>

የጃዋር መሐመድ ፖለቲካ!!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የጃዋር መሐመድ ፖለቲካ!!!   
አቻምየለህ ታምሩ
ጃዋር መሐመድ መንግሥታዊ የሆነው ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን ያዋቀሩበት ርዕዮት ዓለም ውጤት እንጂ የኢትዮጵያ ችግሮች መንስዔ አይደለም። ወደፊትም ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን ያዋቀሩበት ርዕዮተ ዓለም መንግሥታዊ  ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ  ጃዋር መሐመድ  ኖረም  አልኖረም ርስበርስ እየተከሳከስን ሞትን የምናነግስበት የኢትዮጵያ ሁኔታ መቀጠሉ አይቀርም። የጃዋር  መሐመድ  አቅም ይህንን የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ራሱን ሀብታም ለማድረግና ዝና ለመግዛት መጠቀም  እንጂ በኩነቱ ላይ የሚጨምረውም ሆነ  የሚቀንሰው አንዳች ነገር የለውም።
ኦነግ ኢትዮጵያን ያዋቀሩበት መንግሥታዊ  ርዕዮት ዓለም ባይኖር ኖሮ  ጃዋር መሐመድና ዲስኩሩ  ከገለባ የቀለለ፤ጠልቆ ሊገባ የማይችል፣ሐሳብ  የሌለበትና የትኛውንም የማኅበረሰብ ክፍል ሊቀይር የሚችል አይደለም። ጃዋር መሐመድን ያተለቀው ኦነጋውያን የፈበረኩትን ለሕጻን ልጅ  እንኳ የማይወራ የጅል ፈጠራ ሲያስተጋባ  ሳይመረምር እንደወረደ የሚቀበልና እንደፈለገ የሚነዳው የቁቤ ትውልድ መፈጠሩ ነው። ጃዋር  ለሕጻን ልጅ  እንኳ የማይወራ የጅል ፈጠራ የሚያስተጋባው በሌላው ዘንድ መሳቂያ መሳለቂያ ቢያደርገውም የቁቤው ትውልድ  ግን  ያምነኛል የሚል ከፍተኛ ድፍረት ስላለው ነው። በሌላ አነጋገር የጃዋር  መሐመድ የፖለቲካ  ካፒታል የቁቤን ትውልድ ጅል  ነው ብሎ ከልቡ ማመኑ ነው።
ኦነጋውያን  ከዛሬ መቶ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር አምስት ሚሊዮን በማይሞላበት ወቅት ምኒልክ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ ጨፈጨፈ የሚል እጅግ አስቂኝ የፈጠራ ታሪክ ሲያሰራጩ የኖሩት ለሌሎች ቢያስቅም ኦሮሞን ግን ያሳምናል ብለው ስለሚያምኑ ነው። ጊዜ ሰጥተው ትንሽ መጠበብና ከዚህ የተሻለ ተረት ተረት ፈልስፈው ኦሮሞ አማራን እንዲጠላ ማድረግና ርስበር ማጫረስ ተስኗቸው ሳይሆን ኦሮሞን ለማሳመን ያን ያህል ውጣ ውረድ አያስፈልገውም ብለው በማሰባቸው ነው። ጃዋር መሐመድ እየተከተለው ያለው ይህንን አባቶቼ ናቸው ያላቸውን የኦነጋውያንን መንገድ ነው።
ባጭሩ የጃዋር  አቅም  የሐሳብ የበላይነት፣ የሞራልና የሕሊና ልዕልናና የአስተሳሰብ ጥራት  ሳይሆን እሱ ራሱ ውጤት የሆነበትን ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን ያዋቀሩበት ርዕዮት ዓለም ተጠቅሞ ለሕጻን ልጅ  እንኳ የማይወራ የጅል ፈጠራ እያመረተ ሲሰጠው ሳይመረምር እንደወረደ የሚቀበለውንና እንደፈለገ በሚነዳው የቁቤ ትውልድ እያስፈራራ ብር መሰብሰብና  ምንም ተጠያቂነት የሌለበትን የመንጋ ድርጅቱ እያስነሳ የዐቢይ አሕመድን አገዛዝ  በማዋረድ ዝና መግዛት ነው።  ኢትዮጵያ የተዋቀረችበት አስተሳደብ ዛሬው የተለየ ቢሆን ኖሮ ጃዋር  እንደ እውቀት ጾመኛነቱ  ኢትዮጵያ ውስጥ የተለየ  እውነታ ለመፍጠር ሺሕ ዓመታት  እንኳ ቢኖር ከቶ አይቻለውም።
የበቀለ ገርባ፣ የመላው የኦነግ ሠራዊት አቅም ያው ነው። ሁሉም ከገለባ የቀለሉ፣ ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን ያዋቀሩበት ርዕዮተ ዓለም አውሎ ንፋሱ የበተነውን እየቀለቡ የሚበሉ ጥንብ አንሳዎች ናቸው። በመሆኑም በኢትዮጵያ ምድር ካሁኑ የከፋ የርስበርስ ጦርነት ከተነሳ የሚነሳው በነሱ ምክንያት ሳይሆን  ወያኔና ኦነግ ኢትዮጵያን ያዋቀሩበት መንግሥታዊ የሆነው  ርዕዮት ዓለም  የሚወልደው የጎሳ ግጭት  በራሱ ኃይል እየተቀጣጠለ ሲሄድ በሚፈጠረው   የርስ በርስ ፍጅት ነው።
Filed in: Amharic