>

"በአለፉት አመታት ሁለት አይነት ታጋዮች ነበሩ፤ እነሱም የዴሞክራሲ ታጋዮችና ተረኛ ጨቋኝ ለመሆን የታገሉ ናቸው!!!" (እስክንድር ነጋ/ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች)

“በአለፉት አመታት ሁለት አይነት ታጋዮች ነበሩ፤ እነሱም የዴሞክራሲ ታጋዮችና ተረኛ ጨቋኝ ለመሆን የታገሉ ናቸው!!!
    እስክንድር ነጋ – ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች 
ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ከናሁ ቲቪ ጋር መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት ካደረገው ቆይታ በከፊል የተወሰደ ነው።
የአዲስ አበባ ነዋሪ ወደየ ቀበሌው እንዲሄድና ማን እየወጣ እነማን እንደሚገቡ እንዲያረጋግጥ ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጠይቋል።
እስክንድር ነጋ እንደገለፀው በኦሮሞ ብሄርተኝነት ዘንድ ተረኛ ገዥ ወይም ጨቋኝ ለመሆን እየተሰራ ነው።
“በወያኔ ዘመን የታሰርነው ሰዎች መብታችንን ለማስከበር ቢሆንም፣ መብታችንን ተጠቅመን የምናሳካው አላማ ግን ይለያያል። ወያኔ ከተለወጠ በሗላም ይሄው ፍላጎታችን ፍንትው ብሎ ታይቷል” በማለት ነው የገለፀው ጋዜጠኛ እስክንድር።
“በሆነ አጋጣሚ ስልጣን በኦሮሞ እጅ ቢገባ የምናወራርደው የታሪክ እዳ ስላለ እንጠቀምበታለን፣ ሌላው ቀርቶ ስልጣኑ በአሳሪያችን ኦህዴድ እጅ ቢገባ እንኳን ኦህዴድን እንደግፈዋለን” የሚሉ የኦሮሞ ብሄርተኞች እስር ቤት ውስጥ አጋጥመውኛልም ብሏል።
የተረኝነት መገለጫውም “በወያኔ ዘመን እነ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ብሄርተኞች በሀገሪቱ ‘ስር-ነቀል ለውጥ’ መምጣት አለበት በሚል ከእኛ ጋር ተመሳሳይ አቋም ነበራቸው ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር፣ ዛሬ ግን ተገልብጠው ‘ጥገናዊ ለውጥ’ ነው የሚያስፈልገው፣ ህገ መንግስቱም መነካት የለበትም” እያሉን ይገኛሉ በማለት አብራርቷል።
ኦዲፒ አዲስ አበባን ኦሮማይዝድ ለማድረክ አበክሮ እየሰራ ነው ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወደየ ቀበሌው እንዲሄድና ማን እየወጣ፤ እነማን እየተተኩ እንደሆን እንዲያረጋግጥ ጠይቋል።
ምንጭ:- የህግ ባለሙያ ዘፋኒያህ አለሙ
Filed in: Amharic