>
5:13 pm - Thursday April 20, 1933

ባልደራስ መስከረም 4 በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ምንም አይነት ድርሻ የለውም!!! (ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ) 

ባልደራስ መስከረም 4 በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ምንም አይነት ድርሻ የለውም!!!
 ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ 
የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ነኝ ያለው አካል በእምነት ሽፋን የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ መቷል።
 በዚህ ውስጥ ደግሞ በአንድም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የአዲስ አበባን ጉዳይ ነክቷል። የአዲስ አበባ ጉዳይ ደግሞ በቀጥታ የባላደራ ምክር ቤቱን የሚመለከትና የተነሳበት አላማ ነው።
 (ኢትዮ 360 – ጳጉሜ 5/2011) የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ባልደራስ መስከረም 4 በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ምንም አይነት ድርሻ እንደሌለው የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገለጸ።
 ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቆይታ እንደገለጸው ባላደራ ምክር ቤቱ በእምነት ጉዳይ ላይ ጣልቃ የሚገባበት አንዳችም ምክንያት የለውም።
 ሃይማኖትና ፖለቲካ እጅግ የተለያዩና ፍጹም የማይገናኙ ጉዳዮች መሆናቸውን ባላደራ ምክር ቤቱ አጥብቆ ይናገራልብሏል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ።
 ትልቅ ክብርና ቦታ ያለውን ሃይማኖት ወደታች አውርዶ ከፖለቲካ ጋር ማወዳደር በራሱ አግባብነት የሌለውና አክብሮትን ማሳጣት ነው ይላል።
 አርብ መስከረም 2/2011 ባላደራ ምክር ቤቱ የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫም ቢሆን ከዚህ ጋ ምንም የሚያገናኘው ጉዳይ የለም።
 በዋናነት የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ነኝ ያለው አካል በእምነት ሽፋን የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ መቷል።
 በዚህ ውስጥ ደግሞ በአንድም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የአዲስ አበባን ጉዳይ ነክቷል።
 የአዲስ አበባ ጉዳይ ደግሞ በቀጥታ የባላደራ ምክር ቤቱን የሚመለከትና የተነሳበት አላማ ነው ይላል እስክንድር ነጋ።
 ስለዚህ ባላደራ ምክር ቤቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ አቋሙን በመግለጫው ማሳወቅ ይፈልጋል።
 ለመስከረም 2/2011 ከጠዋቱ 4 ሰአት ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ዋና ጽሕፈት ቤት ለሃገር ውስጥና ለውጭ መገናኛ ብዙሃን ሊሰጥ በእቅድ የያዘው መግለጫም አደራጅ ነኝ ለሚለው አካል ግልጽ ምላሽ የሚሰጥበት ነው።
 ይህን ምላሽ ሲሰጥም ይላል እስክንድር ወዶ ሳይሆን በሁኔታዎች አስገዳጅነት የተነሳ  ነው ሲል ገልጿል።
 እንደ አንድ ዜጋ ወይንም እንደ አንድ አካል እሁድ ስለተጠራው ስብሰባ አስተያየት ልንሰጥ እንችላለ፣ያ ማለት ግን የሰልፉ ጠሪ እኛ ነን ማለት አይደለም።
 በሰላማዊ መንገድ የተጠራውን ሰልፍ የፖለቲካ አጀንዳቸው ለማድረግ የሚሯሯጡ አካላት እንዳሉ ይታወቃል።–ይሄ ግን የባላደራው አቋም አይደለም ሊሆንም አይችልም ሲል በግልጽ አስቀምጧል።
 እንደ እስክንድር አባባል የመስከረም 2ቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሁሉንም ነገር ግልጽ ያደርጋል ብሏል።
 እኛ የየራሳችን እምነት አለን ያንን እምነታችንን ደግሞ ሁላችንም እናከብራለን ይሄ ግዴታችን ሆኖ ሊሰመርበት ይገባል ነው ያለው ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ።
 በሌላ በኩልም በእስር ቤት ያሉትን የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መጠየቃችንን አናቋርጥም ብሏል በቃለ ምልልሱ።
 የተወሰኑት ተለቀዋል ጥሩ ነው።ነገር ግን የተፈቱትም ሆነ በእስር ቤት ያሉት ሁሉም ንጹሃን ናቸው፣ ያለ ወንጀላቸው የህሊና እስረኞች እንዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል ሲል ነው የገለጸው።
 ስለዚህ መጪው አዲስ አመት ነው፣እያለቀሱ ከሚጠብቋቸው ህጻናት ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋ በአሉን እንዲያከብሩ ሊለቀቁ ይገባል ሲልም ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቆይታ ጥሪውን አቅርቧል።
Filed in: Amharic