሰባ በሸራተን አዲስ ስለተዘጋጀ እንዲያው ከቻሉ እርስዎ የሚመሩት የአባቶች ቡድን በቦታው ቢገኝና ከጠቅላዩ ጋር ብትወያዩ የሚል ኃሳብ አቅርበዋል።
•••
ቅዱስ ፓትርያርኩም አይ ልጆቼ ነገሩ እንዲህ በቀላል የሚሆን አይደለም። በልዩ ጽሕፈት ቤቱ በኩል ቀጠሮ አስይዘን እዚያው ጽሕፈት ቤቱ ተገኝተን እንወያያለን እንጂ ነገሮች በዚህ መልኩ ከቀጠሉ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው ብለው መልሰዋል። እነ ኃይሌም ከብዙ ማግባባት በኋላ ቅዱስ ፓትሪያርኩን አሳምነው በተባለው ስብሰባ ላይ ተገኝተው ጠቅላዩን እንዲያነጋግሩ ከስምምነት ደርሰው በሰላም ተሰነባብተዋል። በቃ ሌላ ነገር የለም። ይኸው ነው። መንግሥት ልኳቸው፣ ሊሸመግሉ የተባለውን አላየንም አልሰማንም። ይሄን እነ ኃይሌም መጠየቅ ይችላሉ።
•••
ያው እንደተባለው ቅዱስነታቸው አሁን በዚህ ሰዓት የአዲስ አበባ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም አዘጋጀ በተባለው ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። እነ ኃይሌ እንዳሉት ቅዱስነታቸው ወደ ስብሰባው የሚሄዱት እነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በወተወቷቸው መሠረት ዐቢይ አህመድን ለማግኘት ነበር። አሁን እንደደረሰኝ መረጃ ከሆነ ግን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በስብሰባው ላይ ሳይገኙ ቀርተው አሁን በቅርቡ እነ ዐቢይ ጌታን እንዲቀበል ያደረጉት ነው የሚባለትና ሙስሊም የነበረው አቶ ደመቀ መኮንን በእሱ ምትክ በስብሰባው ላይ መገኘቱ ተነግሯል። ፓትርያርኩ የሄዱት ግን እሱን ያገኙታል ተብለው ነው። ደመቀ ደግሞ ምንም የማይፈይድ ሁሌ ምክትል ወንበር ጠባቂ ግለሰብ ነው። ስለዚህ እነ ኃይሌ ፓትርያርኩን ሸውደዋል ማለት ነው።
•••
አቢቹም ቢሆን በስብሰባ ላይ ያልተገኘው ወይ ደክሞት ነው። ወይም በእስራኤሉ ተቃውሞ ደንግጦ ነው። ከአንድም ሰው ጋር ፎቶ ሳይነሳ፣ ከህዝብና ከሴቶች ጋር ሳይላፋ፣ ፎቶ አንሺውም ሥራ ፈትቶ የመጣበት ጉዞ ቢኖር የአሁኑ የኮሪያ፣ የጃፓንና የእስራኤሉ ጉዞ ነው። እናም ደክሞት ወይ ተናዶ ነው ብለን ማሰቡም ተፈጥሮአዊ ነው። አየር ላይ የከረመን ሰው መሬት ላይ እሳት ይዞ መጠበቁም በራሱ አሰልቺ ነው።
•••
የሰውም ጥርጣሬ እውነትነት አለው ማለት ነው። ሲኖዶሱ ከመንግሥት ጋር ያላትን ግኑኝነት አቆማለሁ ማለቷን ተከትሎ የልቧን ትርታም ለመለካትም ይመስላል የሄዱት ቢባል ዋሾዎች አያሰኝም። የሆነው ሆኖ ዛሬ ለሚኖረው የዜና እውጃ በስብሰባው ላይ ይኸው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተገኝታለች ብሎ የፖለቲካ ፍጆታ ለማግኘት ታስቦ ካልሆነ በቀር ነገርየው የሚያዛልቅ አይደለም። ነገን ማሰቡም መልካምም ተገቢም ነው።
•••
ይሄን በዚህ እንቋጭና ከጥቂት ቆይታ በኋላ ደግሞ ፦
• መስከረም 4 አለ ስለተባለውም ሰልፍ እውነት መሆኑንና አለመሆኑን አጣርቼ እመለሰላሁ።
• የፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ በአቡነ መልከጸዴቅ በኩል የጳጉሜ 3 የኩራት ቀንን በተመለከተ ቀረበ ስለተባለው ደብዳቤና እሱን ተከትሎ ስለተነሳው ውዝግብም።
• የሁለት ሊቃነ ጳጳሳትን አደገኛ አካሄድ፣ አንድ አጭበርባሪ ደኅንነት ነኝ ባይ ሰባኪን፣ የሩፋኤል አቡና የኤልያስ ተጫነም ከአቡነ መልከጸዴቅ ጋር ስለሚሠሩት ፀያፍ ተግባር  በተመለከተ… ከፈረሱ አፍ ስቃርም ነውና የዋልኩት ትንሽ አረፍ ብዬ ከድካሜ ስበረታ የጠሩ መረጃዎች እጄ ላይ ተሰባስበው ስለገቡም እነሱኑ አጠናቅሬ በቀጣይ እጽፍላችኋለሁ።
•••
እስከዚያው በያላችሁበት ቸር ቆዩኝ።
•••
ሻሎም !    ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ነሐሴ 28/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic