>
5:13 pm - Sunday April 19, 9418

የአቢቹ መንግሥት መልእክተኛ ዲን ዳንኤልና   የቅዱስ ፓትርያርኩ ኮምጨጭ ያለ ውይይት!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የአቢቹ መንግሥት መልእክተኛ ዲን ዳንኤልና 
 የቅዱስ ፓትርያርኩ ኮምጨጭ ያለ ውይይት!!!
                ዘመድኩን በቀለ¨
★ ለምልዓተ ጉባኤ ስኬት ሁላችንም በያለንበት እንፀልይ። 
 
★ ••• ዲያቆን ዳንኤል ከቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ እንዲገባና የመንግሥትን አቋም ለምልአተ ጉባኤው እንዲገልጽ እንዲያስረዳ፣ ተፈቅዶለታል። ከዚሁም ጋር የኦሮምያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳም ፤ የሰላም ሚንስትሯ( አልቅሶ አደሯ) ወሮ ሙፈሪያት ካሚልም እንድትገኝ አሳስበዋል
 
★ ከመቻቻል ወደ መከባበር የግድ መመጣት አለበት። መቻቻል ለባልና ለሚስት ነው። በሃይማኖት መከባበር እንጂ መቻቻል ብሎ ነገር የለም። ሃላስ። 
•••
ጠዋት ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቢሮ በመደወል ከቅዱስነታቸው ጋር ረዘም ላሉ ደቂቃዎች መወያየታቸው ተነግሯል። አቢቹ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ ተፈጠረ ስለተባለው ነገር እንደሚያውቁት ሀገር ውስጥ ስላልነበርኩ ምንም እንዳልሰማና አሁን እዚህ ከመጣ በኋላ እንደሰማ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌለውም ለቅዱስነታቸው ለማስረዳት ምክሯልም ነው የተባለው።
•••
ቅዱስነታቸውም ከወትሮው ጠንከር ባለ ቃል ጠቅላዩን ሞግተውታልም ነው የተባለው። የለም የለም እንደዚያ አይደለም “ አንተ ባትኖርስ? አንተ ስትሄድ ሀገሪቱን ሌሎች ምክትሎች አይደሉ እንዴ የሚመሯት? እንዲህማ አይባልም። ለማንኛውም ቤተ ክርስቲያኒቱ በደሏ በዝቷል። ከአቅሟ በላይም ሆኗል። ሁሉን እንቻል ግድየለም ያልፋል ብለን የሞቱ የተገደሉብንን እየቀበርን፣ የተቃጠሉብንን አብያተ ክርስቲያናት መልሰን ለማነጽ መከራችንን በምንበላባት በዚህ ሰዓት ጭራሽ በመዋቅሯ ውስጥ የሌሉ፣ በእናንተ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ግለሰቦች ተደራጅተው ከሕግ አግባብ ውጪ እንዲህ በአደባባይ ሲደነፉብን ምን እንድንል ነው እንዴ የሚጠበቀው? በጭራሽ ይሄ ከእኛ አቅም በላይ ነው። አሁን ህዝቡም አባቶችም ትእግስታቸው ስላለቀ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተናል። እናም ሁኔታው በዚህ ላይ ነው ያለው ብለውታል ተብሏል።
•••
ጠቅላዩም በሁኔታው ማዘኑን ገልጦ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምንም አትሆንም። አትፈርስም። ሁኔታውም ይስተካከላል። ለመፍትሄውም እንደሚሠራ፣ በመግለጥ ለጉዳዩ በቂ መረጃ ስለ ሌለኝ ጉዳዩን በማጣራት አስፈላጊውን መፍትሄ እሰጣለሁ ብሏልም ተብሏል።
•••
ቅዱስነታቸውም የለም የለም ሰዎቹ እኮ በመንግሥት ድጋፍ የሚሰጣቸው ናቸው። በእናንተ ቢሮ እኮ ነው የሚንቀሳቀሱት። የአንተ ባለ ሥልጣናትም እዚህ ድረስ መጥተው ዋሽተውን ነው የሄዱት። ( አልቃሻዋና በየሄደችበት ተነፋራቂዋ እስላሟ ሙፈርያት ካሚልና ሞዴላ ሞዴሉ ጴንጤው ታከለ ኡማን ማለታቸው ነው። በነገራችን ላይ ለዚህ ሁሉ ጥፋት ሙፈሪያትና ታከለ በደንብ እጃቸው አለበት። ምክንያቱም። ራሷ ሙፈሪያት የሲኖዶሱ አባላት ባሉበት ስለ ቀውስ በላይ በተነገራት ጊዜ፣ “እሱ ሌባ ነው። ክህነቱን ያዙትና ክሰሱት። እኛ አስፈላጊውን እርምጃ እንወስድበታለን ” ካለቻቸው በኋላ ነው ቃሏን አጥፋ ቀውስ በላይ መኮንን እንዲንበጫበጭብን ያደረገችው። ታከለ ኡማም 10 ሚልዮን ብር በህጻናት ደብተር ስም ለጫማና ሱፉ መዘነጫ ሊለምን በመጣ ጊዜ ስለ ጉዳዩ ተነስቶለት “…በፍጹም እኔ ጉዳዩን አላውቅም አሁን ለሽመልስ አብዲሳ ደውዬለት ጉዳዩ እንዲቆም አደርጋለሁ …..” ብሎ ከወጣ በኋላ እንኳን ሊያስቆም ጭራሽ ጴንጤዋ እናትዓለም መለስና እስላሙ አቶ ኢብራሂም በሚመሩትን የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃንን ቤተ ክርስቲያኒቱ ያወገዘችውን ሕገወጥ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲቀርጹ ነው የላከው። በእሱ ቤት ሽማግሌዎች ናቸው አጃጅዬያቸዋለሁ፣ ሸውጄያቸዋለሁ ማለቱ ነው)  እናም አሉ ቅዱስነታቸው አሁን ውሳኔው የምልአተ ጉባኤው ነው። ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ወጥቷል። ሲኖዶሱ የሚወስነውን መስማት ብቻ ነው ብለውታል ነው የተባለው።
•••
በመጨረሻም ጠቅላዩ ቅዱስነታቸውን አንድ ነገር ብቻ እንደለመናቸውም ተሰምቷል። ይኸውም ካለው ሁኔታ የተነሳ እሱ በዚህ ስሜት በነገው የአባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ባልችልም ዲን ዳንኤልን ልላከውና የእኔንና የመንግሥቴን ሃሳብ ለእናንተ፣ የእናንተን ሃሳብ ደግሞ ለእኛ ይንገረንና ወደ መፍትሄው በአስቸኳይ እንድንገባ ይፍቀዱልን ብለውታል። ቅዱስነታቸውም መልካም ይሄንንም ለማድረግ ብቻዬን መወሰን አልችልምም እናም ከሰዓት በኋላ ላከው ብለውታል። ለዚሁ ብሎ ነው ዲን ዳንኤል ትናንት ከሰዓት በኋላ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተገኘው የተባለው።
•••
በከሰዓቱ ጉባኤ ላይ የተወያዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ዲን ዳንኤል ክብረት ናቸው ተብሏል። የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ለጊዜው በሥፍራው አልነበሩም ነው የተባለው።
•••
ውይይቱም መልካም ነበር ተብሏል። በተለይ ብፁዕ አቡነ ያሬድ መረር ያለ ቃል መናገራቸው የነገው ጉባኤ ድባብ ምን ሊመስል እንደሚችል ጠቋሚ ነውም ተብሏል። በመጨረሻም ዲያቆን ዳንኤል ከቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ እንዲገባ፣ ለዋና ጸሐፊው እንዲነገራቸው። የመንግሥትን አቋም ለምልአተ ጉባኤው እንዲገልጽ እንዲያስረዳ፣ ተፈቅዶለታል ተብሏልም። ከዚሁም ጋር አቶ ሽመልስ አብዲሳም እንዲገኝ። የሰላም ሚንስትሯ አልቅሶ አደሯ ወሮ ሙፈሪያት ካሚልም እንድትገኝ አሳስበዋል።
ዲን ዳንኤል ወሮ ሙፈሪያት የምትገኝ አይመስለኝም። ነገ ስብሰባ አለባት ብሎ የነበረ ቢሆንም ስማ ዳንኤል እኛ ነገ የምንነጋገረው በሀገሪቱ ውስጥ ስላለው አጠቃላይ ችግር ነው። እንጂ ስለ እነ በላይ መኮንን ብቻ አይደለም። ስለዚህ ሙፈሪያት የግድ መገኘት አለባት፣ ይሄ ቁርጥ ነው ብለው አስረግጠው እንደነገሩት ነው የተሰማው። ዲን ዳንኤልም እሺ ስብሰባውን ሰርዛም ቢሆን እንድትገኝ እነግራለሁ ብሎ ሄዷል።
★ አሁን በደረሰኝ መረጃ መሠረት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንቱ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በስብሰባው ላይ ለመገኘቱ ማረጋገጫ እንደሰጠ ተሰምቷል። የሙፈሪያት ግን እስከአሁን መልስ የለም። አፍራ እንደሚሆን እገምታለሁ። ከመጣች ግን ጉባኤው በፕሮቴስታንትና በእስላሞች የተሞላው በዐብይ መንግሥትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቃውንት መካከል እንደሚሆን ነው የሚሰማኝ። አቶ ሽመልስ አብዲሳም ፕሮቴስታንት እንደሆነ ልብ ይሏል። ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያኒቱ የተናቀችው። የጃዋር ቡችሎች የፈነጩባት። ነጩ እውነት ይኸው ነው።
•••
ብፁዓን አባቶች ከየ አህጉረ ስብከታቸው እየተመሙ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው ተብሏል። ከእነ ቀውስ በላይ መኮንን ጀርባ ያሉና ራሳቸውን ፓትሪያርክ ጭምር አድርገው ተመራርጠው ጨርሰው የነበሩት የኦሮምኛ ተናጋሪ ሊቃነ ጳጳሳትም በጉባኤው ላይ ይምጡ አይምጡ እስከአሁን የታወቀ ነገር የለም። ይህ ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትንሣኤዋን ወይም ውድቀቷን የሚወስን ይሆናል ባይም ነኝ።
•••
የነገውን ጉባኤ ልክ እንደ ቁስጥንጥንያው ጉባኤ ነው የምቆጥረው። እንደ ኒቂያውም ጉባኤ ጭምር። ጉባኤውን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይምራው። ይቆጣጠረውም። እናት ቤተ ክርስቲያን በመሰረተችው ሀገር በማንም መንገደኛና ወጠጤ ጫታም የመስቀል ደመራ መደመሪያ ማክበሪያ ሥፍራዋን፣ የጥምቀት ከተራ የበዓል ማክበሪያ ቦታዋን፣ የመቃብር ስፍራዋን ተነጥቃ እጆቿን አጣምራ የማይታይበት ዘመን ማብቃቱን አስረግጠው መወሰን አለባቸው።
•••
እስከ አሁን እየተቃጠልን ቆይተናል፣ እየነደድን፣ እየከሰልን አመድም ጭምር አድርገውናል። ታርደናል፣ ተገድለናል። ነገር ግን አንድም የተጠየቀ አካል የለም። ገዳዮቹ ጴንጤ ወይም እስላም ስለሆኑ መንግሥቱም የእስላምና የጴንጤ መንግሥት ነው ብለው ስለሚያስቡ “ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ” የሆኑ ግለሰቦችና ባለሥልጣናት በሙሉ ለፍርድ ሳይቀርቡ ተዝናንተው ይኖራሉ። አብዲ ኢሌ 10 አብያተ ክርስቲያናት አቃጥሏል ብሎ አጯጩሆ ያለው የዐብይ መንግሥት አቶ ሚልዮን በሲዳማ 7 አብያተ ክርስቲያናት ሲያቃጥል የተቀጣው ቅጣት ከደቡብ ክልል ፕሬዘዳንትነት ወርዶ አዲስ አበባ በግዞት ሚንስትር ነው የተደረገው። ለምን ቢባል ጴንጤ ስለሆነ። ነጭ ነጩ እውነት ይሄው ነው።
•••
ምእመናን በያለንበት እንጸልይ፣ ሁከት ግርግር የባህሪ ገንዘባችን አይደለም። የአባቶቻችንን ድምጽ እንስማለን። የሚያዙንን እንፈጽማለን። እኛ ጃዋር አባ ሜንጫ በምርቃና  የሚነዳን መንጋ አይደለንም። የሕግና የሥርዓት ባለቤቶች ነን። ብዙ እንታገሳለን። ሲበዛ ግን ለምን ማለታችን በራሱ ሀገር ይነቀንቃል። አሁን የታየውም እሱው ነው። ተዋሕዶ ሀገር ናት። ለጣሊያን ያልተንበረከከች ለጃዋር ቡችሎች የምትንበረከክ አይደለችም። እኛ የምንገለው ጠላት የለንም። የምንሞትለትም ብሔር የለንም። የምንሞትለት ሀገርና ሃይማኖት ግን አለን። ሁሉም ይሄን ሊያውቁት ይገባል።
•••
