>

የሰልፉ አስተባባሪ ካህን በደህንነቶች ታፍነው ተወሰዱ!!! - "መስከረም 4 ማንም አያቆመንም" ቀሲስ ምትኩ በየነ ለጠ/ሚሩ ... (ዘመድኩን በቀለ)

የሰልፉ አስተባባሪ ካህን በደህንነቶች ታፍነው ተወሰዱ!!!
ዘመድኩን በቀለ
“መስከረም 4 ማንም አያቆመንም”
ቀሲስ ምትኩ በየነ ለጠ/ሚሩ ከሰጧቸው ምላሽ!
★ መንግሥት ሆይ በገዛ እጅህ ነገር አታበላሽ። መብትን መጠየቅ አያሳስርም። ይሄ እንደ ፖለቲካው አይደለም። ካህን አስረህ ዝም የሚልህ አይኖርም። እየመከርኩ ነው!!!
 
ጅማ ላይ የተደረገውም እንዲሁ ነው። የሰልፉን አደራጅ ፖሊስ ያዘው። ህዝቡም ለምን ብሎ ጠየቀ። መንግሥትም ፈታው። አዲስ አበባስ ይደገም ይሆን?
•••
ከመስከረም 4ቱ ሰልፍ አደራጆች መካከል በጥብዓት ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ወኪሉ ቀሲስ ምትኩ ደምሌን የፌደራል ደኅንነቶች ነን ያሉ አካላት አሁን እንደያዙአቸውና ወደ ፖሊስ ጣቢያም እንደወሰዷቸው እየተነገረ ነው።
•••
ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በነበረው ወይይት በኃይልና በሥልጣን በጥበብም ይሞግቱ የነበሩት እሳቸው እንደነበሩም ተነግሯል። ዛሬከክልል ፕሬዘዳንቶች ጋር በነበረው ስብሰባም ዋነኛ ሞጋች እንደነበሩ ተሰምቷል።
•••
የአዲስ አበባውን ሰልፍ አስተባባሪዎች ማስፈራራት እና እነሱኑ በጎሳ አቧድኖ ለመከፋፈልም ጥረት ሲያደርግ የቆየው መንግስታዊ አሸባሪ ቡድን ከጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከክልል ፕሬዝዳንቶች ጋር በነበረው ውይይት ሰልፉን ከመፍቀድ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው የተናገሩት  እና ሰልፉን ማቆም እንደማይቻል የተከራከሩትን  የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ወኪል ቀሲስ ምትኩ ደምሌ ዛሬ ጧት 5ኪሎ ቅድስተማሪያም አካባቢ ደህንነቶች አፍነዋቸዋል ተብሏል። ቀሲስ ምትኩ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ታቢያ እንደተወሰዱም ተነግሯል።
60ሚሊዮን ኦርቶዶክሳዊያን የተዋህዶ ልጆችን አስሮ እና ገድሎ ካልጨረሰን በቀር የአንድ ሰው መታሰር ከመስከረም 4ሰልፍ እንደማያግደን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል። የሰልፉ ዓላማ ማንም እንዲህ እየተነሳ እንዳያፍነን ፣እንዳያስረን፣ በሃያማኖታችን እንዳይረማመድ እና በቤተክርስቲያናችን እንዳይመጣብን ለማሳሰብ እንደሆነ ልብ ማለት አለብን። ይህን ሰልፍ የሚቀር የተዋህዶ ልጅ መጭው ጊዜ እንደ አውሬ የሚታደንበት መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለበትም።
መንግስት የሚያደርገው ይህ እስራት እና ለቤተክርስቲያን አቃጣዮች የሚሰጠው ከለላ የትልቁ ጸረ ኦርቶዶክሳዊ ዘመቻ አካል መሆኑን ማወቅ ይገባናል። መስከርም 4 በምንም እና በማንም ምክንያት ስለ እናት ቤተክርስቲያን የምናደርገውን ሰልፍ የሚያቆም ምድራዊ ሃይል የለም።
***
በእነ መብራቱ ኪሮስ ጥርስ የተነከሰባቸው ካህን ምትኩ ዛሬ ከክልል ፕሬዘዳንቶች ጋር በነበረው የኮሚቴ ውይይት ላይ ቆይተው ሲመለሱ ቅድስት ማርያም አካባቢ በደኅንነቶች ታፍነው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተነገረኝ። ስልካቸው ተዘግቷል። ጥሪም አይቀበልም።
•••
እናም ወዳጄ ሰልፉ ተደረገም አልተደረገ አውሬው እንደሆን መናደፉን አይተውህም። ወይ ቀድሞ አለመጀመር ነበር። አሁን ሁሉ ነገር ጫፍ ከደረሰ በኋላ መንሸራተት ኮሚቴዎቹንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመበላት አያድናቸውም።
•••
የሚሻለው፣ የሚበጀውም ሰልፉ ቀርቶ በተናጥል ከምትበሉ። ( ደግሞም መበላታችሁ አይቀርም።) ሰልፉ ተደርጎ ከዚያ በኋላ የሚመጣም ነገር ካለ በፀጋ መቀበሉ ነው የሚሻለው። ሰማዕትነትም ቢሆን።
•••
መንግሥትም ቢሆን የሚሻለው ሰልፉን መፍቀድ፣ ጥበቃውን ማጠናከር እንጂ የልጅ ጨዋታ ባይሞክር መልካም ነው። ዘመነ ዮሐንስ ዘመነ ሰማዕታት በመባልም ይታወቃል። እናም ኦርቶዶክሳውያን ዘምረው ለሚገቡት ነገር ብዙም ባይንበጫበጭና ባቡሩን ከሃዲዱ ላይ መስመሩን ባያስተው መልካም ነው።አዎ! ቀሲስ ምትኩ በየነ እንዳሉት ከመስከረም 4 ሰልፍ ማንም አያቆመንም!
•••
ጅማ ላይ የተደረገውም እንዲሁ ነው። የሰልፉን አደራጅ ፖሊስ ያዘው። ህዝቡም ለምን ብሎ ጠየቀ። መንግሥትም ፈታው። አዲስ አበባስ ይደገም ይሆን? በኋላ መግለጫው ላይስ ምን ይባል ይሆን? ሲኖዶሱስ ምን ዓይነት አቋም ይኖረው ይሆን?
•••
ለማንኛውም  በእነ ዶክተር ዘሪሁን ሙላት የሚመራ የመንፈሳዊ ኮሌጁ ማኅበረሰብ አባላት ወደ 3ተኛ ፖሊስጣቢያ ሰሜን ሆቴል አካባቢ ሊፈልጓቸው እየሄዱ እንደሆነም መረጃው ደርሶኛል።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
መስከረም 2/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic