>

ከከሸፉ አይቀር መክሸፍ እንደ ትምህርት ሚኒስቴር!!!  (ውብሸት ሙላት)

ከከሸፉ አይቀር መክሸፍ እንደ ትምህርት ሚኒስቴር!!!
 ውብሸት ሙላት
* ሀላፊነቱ የተወሰነ የጃዋር የግል ትምህርት ሚኒስቴር – የተማሪዎችን የፈተና ውጤት ሰርዟል!!!
 የዓመቱ 1ኛ የከሸፈ መሥሪያ ቤት ትምህርት ሚኒስቴር ነው። “የጃዋር የግል ትምህርት ሚኒስቴር”  እንጂ የኢትዮጵያ መባል የለበትም። ትምህርት ሚኒስቴር ቋንቋን በሚመለከት ያወጣውን ፖሊሲ ጃዋር “በኦሮሚያ አይፈጸምም” ሲል፣ ትምህርት ሚኒስቴር “እሺ አስገዳጅ አይደለም” አለ ። ጃዋር፣ “የ12ኛ ክፍል ውጤትን ስተካክልና ነው ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚመደቡት” ሲል፣ “እሺ” ብሎ ትእዛዝ ተቀበለ። ፈጸመም። ከፌደራል የትምህርት ሚኒስቴርነት ወደ ግለሰብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትነት የተቀየረ የከሸፈ መሥሪያ ቤት ነው።
ይህው የድንቁርናው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውሳኔ በጣም የሚያናድና በተማሪዎች ልፋትና ትጋት ላይ የተሳለቀ ነው። ህክምና ለመግባት የሚለፉ ቀለሜ ተማሪዎች የሚያተኩሩት ባዮሎጂ እና ኬሚስትሪ ነው። ወደ ማህበራዊ ሳይንስ የሚያደሉት የታሪክ ትምህርትና ሲቪክስን በደንብ የሚያጠኑት ናቸው። ተማሪዎች አንዱን የትምህርት አይነት ለሌለኛው መስዋዕት እያደረጉ ነው ወደ ዩኒቨርሲቲ መሄጃቸውን መንገድ በስልትና ስትራቴጂ የሚነድፉት።
ይህ የትምህርት ሚኒስትር ውሳኔ የሺዎችን ተስፋ ያጨለመ የደንቆሮ ውሳኔ ነው። ጥፋተኛው አካል ሳይለይ፣ ግሽበት ታየባቸው የተባሉትና የተሰረዙት የትምህርት አይነቶች በምን ምክንያት መሆኑ ሳይብራራ፣ ጥፋተኞች በህግ ሳይጠየቁ፣ እንዲሁ በሁለት ቀናት ብቻ የተሰጡትን እንደማወዳደሪያ መውሰድ ኢፍትሃዊ ነው። ውጤቱን በሙሉ ሰርዞ ተማሪዎቹን ዳግም በጥብቅ ቁጥጥር በመፈተን ስህተቱን ማረም ይሻል ነበር። ግን እየተሰራ ያለው ስራ የቡድኖችን የግለሰቦችን ፍላጎት ከማሟላት የዘለለ ባለመሆኑ እንደሀገር እያዘንን የሀጂ ጃዋር ደናቁርት ድቤ ደላቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።
Filed in: Amharic