በሲኖዶሱ ስብሰባ መሃል እገኛለሁ። እኔም ከተሰብሳቢዎቹ መሃል አንደኛው ነኝ። እነ አቡነ ቀውስጦስን፣ እስጢፋኖስን፣ አቡነ ሳሙኤልን፣ አቡነ አብርሃምን፣ እስካይ ናፍቄአለሁ፣ እነ አቡነ መቃርዮስ ዘሱማሌ፣ እነ አቡነ አትናትዮስ ዘወሎ፣ አቡነ እንድርያስን እስክሰማ ናፍቄያለሁ። አቡነ ኤልያስ የአውሮጳው፣ አቡነ ኤልያስ የአርባምንጩን እስክሰማ ጓጉቻለሁ። እነ አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ሄኖክን መስማት ጓጉቻለሁ። ማን ምን አይነት አቋም እንዳለው፣ ማን ምን እንዳለ ጭምር ይፋ አወጣለሁ።
 በጉባኤ የምሥራቅ ሸዋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ፣ የሰሜን ሸዋው የደብረ ብርሃኑ ብፁዕ አቡነ ቄሌሜንጦስ፣ የጉራጌውና የአዲስ አበባው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ፣ የሚኒሶታው ብፁዕ አቡነ ኤውስታጤዎስ፣ የአዊ ሀገረ ስብከቱ ብፁዕ አቡነ ቶማስ እና የምዕራብ ሸዋው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የሚሉትን በትኩረት እከታተለዋለሁ። ነገ አቡነ ጎርጎሬዎስና አቡነ መልከጸዴቅ እንደለመዳችሁት አሞናል ብላችሁ ብትቀሩ የአባትና ልጅነታችን ነገር ያበቃለታል። ተናግሬአለሁ።
•••
ሚሊዮኖች ዐይንና ጆሮአችን አራት ኪሎ ቅድስተ ማርያም አራት ኪሎ ነው። ወዳጅም ጠላት ሰይጣንም ወደ አራት ኪሎ ነው። የእነ ቀውስ በላይ ጉዳይ ግን ያበቃለታል። መራታ ሁላ። አከተመ።
በተረፈ ምስጋናም የማቀርብላቸው ወንድም እህቶችም አሉኝ። ቀላል ቁጥር የሌላቸውን ሙስሊም ወንድሞችና እህቶችንም በፌስቡክ ላይ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲሟገቱ አይቻለሁ። ይህን በማድረጋቸውም በወሃቢያ አክራሪ እስላሞች ሲሰደቡም አይቼ ኮርቼባቸዋለሁ። በተለይ ሙክታር ኡስማኖቪች የሚባል ልጅ እንባዬ ነው የመጣው። የፕሮቴስታን እምነት ተከታዩ ተስፋዬ ሰሙ ንጉሥ ተስፍሽ አፕም እንዲሁ ፍካሬ ዘጻድቃንን በቃሉ እያስሄደ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ቆሞ ሲከራከር አይቻለሁ። ፓስተር ኃይሉ መኮንን የተባለም ፓስተር እየሰደቡት በቀጥታ የቪድዮ ንግግር ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሲሞግት አይቻዋለሁ። የአዲስ ጉዳዩ ጋዜጠኛ ፕሮቴስታንቱ ታምራት ነገራም በይፋ በፌስ ቡክ ፔጁ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጎን የምንሰለፍበት ጊዜ እየመጣ ነው ብሎ አጋርነቱን ገልጿል።
•••
የእስልምና ምክርቤት ድራሹ የለም። የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንዲያውም የተበሳጩ ይመስል ዝም ብለዋል። ካቶሊክማ በሀገሩ ያለች አትመስልም። የየኔታ ዓለማየሁ እሸቱ ወዳጆች እነ ኡስታዝ፣ አቡበከር፣ እነ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ለፉገራ ያህል እንኳ ድምጻቸውን አላሰሙም። ይኼው ነው እውነቱ።
•••
ማስታወሻ | ~ መስከረም 4 ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ ሰልፍም አስተባባሪ ኮሚቴዎቹን አግኝቼያለሁ። እናም ነገ ጥርት ያለውን አቋማቸውን ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
•••
አቦ ያ ኦቦሌሶ!  ከነሙ ጋ ዱቢን። 
•••
ሻሎም !   ሰላም !  
ነሐሴ 29/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic