>

የቤተ መንግሥቱ ስብሰባ አልቆ የቤተ ክህነቱ ተጀምሯል!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

የቤተ መንግሥቱ ስብሰባ አልቆ 
   የቤተ ክህነቱ ተጀምሯል!!!
 ዘመድኩን በቀለ
ያለ ቀጠሮ የመጣው ታከለ ኡማ በቤተ ክህነት ግቢ መኪና ውስጥ ተቀምጦ ዋለ።
 
• 10 ሚልዮን ብሩን ካልሰጣችሁኝ አልወጣም!! አስመስሎበታል። [ የጉድ ዘመን ] 
 
አቡነ መልከጼዴቅ በገጠር ከሚቃጠሉት ሌላ ንዋያተ ቅዱሳትና ጧፍ እጣን ዘቢብ አጥተው የተዘጉ እልፍ አብያተ ክርስቲያናት እያሉ ለጠገበ ጎረምሳ 10 ሚልየን ብር ካልተሰጠ ሞቼ እገኛለሁ ማለታቸው ምስጢሩ ምን ይሆን??? 
–‘-
የቤተ መንግሥቱ ስብሰባ በሰላምም በኢሰላምም መልኩ ተጠናቅቋል። አሁን ደግሞ ቀውስ በላይን መኮንን ለማናገር በቤተ ክህነት ጉባኤ ተዘርግቷል። ዝርዝሩን ለመዘርዘር ጊዜ ይፈልጋልና በቀጣይ እመለስበታለሁ። በዚህ ምክንያት የተነሳ ለዛሬ ይሰጣል ተብሎ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለነገ ጠዋት መተላለፉ ተነግሯል። አሁን ቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ነው።
•••
 
አስገራሚው ዜና የሚከተለው ነው
በአቡነ መልከጼዴቅ ወትዋችነት ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ አሁን ቤተ ክህነቱ ግቢ ይገኛል። አቡኑ መልከጼዴቅ በቀደም ዕለት ቅዱስ ፓትሪያርኩ እኔ አልፈርምም ያሉትን 10 ሚልዮን ብር በራሳቸው ሥልጣን ከካዝና አውጥተው ለመስጠት በመወሰናቸው ዛሬ ከቤተ መንግሥቱ ስብሰባ በኋላ ከንቲባውን ጠርተው ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ለማገናኘት ያደረጉት ሙከራም በቅዱስ ፓትርያርኩ እምቢተኝነት ያለመሳካቱ ነው የተነገረው። “ እኔ ከታከለ ኡማ ጋር የያዝኩት ቀጠሮ ስለሌለን አላናግርውም” በማለታቸው ታከለ ኡማ እስከ አሁኗ ሠዓት ድረስ እዚያው ቤተ ክህነቱ ግቢ ውስጥ ከመኪናው ሳይወርድ ለመቀመጥ ተገድዷል
•••
ይሄን 10 ሚልየኑን ብር ጳጳሱ ለመስጠት እንዲህ መጣደፋቸው፣ ታከለ ኡማም ቼኩን ለመቀበል ሥራ ፈትቶ መኪና ውስጥ እንደተራ ሰው ካሜራ ማን ወድሮ መቀመጡ ሀገሪቷ ምን ያህል በድኩሟኖች እጅ እንደወደቀች ማሳያ ነው ይላሉ የመረጃ ምንጮቼ። ተመልከቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ገንዘቡን ባይፈርሙም እነ አቡነ መልከጸዴቅ ከሃገረ ስብከቱ ካዝና አውጥተው ለታኬ አራዳ ሊሰጡት መወሰናቸው የሚጠቁመን ነገር አለ። ሥርዓት የሚባል ነገር መጥፋቱን እንመለከታለን።
•••
በፓትርያርኩ ቢሮ ቼኩን እንደማይቀበል ያወቀው ታከለ ኡማ ከተቻለ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ይቀበል ዘንድ አቡኑ የሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ አቡነ ዮሴፍን ለማናገር ላይ እታች እያሉ መሆኑ ነው የተነገረው። ስንት ፈርቅ ይዘውበት ይሆን እንዲህ የተራወጡት? የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ተጀምሮም ታከለ ኡማ አልወጣም ብሎ ቁጭ ማለቱን ያዩ አባቶች ግራ መጋባታቸውን ነው የሚናገሩት። ታከለ ቅዱስ ፓትርያርኩ አንድ ጊዜ ቤሮ ውስጥ መጥተው ቼኩን ሰጥተውኝ ቢመለሱ ምን አለበት ቢልም ቅዱስነታቸው ግን ከፈለጋችሁ እዚሁ ይግባና እናንተ ፊት ልስጠው እንጂ እኔ በቢሮዬ አላናግረውም። ቀጠሮም የለኝም ብለዋል።
•••
በመጨረሻም የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን በመውቀስ ታከለ እንዲገባና በጉባኤው ፊት ብሩን እንዲቀበል። በዚያውም የምንጠይቀው ነገር ይኖረናል በመባሉ የአዲስ ቲቪ ካሜራውን ወድሮ ወደ ሲኖዶሱ ስብሰባ መግባቱን የመረጃ ምንጮቼ ከሥፍራው ጠቁመዋል። ወይ የቤተ ክርስቲያን ብር። እንዲህ የማንም መጫወቻ ሆኖ ይቅር? በገጠር ከሚቃጠሉት ሌላ ንዋያተ ቅዱሳትና ጧፍ እጣን ዘቢብ አጥተው የተዘጉ እልፍ አብያተ ክርስቲያናት እያሉ ለጠገበ ጎረምሳ 10 ሚልየን ብር ለመስጠት መላላጡ ይገርማል።
•••
 ታከለ ኡማም ስለእነ በላይ መኮንን እንቅስቃሴና መስከረም 4 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበራት ኅብረት ስለጠሩትን ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ ሲኖዶሱ ጉዳዩን ያውቀው ይችል እንደሆን መጠየቅም እንደሚፈልግ ነው ነው የተነገረው።
•••
እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት ግን በትናንትናው ዕለት የማኅበራት ኅብረቱና፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም በዐውደ ምህረት የሚያገለግሉ መምህራን ከከንቲባው ጋር ሲወያዩ መማምሸታቸውን ከውይይቱ ተሳታፊዎች የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። ከንቲባው እንዳሉት ከሆነ እፈቅዳለሁም አልልልም፣ አልፈቅድምም አልልም። ምክንያቱም በደሉ ግልጽ ነው። ለመፍቀድ ደግሞ እቸገራለሁ ማለታቸው ተነግሯል።
•••
በመጨረሻም እስከዛሬ ስወቅሰው የኖርኩት መምህር ባህሩ ለክቡር ከንቲባው ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል እኛ መስከረም 4 በሰላማዊ ሰልፍ ለዓለም ህዝብ ለመንግሥትና ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳወቃችንን አንተውም። የእናንተ ሥራ ለሰልፉ ጥበቃ ማድረግ ብቻ ነው ማለቱንና ሁሉም በበመምህር ባህሩ ሃሳብ ተስማምተው መውጣታቸው ተነግሯል።
• ጥርት ያለውን መረጃቸውን ኮሚቴዎቹ እንዳደረሱኝ አቀርብላችኋለሁ።
•••
ሻሎም !   ሰላም ! 
ጳጉሜ 1/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic