>

አክራሪዎች ጋር በቋንቋ መግባባት በፍጹም አይቻልም (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

አክራሪዎች ጋር በቋንቋ መግባባት በፍጹም አይቻልም

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ኦቦ በቀለ ገርባና አክቲቪስትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በናሁ ቲቪ ያካሄዱትን ጭቅጭቅ (ውይይት ማለት ስለሚከብድ ነው) አሁን ከዩቲዩብ አውርጄ እያየሁ ነው፡፡

አንድ ሰው በአግባቡ ተከራክሮ ማሸነፍ ሲያቅተው፣ ተፋላሚውን በሃሳብ መርታት የሚያስችለው ሚዛን የሚያነሣ የመከራከሪያ ነጥብ ሲያጥረው ወደምን እንደሚገባ ለማወቅ ይህን ዝግጅት ማየት ብቻውን በቂ ነው፡፡ ከስሜትና ከአሉቧልታ ውጭ ረብ ያለው ነገር ይዞ ወደ ክርክርና ውይይት የማይገባ ሰው በቅጽበት መላ ሰውነቱ በንዴት ሲምቦገቦግና ወደ ቁጣና ስድብ እንዲሁም አስተሳሰብን ሣይሆን ስብዕናን ወደሚያጠለሽ ዘለፋና ዛቻ ሲለወጥ እንታዘባለን፡፡ ተፈጥሮ በውነቱ ታዳላለች፡፡ አንዱ ከአእምሮ ጓዳው በልክ በልክና በዘርፍ በዘርፍ ከሚፈለገው የዕውቀትና የጥበብ ማዕድ እየጨለፈ ሃሳቡን በተረጋጋ ሁኔታ ሲያፈስ ያ ዓይነት ችሎታ የሌለው ግልብና የስሜት ፈረስ ጋላቢ ደግሞ ቅኔና ቀረርቶን መለየት እንዳቃተው ያገሬ ደብተራ የተከራካሪውን መሃል አናት ሊበረቁስበት ውኃ የማያሰኝ ዱላና ደቦል ድንጋይ ፍለጋ አካባቢውን ሲያማትር ይታያል፡፡ የአለመታደል ገጽታው ብዙ ነው፡፡

በቀለ ሰው ባይኖረው እንጂ ቢኖረው ኖሮ ከሚዲያ ዕይታ ውጪ ቢሆን ይበልጥ ተጠቃሚው ራሱ ነው – አሁን እኮ የሰው መሣቂያ እየሆነ ነው፤ መደበሪያም ጭምር፡፡ (ዩቲዩብ ግባና በበቄ ንግግር ድብርትህን አስወግድ” ቢባል ትክክለኛ ምክር ይመስለኛል – ውይ የእናት ማኅጸን ስንቱን ያወጣል፡፡ እውነቴን ነው – ሚዲያ በጭራሽ አያዋጣውም፡፡ ብዙ ጊዜ አየሁት፡፡ አገር ያወቀውንና ጠሐይ የሞቀውን የኦሮሞን በፌዴራል መንግሥት የበላይነት ሲሸመጥጥ ቅንጣት ቅር አይለውም፤ የሚያናቅፈው ነገርም የለም፡፡ ለነገሩ ውሸትና ቅራሪ እንዲህ ያለ ሰው ነው የሚፈልጉት ይባላል – ሳያጣጥሙ ይዞ ሽምጥጥ!

በቄ እንዲያውም በብጥለው ገለበጠኝ ዓይነት ያረጀ ያፈጀ ፈሊጥ ኢቲቪንም ንግድ ባንክንም ትምህርት ሚኒስቴርንም … አማራ በበላይነት ይዞ እንደተቆጣጠረው ያለ ሀፍረት ሲናገር ለሚሰማው ሰው የወያኔዎችን የዘመናት ልፋት በዜሮ በማባዛቱ ዘሄግ ላይ በተሰየመው ዓለም አቀፍ ችሎት ፊት መገተር ነበረበት፡፡ መጥፎነቱ ከሳሾቹ መቀሌ ላይ ስለመሸጉ በቄ እንዳሻው ቢፏልል ዝምቡን እሽ የሚለው የለም፡፡ ወይ መማር ከንቱ! መማር እንዲህ የሚያጃጅል ከሆነ ከነገ ጀምሮ ልጆቼን ከትምህርት ቤት አስወጣለሁ፡፡ መማር እንደነሕዝቅኤልና ጃዋር ኅሊናን እያሣተ በጥቅምና በድውይ ዓላማ የሚያሣውር ከሆነ ትምህርት ባፍንጫ ቀርቶ በፍንጭት ጥርስም ይውጣ፡፡ እናስ ታዲያ እኔስ ገንዘቤን ለምን በከንቱ እከሰክሳለሁ? በዚህ መልክ ስንቱ ይሆን በገንዘቡ የሚጫወት? ሰው ተምሮ ቁም ነገር ካልሠራ “መማሩ” ይቅርና መወለዱ ራሱ በቁጭት ያንገበግባል፡፡ ሀገር ለማፍረስ?

እንጂ ከ1983 ዓመተ ምሕረት ወዲህ በተለይ ሁሉንም ነገር ወያኔዎች ተቆጣጥረው አማራን እግር በእግር እየተከታተሉ ከኢትዮጵያ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ዐውድ ሙልጩን እንዳላወጡት ዛሬ ይህ በቀለ የሚባል ጀዝባ ቢጤ ተነስቶ አማራን በበላይነት ሲከስ መደመጡ ማሣፈር ብቻ ሳይሆን ሰውዬውን ማሳሰር የሚያስችል ወንጀል ነበር፡፡ ሁለት በደል ነዋ! “ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” ያለችው ማን ነበረች? እንኳንስ የበላይ ሊሆን በገዛ ቀየውም መኖር በተፈቀደለት፡፡ በቅርቡ እንኳን ኦህዲድ አይደለም እንዴ ባሕር ዳር ድረስ ሄዶ የአማራ አመራሮችን በዘዴ አጨፋጭፎ (ጨፍጭፎ?) ክልሉን በእጅ አዙር በራሱ ሠርጎ ገቦችና አበረ አዳሙን ለመሰሉ የግንቦት ሰባት ተላላኪዎች ያስረከበው? አናውቅምና ነው? እ? ንገሩኝ ባይ ሁላ!

እስክንድር እንዳለው የአክራሪ ኦሮሞዎችን ተፅዕኖ በዐይን አይቶ ለመረዳት ከተራ ቀበሌና ወረዳ እስከ ከፍተኛና የፌዴራል ተብዬው መሥሪያ ቤቶች ተዟዙሮ መቃኘት ነው፡፡ መብልና መጠጥ (ጉቦና ሙስና ማለቴ ነው) ያለባቸው መሥሪያ ቤቶች በተለይ የኦነግና ኦህዲድ ዋና መንፈላሰሻዎች ናቸው፡፡ ወደዚያ ዝር የሚል የሌላ ጎሣ አባል የለም፤ ቢኖርም በነሱ በጎ ፈቃድና የነሱ ተባባሪ ሆኖ ነው፡፡ ንግድ ባንክ፣ አየር መንገድ፣ ገቢዎች፣ … የኦነግ/ኦህዲድ አንጡራ ሀብቶች ናቸው፡፡ ያ ጀዝባ “ፖሊስ መሆን ምኑ ያስቀናልና ነው እንዲህ ያንጫጫችሁ…?” ሲል እስክንድርን መውቀሱ ደግሞ ሳልጠቅሰው ማለፍ የማፈልገው ሙትቻ ሃሳብ ነው፡፡ ፀጥታውንና መከላከያውን መያዝ ማለት የሁሉም ኦህዲዳዊ ወንጀሎች አረንጓዴ መብራት መሆኑን ጀለንፎው መምህርና የኦነግ ካድሬ በቀለ ገሪባ አልተረዳም ወይም ሊረዳ አልፈለገም፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስና የትራፊክ ፖሊስ ሁሉ ከሞላ ጎደል ኦሮሞ ነው፡፡ ስትሰርቅና ስትዘርፍ፣ ህግን ስትደፈጥጥ የሚይዝህን የፖሊስ ኃይል በራስህ ሰዎች ከተቆጣጠርክ ከዚህ በላይ የበላይነት የት አለ?

አንባቢ ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ! ድንቁርና ለካንስ በመማር አይወገድም፡፡ የአእምሮ መካንነት ለካንስ በዲግሪና በዕድሜ ብዛት አይቃናም፡፡ የበቄን መሰሉ በከንቱ ያለፈ ዕድሜ “የእንጨት ሽበት” መባሉ ለካንስ እውነት ነው – እንጨትና ድንጋይም ስለሚሸብቱ፡፡ ሸውራራ አመለካከት ለካንስ በትምህርት አይስተካከልም፡፡በየፈጠጠ ማኅበራዊ እውነትን ለመረዳትና ተረድቶም በሃቅ ለመመስከር ለካንስ ከስሜታዊነትና ከዘረኝነት ልክፍት መጽዳትን ይጠይቃል! በበኩሌ እጅግ አፈርኩ፡፡
አበስኩ ገበርኩ! በሉ ያን የበቀለ ገሪባን ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ያላያችሁ ዩቲዩብ ግቡና እዩት፡፡ እዩትናም አፋችሁን በመዳፋችሁ አፍናችሁ በአግራሞታዊ የማሽላይቱ ዓይነት ሣቃችሁ ተንተክተኩ፡፡ በሰው ተፈጥሮም ማፈርን እንዳትረሱ፡፡ ውይ! ጎሠኝነት እንዲህ ያበለሻሻል? እስከዚህን ኅሊናን ያሣውራል? ያ ሣተና መምህር፣ መምህር ታዬ ቦጋለ ይህን የበቀለ ገሪባን “ክርክር” ቢመለከት ምን ይል ይሆን? እንደኔው በንዴት መንጨርጨሩ መቼስ የማይቀር ነው፡፡ ከዚህን ዓይነቱ ሰው ጋር እንደሰው መቆጠር ራሱ ያበሳጫል፡፡ ወዴት ሄደን እንኑር?

Filed in: Amharic