>
2:13 am - Saturday November 27, 2021

ታማሚ!! እኔ ስለ ራሴ!!! (ዳንኤል ገዛህኝ ወንድሙ)

ታማሚ!! እኔ ስለ ራሴ!!!
ዳንኤል ገዛህኝ ወንድሙ
እንዲህ ባለ ሰፊ መድረክ ላይ ስለ ራስ መጻፍ ትንሽ ይከብዳል። ስለ እኔ ሰዎች ይበሉ እንጂ ስለራሴ እኔው ማለቴ ምቾት አይሰጠኝም ። ይሁን እና ይህን ብዬ በዝምታ ከመብሰልሰል …በይሉኝታ  በውስጥ ታምቆ እንደ   ቁዋሳ ከሚለበልብ የሀሳብ እሳት… ነገሮች ብልጭ ባሉ ቁጥር ከመብከንከን ይልቅ የመጣው ይምጣ ብዬ መጻፍን መርጫለሁ። የሆነው ሆኖ ለወራት የቆየሁበት. ያለሁበት አስቸጋሪ የጤና እክል እንደዚህ እንድወላዳ የሚያደርግ ባይሆንም በድፍረት ልሂድበት።
በሆስፒታል የነበረኝ ቆይታ እስከ ሞት አፋፍ የዘለቀ ነበረ። ICU በከፍተኛ ክትትል ስር የሚገኙ ህሙማን የሚተኙበት ከጤና ባለሞያዎች በቀር ህሙማን ከማንም ጋር የማይገናኙበት ነው በተለምዶ ኮማ የምንለው ቆይታዬ በዚያ ነበር። በተለይም የምተነፍሰው አየር እጥረት Shortage of Breathing በከፍተኛ ሁኔታ የተሰቃየሁበት የተፈጥሮ አየር ማጣት በቃላት ሊገለጥ የማይችል ነበር። የመጀመርያዎቹ በተለይ ከኔ ጋር ከሰነበተው የ Deabetics እና Blood Pressure ህመም ይልቅ ሆስፒታል ለመኝታ የዶለኝ የሁለቱ ኩላሊቶቼ መጎዳት ደረጃ ከፍ ማለት ከአካላዊ የሰውነት ጉዳት ይልቅ የውስጥ የህሊና ቁስል ቀላል አልነበረም። በተለይም ከሁለቱም ኩላሊት ስራ ማቆም Kidney Fail Stage 4, Chronic Kidney Diseases ባሻገር ከጎኔ ባጣሁዋቸው ነገሮች ምክንያት ይብሱኑ ለከባድ ህመም
Grievance ብሶት  የዳረገኝ ጉዳይ አንዱ ነው። ስጠብቃቸው ባጣሁዋቸው ሊያዩኝ ሲገባ እይታ በነፈጉኝ invissiblity pain ያለመታየት ያለመታወስ ስቃይ ነው። ይህን ህመሜን አብዝቼ የማነሳው ለእውቅና ለአድናቆት አይደለም ። የህመሙ ባህሪይ በተለይ ከicu ስነቃ የማን አስታወሰኝ…የማን ጎበኘኝ ጉጉት በውስጤ  አሳድሮዋል። ብሌላ በኩል የኩላሊቶቼን ስራ በከፊል የሚሸፍኑልኝን መድሀኒቶች አግኝቼ ስቃዩን በተወሰነ ደረጃ ሲቀንስልኝ ለድጋፍ ሰዎችን ማማተሬን ቀጠልኩ።
በቅድሚያ ምንግዜም ለረጅም ጊዜ ከጎኔ የማላጣቸው ንስሮቹ የነጻው ፕሬስ ጉዋደኞቼ ዋናዎቹ ናቸው። በተለይ ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየሁ ያደረገውን ለመናገር በእውነት ቦታ አይበቃም። አርጋው አሽኔ ተስፋህ ልብ ይሞላል። አቤ ቶኪቻው ቅነትህ ወሰን የለውም። ዳዊት ሰለሞን ትህትና የተሞላው ጥየቃህ ልብ ያሞቃል። አርአያ ተስፋማርያም እውነታዎቼን አጉልተህ ትኩረት እንድናስብ የወገኖቼን ድጋፍ እንዳገኝ አግዘኽኛል፣ቶማስ አያሌው፣ቴዎድሮስ ዳኜ፣ ሲሳይ አጌና፣ዮሀንስ አበበ ሞረሽ፣አዝመራዬ ዳንኤል ልቤን ነክታችሁታል የአትላንታው ቴዎድሮስ ታደሰ ከልብ አመሰግናለሁ።በማስመሰል ሳይሆን በተግባር መልካምነታችሁን አሳይታችሁኛል። እርግጥ ነው ማመስገን ካለብኝ በርካታዎችን መጥቀስ ይቻላል ቦታው አይበቃም እንጅ።
በዝምታ ብዙ ግዜ ውስጥ ይጎዳል። አንዳንዶች ስልክ ላይ የማይታወቁ setup በማዘጋጀት በማይታወቁ ሰዎች ፕራንክ የሚመስል ተግባር በመፈጸም፣ ሌሎቹ ጎፊንድ ማለት በጣም የተለየ ፕሮሰስ ያለው አስቸጋሪ ውጣ ውረድ ያለው መሆኑን ብቻ አይደለም በእነ እክሌ ስም ቢከፈት ፣ ሌሎቹ ጎፈንድ  ብቻ ይከፈት እንጅ …ወዘተርፈ በመናገር በሰው ቁስል እንጨት የሚሰዱ የእከክልኝ ልከክልህ አላማ አስፈጻሚዎች በህመምተኛ ግለሰብ ደካማ ጎን psychology በመግባት የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈጸም በታዋቂ ሰዎች ስም ርካሽ ተግባር ለማከናወን የሚዳዳቸው አሉ። በኦሮሞ ባህል አንድ የተለመደ አባባል እለ;”ከን ሶዳተን ዱአ…ከን ኢን ኦሌስ ዱአ ” የሚፈራ ሞት ነው የማይቀርም ሞት ነው. ። ስለዚህ በመታመሜ የጎፈንድ support በመጠየቄ የታካሄደብኝን ድራማ አሳውቃለሁ። ለሞት ብቃረብ እንኩዋን የእለት ተእለት ንግግራችንን ለሚቀዳው ስልክ አንድሮይድ ምስጋና ይድረሰው እና አጋልጨ አልፋለሁ።በተረፈ ሳልድን ለመውተርተር ያለሀኪም ፈቃድ ከህክምና ስፍራ በመውጣት በሁለት እግሮች ገብቼ በስድስት እግር መውጣቴ በድምጽ ከሰዎች ጋር መነጋገር የኩላሊት patient’s መሆኔ ቀርቶ ጎፈንዱ ወደ ኢንቨስትመንት ሀሳብ የተቀየረባቸው የርካሽ አላማ ተግባር ባለቤቶች በእኔ ላይ የከፈቱት ዘመቻ እንደማይሳካ እርግጠኛ ነኝ።ለበለጠ መረጃ የህክምና ክትትል የዶክተር መረጃ በተዘዋዋሪ መንገድ ጠይቃችሁኝ የደረሳችሁ አንዳንዶች እንዳላችሁት ሁሉ በድጋሚ ከፈለጋችሁ በጋዜጠኝነት አልያም በህዝብ ግንኙነት mood ማጣራት ይቻላል የዶክተሮቼን መረጃ አያይዥአለሁ። ለኔ የህክምና ወጪ ለማሰባሰብ ground ሎቢ በማድረግ ለማከላከል ከሞከር ይልቅ ከተላላኪነት በመውጣት ራሱን ወደቻለ ግልጽ ህዝባዊ ስራ መስራት ይበልጣል።
በተረፈ ለተደረገልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ። 
Filed in: Amharic