>
11:13 pm - Wednesday November 30, 2022

በመስከረም ፬ ሰልፍ  ምንም ብዥታ የለም (ሀብታሙ አያሌው)

በመስከረም ፬ ሰልፍ  ምንም ብዥታ የለም
ሀብታሙ አያሌው
ለማንኛውም ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ  እየጠበቁ ባላደራውን ጭቃ ለመቀባት የሚሰለፉት እነማን እንደሆኑ ማርክ ማድረጉን አትርሱ!!!
* የሰልፉ አስተባባሪዎች በግልፅ የታወቁ ናቸው
* ባለአደራው አጋርነቱን ከመግለፅ በቀር በሰልፉ
    ምንም ድርሻ አለኝ አላለም። እንደሌለውም እስክንድር
     ነጋ ለኢትዮ 360 በቃለ ምልልስ አረጋግጧል።
* አጋርነት ከሁሉም አገር ወዳድ ተቋማትና ግለሰቦች
   ይጠበቃል
                           *-*-*
በእኔ እይታ
————-
የማንኛውም እምነት ተከታይ፤ የሲቪል ማህበር፤ የፖለቲካ ድርጅት፤ የሙያ ማህበር፤ የፌደራልና የክልል መንግስታት፤ ዓለም አቀፍ ተቋማት፤ የውጭ አገር መንግስታት፤ አህት አብያተክርስቲያናት…በመስከ 4 ቀን በሰላማዊ ሰልፍ ትዕይንት የሚገለጠውን  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህልውና እና የፍትህ ጥያቄን በመደገፍ አጋርነታቸውን ቢያሳዩ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ተመዝግበው ይኖራሉ እንጂ ለምን ደገፋችሁን አይባሉም።
ድጋፍ ለማሳየት ቀዳሚ የሆነው የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ምስጋና ይገባዋል።   የባላደራው ምክርቤት ኃላፊ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ እንዳለው ባላደራው በመስከረም 4ቱ ሰልፍ ምንም ድርሻ የለውም።
ለማንኛውም ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ  እየጠበቁ ባላደራውን ጭቃ ለመቀባት የሚሰለፉት እነማን እንደሆኑ ማርክ ማድረጉን አትርሱ።
 
        ***
 
የመስከረም 4ቱ ሰልፍ አስተባባሪዎች
★ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት፤
★ የመንፈሳዊ ኰሌጅ ተማሪዎችና ምሩቃን፤
★ በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን፤
★ የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት፤
★ የሠለስቱ ምዕት ማኅበራት ኅብረት፤
★ የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ተናሥኦት
      ኅብረት፤
★ የጽዋ ማኅበራት ሙሴና ደርገ ሙሴዎች ናቸው፡፡
አጠቃላይ የሰልፉን ሂደት በተመለከተ ዛሬ በኅብረት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።
                     ***
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውም፤ የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው።
                                  መዝ 95÷4
 
የባለአደራው ጉዳይ
ባለአደራው ምክር ቤት የመስከረም 4 ቀን ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።
መግለጫው የባለአደራው ምክርቤት አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው የአዲስ አበባ ህዝብ ስለፍትህ ሲል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጎን እንዲቆም ለማሳሰብ እና ጥሪ ለማቅረብ ከሆነ በእርግጥም ባለአደራው ለፍትህና ለህዝብ መቆሙን ያረጋግጥበታል።
ባላደራውን ሊያስወቅሰው የሚችለው ለእውነትና ለፍትህ አለመቆም እንጂ ለድጋፍ አጋርነት ማሳየቱ አይደለም። አዲስ አበባ የአንድ ብሔር ናት የሚለው አደገኛ የሆነው የቄስ በላይ  ጉሩፕ ለአዲስ አበባ ህዝብ ስጋት ነውና ሊወገዝ ይገባል የሚል አቋም ካሳየ ይመሰገናል እንጂ አይወቀስም።
ደግፎ ለመሳተፍ ለማንም ክፍት ነው።  ወደጅ የሚለየውም በዚህ የመከራ ጊዜ በሚያሳየው አጋርነት ነው። የእምነት ተቋማት እና ሌሎች ሲቪል ማህበራት ከዚህ በላይ ሳይረፍድ ልክ እንደ ባለአደራው አጋርነታቸውን ቢገልፁ መልካም ይመስለኛል።  የሰልፉ ባለቤትና አስተባባሪ ግን ሰልፉን የጠሩት ማህበራት ናቸው። ለማንኛውም ሌላ ዓላማ ማዋል ሐጢያትም ወንጀልም ይሆናል በሚለው እስማማለሁ።
 የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት 
ለሀገር ውስጥና ለውጭ መገናኛv ብዙሃን የተላለፈ ጥሪ
✔️ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመስቀል አደባባይና
       በተለያዩ ከተሞች የሚደረገውን ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በተመለከተ
✔️ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አዳራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ  ቀሲስ በላይ መኮንን ስለ አዲስ አበባ የተናገሩትን በተመለከተ
✔️ በኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢና አዲስ  አበባን በሚመራው ኦህዴድ መካከል ስላለው ግንኙነት
➡️  ዓርብ፣ መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም

                 🕟  ከጠዋቱ 4፡30 

▶️  በአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ዋና ጽ/ቤት
                 🔴 ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል
አድራሻ፡- ከአራዳ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ፣ ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኘው ዋና ጽ/ቤት
Filed in: Amharic