>

የህወሓት ተስፋፊነትና "የታላቋ ትግራይ" ቅዠቱ!!! (ቸርነት ጌታሁን)

የህወሓት ተስፋፊነትና “የታላቋ ትግራይ” ቅዠቱ!!!
ቸርነት ጌታሁን
የህወሓት ዋና አጀንዳ የሆነዉን የታላቋን ትግራይ ምስረታ በተመለከተ ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ፅፊያለሁኝ! አሁንም ትንሽ የምለዉ ስላለኝ አዳምጡኝ!!!።
ህወሓት በማናፊስቶዉ የታላቋን ትግራይ የመመስረት ዓላማ በአስቀመጠዉ መንገድ የአማራ እርስትን በጉልበትና በሀይል በመንጠቅ አላማዉ ሁሉ በድል እየሔደለትና ድል እየቀናዉ እየመጣ እንደሆነ ጭላንጭል መረጃዎች ያሳያሉ። ከዛሬ ሀያ ዓመታት ወዲህ በሀይል የራያን፣ጠለምትና ወልቃይት ጠገዴን ይዞ የቆዬና እያስተዳደረ ያለ መሆኑ ያለ ጥሬ ሀቅ ነዉ!! ከዚህ ጋር በተያያዘ ከታች የምታዩት የታላቋ ትግራይ ካርታ እዉን ይሆን ዘንድ የአማራ እርስት የሆነዉን የጎጃምን ምድር መተከልን ከጎጃም ቆርሶ ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰጠ ለመሆኑ አሁንም መሬት ላይ ያለ ጥሬ ሀቅ ሆኖ እናገኘዋለን! ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለፈዉ ዓመት የለዉጡ መንግስት ከመጣ ወዲህ የቀድሞዉ የቤኒሻንጉል ክልል ርዕሰ ምስተዳደር አቶ ያረጋል አይሸሹም በአንደ ቃለ ምልልስ ላይ የድሮዉ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሊቀ ሰይጣን ሟች መለስ ዜናዊ ትግራይ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ጋር ወሰን እንዳላት ገልፆለት ይህነን ታሳቢ በማድረግ የመተከል አማራን እረፍት የመንሳትና የዘር ማጥፋት በተጠና መልኩ በመዋቅር እንዲፈፀምበት መናገሩ አቶ አይሸሽም በቃለ ምልልሱ ላይ የሰጡት አስተያየት መሆኑን ልብ ይሏል!!! ታዲያ ይህነን ካርታ እዉን ለማድረግ ቀሪዉን የምዕራብ ጎንደር መሬትን ደግሞ የሀሰት ትርክት በመፈብረክ ቅማንትና አማራን እሳትና ጭድ አድርጎ ቤንዚን እያርከፈከፉ ክብሪት መለኮስ ማቃጠል ከጀመሩም አመታት አልፈዋል!
ለረጅም አመታት በደምና በስጋ የተጋመደዉን አንድነትና የአንድ አጥንት ፍላጭ የሆኑትን ቅማንትና አማራን በተለያዩ ጊዚያቶች በሚሸርቡት ሴራ አሁን በቅማንት በኩል ሰምሮላቸዉ የድል ጭላንጭል መታየቱም ጀምሯል! የቅማንት ህዝብ ለለፉት ድፍን ሰላሳ አመታት አሁን በቅማንት በኩል ሰምሮላቸዉ የድል ጭላንጭል መታየቱም ጀምሯል! የቅማንት ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለለፉት ድፍን ሰላሳ አመታት በስዉር፣ የአማራ ህዝብ በማያወቀዉና ጭራሽ በማይጠብቀዉ መልኩ በህወሓት የአማራ-ጠል ትርክት ከመጠመቁም በላይ ላለፉት ዓመታት በማናለብኝነት በህወሓት ባለ ስልጣናት ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ስልጠና ከተሰጠዉ በኋላ ጭራሽ በሀገሪቱ መከላከያ ስራዊት እጅ እንኳን ሊገኝ የማይችል ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ እንዲታጠቅ ተደርጓል ይህ ሁሉ ስራ የሚሰራዉም ዋና መቀመጫዉን መቀሌ ያደረገዉ በዚሁ በቅማንት ህዝብ ስም የሚነግደዉ የቅማንት ኮሚቴ(ቅዴፓ) መሆኑም መሬት ላይ ያለ ጥሬ ሀቅ ነዉ።
በተደጋጋሚ አማራዉን ከምዕራብ ጎንድር ጠቅልሎ በማፅዳት(Genocide) በመፈፀም፣ በማፈናቀልና በማስወጣት፣ ሀብት ንብረቱን አዉድሞ በማደህየት፣ አማራዉ ጠቅልሎ እርስቱን ትቶ ብን ብሎ እንዲጠፋ በማድረግ ምዕራብ ጎንደርን በቅማንት ስም መጠቅለል ነዉ!፡ እኔ በግሌ በእዉነት በመዳህኒያለም እምላለሁኝ የቅማንትን ህዝብ ጭራሽ ከአማራ ወገኑ የተለዬ እንደሆነ አስቤም ሰምቼም አላዉቅም ነበር!። ነገር ግን አሁን እንደማየዉና እንደምሰማዉ ከሆነ ድፍን የቅማንት ህዝብ በሚባል ደረጃ በአማራ ህዝብ ላይ በክፍተኛ ጥላቻ የናወዘ መሆኑን ለመረዳትም ችያለሁኝ!። ላለፉት አመታት የሰሩትን ትተን እንኳ በሰሞኑ በአንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ሾፌሩንና ረዳቱን በአሰቃቂ ሁኒታ ከገደሉ ብኋላ  ከነሚኒባሱ መንገደኞችን ወደ ገደል የተወረወሩበት ድርጊት በጭራሽ ከሰበዓዊነት የወረደና እጅግ በጣም ከባህላችን ያፈነገጠ አረመኒያዊ ድርጊት ሆኖ በማግኘቴ ነዉ!። ጊዜዉ ከፍቷል! አንጀታችን ተበጥሷል!
Filed in: Amharic