>

*የትግራይ ህዝብ ትግል እና መስዋእትነት፤ ለእኛ ለኦሮሞ ህዝቦች ከፍለን የማንችለው ውለታ ነው!!! (ኦቦ በቀለ ገርባ) 

የትግራይ ህዝብ ትግል እና መስዋእትነት፤ ለእኛ ለኦሮሞ ህዝቦች ከፍለን የማንችለው ውለታ ነው!!!
ኦቦ በቀለ ገርባ 
* ጊዜና ፀሓይ የወጣላቸው መስሏቸው፤ የትግራይ ህዝብ በትግሉ ኣሽቀንጥሮ ያሸነፋቸው ሓይሎች፤ ከቶውንም እንዲበቀሉት አንፈቅድላቸውም። 
* …እኛን ሲያስር እና ሲከታተለን የነበረው የደህንነት ሰው እኮ ኦሮምኛ የተለማመዱ የትግራይ ሰዎች ኣልነበሩም። የኦፒዲኦ ደህንነቶች ናቸው
በአዳማው ስብሰባ ከተናገሩት
“… 1ኛ ይቅርታ ማድረግ ካለብን እኛ ነን ይቅር የምንለው። አሁን ላለውም ሆነ ለነባሩ የኢሕአዴግ አመራር፣ ምክንያቱም ፍዳችንን ስናይ የነበርነው እኛ በመሆናችን። ወደ አንድ አካል ብቻ ያነጣጠረ የተጠያቂነት መንፈስ ፈፅሞ የማንቀበለው ነው።
እኛን ሲያስር እና ሲከታተለን የነበረው የደህንነት ሰው እኮ ኦሮምኛ የተለማመዱ የትግራይ ሰዎች ኣልነበሩም። የኦፒዲኦ ደህንነቶች ናቸው።  ስለዚህ መጠየቅ ካለበት፤ እንደ መንግስትና እንደ ኢሕአዴግ እንጂ፤ ወደ አንድ ፖርቲ ያነጣጠረ ማድረጉ ከጥፋት ከመሸሽ በዘለለ ፍፁም ቅቡልነት የለውም።
“… 2ኛ እኛ እንደ ኦሮሞ ራሳችን በራሳችን እንድንተዳደር ዋጋ የከፈለልን፤ እንደ ህዝብ ትግራዋይ እንደ ድርጅት ደሞ ወያኔ ነው። ይህ ወደድንም ጠላንም የተሰራ ታሪክ ስለሆነ ልንቀይረውም አንችልም። ይህ ማለት የኦሮሞ ትግል ዋጋ አልነበረውም ማለት ሳይሆን፤ እንደ ኦሮሞ የከፈልነው ውድ መስዋእትነት እንዳለ ሁኖ፤ የነዚህ የትግራይ ልጆች መስዋእትነት ግን ለትግላችን ግብ እና ለጥያቄኣችን መልስ የህይወት የኣካል የንብረት ዋጋ አበርክቶልናል።
“… ለዚህም ነው በራሳችን የምንተዳደረው፤ ለዚህም ነው በቋንቋችን የምንዳኘው የምንማረው፤ ለዚህም ነው እንደ ኦሮሚያ በክልልነት በፌደራል ስርዓት የምንተዳደረው፤ ለዚህም ነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ብለን ራሳችን በራሳችን የምንተዳደረው፡፡ ለዚህም ነው የፌደራሊስት ስርዓት ከሚያምኑ እና ከሚከተሉት ሓይሎች ጋር በተደጋጋሚ እየታየን ያለነው።
“… ስለዚ የትግራይ ህዝብ ትግል እና መስዋእትነት፤ ለእኛ ለኦሮሞ ህዝቦች ከፍለን የማንችለው ውለታ ነው። ለዚህም ነው የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ በየትኛውም ዘመን የኦሮሞ ጠላት አይደሉም ኣይሆኑምም፤ የስትራተጂ ወዳጃችን ናቸው የምንለው።
“… ከዚህ ጎን ለጎን ጊዜና ፀሓይ የወጣላቸው መስሏቸው፤ የትግራይ ህዝብ በትግሉ ኣሽቀንጥሮ ያሸነፋቸው ሓይሎች፤ ይህ ባለውለታችን የሆነውን ህዝብ፤ ከቶውንም እንዲበቀሉት አንፈቅድላቸውም። ቢሆን ቢሆን ትግራዋይ የሚንበረከክ ህዝብም ኣይደለም። ቢያንስ ቢያንስ ግን ስለከፈሉልን ዋጋ ስንል ከጎናቸው መሰለፍ ኣለብን። ይህንን እምለው የትምክህት ሃይሎች ስለ ትግራይ ህዝብ የሚያቀነቅኑትንና የሚፈፁሙትን ሴራ ማለቴ ነው።
“… ስለዚህ ከውጭም ከውስጥም ስለዚህ ህዝብ ደህንነት ጉዳይ እንደ መርህ እና እንደ ዓለማ ይዘን መንቀሳቀስ ይኖርብናል። በዚህ አማካኝነት ደግሞ የፌደራል ስርዓታችንን እያጠናከርን መሄድ ይኖርብናል ብየ ኣምናለሁ…”
ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ በአዳማ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች የትብብር መድረክ ላይ የተናገሩት
ምንጭ – ካሳ ሃይለማርያም
Filed in: Amharic