>
9:26 am - Saturday November 26, 2022

°• የዛሬው የሊቃነ ጳጳሳት ምልዓተ ጉባዔ ውሎና የተነሡ እውነቶች! (ነገረ ቅዱሳን)

 የዛሬው የሊቃነ ጳጳሳት ምልዓተ ጉባዔ ውሎና የተነሡ  እውነቶች!
ነገረ ቅዱሳን
 “እኔ መቃብር እስክገባ እፋለማለሁ!”
 
  “ኧረ ለመሆኑ እነ ሜንጫ ጃዋርንና ቀውስ በላይንስ የልብ ልብ የሚሰጠው ማነው?!?” 
አቡነ ማቲያስ
የዛሬው የዕለተ ሐሙስ አስቸኳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከ60 ሚልዮን በላይ የኦርቶዶክስ አማኝ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረ ጉባዔ ነበር። ጉባዔው ወደፊት የቤተክርስቲያናችንን የጉዞ ምዕራፍ የሚያሳምር ወሳኝ ጉባዔ ነበር። ጉባኤው ወደ ሰባት አጀንዳዎችን ቀርጾ ነበር ስብሰባውን የጀመረው። ከወትሮው በተለየ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት እና የታረዱ ካህናት፤ የፈሰሰው ደምና እንባ በሕሊናቸው እያቃጨለ በቁጭትና በመንፈሳዊ ወኔ ተሞልተው ነበር ስብሰባውን የጀመሩት።
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጸሎት አድርሰው ውዳሴ ማርያምና ጸሎተ ማርያም ተደርሶ 3:00 ላይ ስብሰባው ተጀመረ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
የእንኳን ደኅና መጣችሁና አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔው መጠራት ለምን እንዳስፈለገው አጭር ንግግር አደረጉ።
በመቀጠልም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዮሴፍ በሚያምር አንደበታቸው ስለሚወያዩባቸው አጀንዳዎችና ማብራሪያ ሰጡ። ቤተክርስቲያን ስለደረሰባት መከራና መራር ዘግናኝ ታሪክ የማይረሳው ሰቆቃ ውይይት ተጀመረ። የቅዱስ ሲኖዶሱ ድባብ አትጠይቁኝ መንፈስ ቅዱስ የወረደ እስኪመስል ድረስ ይናገራሉ ተብሎ የማይጠበቁ አባቶች ሳይቀር ያወርዱት ጀመር።
•°• ማን ምን አለ በከፊል፦
 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፦
” …አባቶቼ ቤተክርስቲያን ብቻ አይደለችም የተቃጠለችው። የ3000 ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ጭምር እንጂ። ታዲያ ታሪክ ሲቃጠል ዝም የሚል መንግሥት ምን ይሉታል? ተሸውደናል፤ ተንቀናል፤ የፈራ ይመለስ፤ እኔ መቃብር እስክገባ እፋለማለሁ”
አቡነ ሩፋኤል
” አባቶቼ የደረሰብንን ዘግናኝ ግፍ አንረሳውም። አሁን ማንንም የምንጠብቅበት ዘመን ላይ አደለንም። ሁላችን ወደ ፊት! እኔን የሚያስተዳድረኝ ሰማያዊ
መንግስት ነው።”
አቡነ ጎርጎርዮስ
“ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ብሎ የነገረን መንግሥት ቤተክርስቲያን ስትቃጠል ሀገር መቃጠሏን ረስቷል። ቅድሚያ ሰላም ማምጣት ነበር ተቀዳሚ ተግባሩ”
ከዚህ ውይይት በኋላ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የጠቅላይ ሚንስተሩ ተወካይ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገቡ። ሁሉም አበው ጋር የሚነበበው እንደ ቀድሞው ባለሥልጣን ሲመጣ እንደሚያስተናግዱት ሳይሆነ በሃዘኔታ ገፅታ ተቀበሏቸው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ቤተክርስቲያን ስለደረሰባት ችግር አብራርተው ጥያቄዎችን ማዝነብ ጀመሩ።
ከበርካታ ንግግራቸውና ጥያቄያቸው በጥቂቱ፦
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፦
“መንግስት ሥራውን እየሠራ ነው ብለን ባናምንም ትመልሱልናላችሁ ብለን ተስፋ ባናደርግም ለመሆኑ በኦሮሚያ ክልል ከክልል ዞንና እስከ ቀበሌ ድረስ
የምትሾሙት ፕሮቴስታንትን ብቻ ለምን ሆነ? ኦሮሚያ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚመሩት አካላት ማን ነው ዕድል የሠጣቸው የልብ
ልብ ማን ሠጣቸው?” ለምንድነው በኦሮሚያ ክልል የፕሮቴስታንት ተከታይ ባለሥልጣናት ብቻ እየተሾሙ ቤተክርስቲያን እንድትፈተን የሚደረገው?
ስለቤተክርስቲያንስ ስንጮህ በመንግሥት ወንበር ላይ ተቀምጠው ሳለ ድምፃችንን የማትሰሙን ለምንድነው?” በማለት የሚያስደነግጥ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳትም በክልሉ ከፍተሻና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሚደርስባቸውን እንግልት አስከትለው አቅርበዋል። “ኧረ ለመሆኑ እነ ሜንጫ ጃዋርንና ቀውስ በላይንስ የልብ ልብ የሚሰጠው ማነው?” ሲሉም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኩል ለዘረኞችና ፀረ ቤተክርስቲያን አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ ኮንነዋል። በምዕላተ ጉባዔው የታደሙ ቅዱሳን አበው  የቅዱስነታቸውን ብርታት እያዩ ፊታቸው በደስታ ተሞላ።
የኦሮምያ ክልል ም/ ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ    አብዲሳ፦
* ባፋጣኝ እናስተካክላለን ከእናንተ ከአባቶቻችን ጋር መስራት እንፈልጋለ  በክልል ደረጃ ለተፈጠረው ኃላፊነት ወስጄ በቅርቡ ከእናንተው ጋር እሰራለሁ ብሏል። የፌደራሉን ደግሞ ለጠቅላዩ እናቀርብና በጭር ጊዜ ተገናኝታችሁ ይፈታል ብለዋል። እናንተ መምጣት ሳያስፈልጋችሁ እርስዎ ይደውሉልኝ በተፈለገ ሰዓትም እመጣለሁ ብለዋል። ያም ካልሆነ አንድ ተወካይ ከእኔ ጋር የሚገናኝ አባት መድቡልኝ በማለቱ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን የሲኖዶስ ጉባኤው መድቧቸዋል።
አክለውም “የ ኦሮምያ ቤተ ክህነት” እየተባለ የሚወራው ጉዳይ ጭራሽ የማይታሰብ ጉዳይ ነው። እኛም አንፈቅድም። የማንፈቅደውም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ ስለሆነ ነው። ጉዳዩ እንደመንግሥት መቸም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም”። በተረፈ ግን በቋንቋ የማስተማር የማገልገል የመገልገሉን ጉዳይ አጠናክራችሁ ቀጥሉበት። ለምሳሌ እኔ ቤተ ሰቦቼ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ነበሩ። ይኸው በቋንቋ ያለመገልገል ጉዳይ ዛሬ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የቀላቀለን። እናም አስቡበት ብለዋል። – ገለቶማ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ !!!
ብጹአን አባቶች በየተራ እየተነሱ ዛሬ ላይ እየሆነ ያለውን ለነገ ይመጣል ብለው የሚሰጉበት ጉዳይ በስፋት አንስተዋል። ወደፊት ምን እንሥራ የችግሩ ምንጭ የሆኑ ተልካሻ አሰራራችንም ይፈተሽ ተዋሕዶን እናስቀድም የውይይቱ አካል ነበር።ጉባዔው አሁን ቀቀጥሏል ውሳኔዎች ይጠበቃሉ።
Filed in: Amharic