>

ሜንጫ ወደ ጓዳ፤ ሀሳብ ወደ ሜዳ!! (ዳንኤል ሺበሺ)

ሜንጫ ወደ ጓዳ፤ ሀሳብ ወደ ሜዳ!!
ዳንኤል ሺበሺ
አቶ በቀለ ገርባ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ  በናሆ ቴቪ ያደረጉትን የሀሳብ ሙጉትን ተከታትያለሁ፡፡ በእኔ እይታ በቄ! በብዙ ነጥቦች እስክንድርን መቋቋም አቅቶታል፡፡ ይህ ማለት ግን አቶ በቀለ ገርባ የተናገረው ሁሉ ዜሮ ነው እያልኩ አይደለም፡፡ በሙጉቱ ወቅት ለጋሽ በቄ! አቀበት ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ሁለቱን ብቻ ባነሳ፦
የተረኝነት ጉዳይ
” የአሁኑ መንግስት አውቀው ይሁን ሳያውቁ አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የተረኝነት ስሜት አለ። በየ ቀበሌው፣ በየ ክፍለ ከተማው፣ በከንቲባው ቢሮ ከላይ እስከታች አለ። የበፊቱ ነገር እየተደገመ ነው ወይም እያቆጠቆጠ ነው። በየመስሪያ ቤቱ
የተረኝነት ስሜት አለ። አሁን ላይም የሥራ እድገት፣ ሹመት ወዘተ. . .የሚሰጠው በማንነት ነው።”
ስለ አዲስ አበባ እና ለሀገር ያለው ግንዛቤ
የሥነ ልቦናና ትርጉም ማነስ ነው ፤ ምናልባት ለወደፊት ይረዳው እንደሆነ ለእኔ በገባኝ መጠን ጥቂት ነገር ላካፍልለት፡፡
አቶ በቀለ ሲናገር “ኦሮሚያ አገር” እያለ በተደጋጋሚ ሲጠቀምበት ነበር፡፡ ይህ ደሞ ተራ የአፍ ወለምታ አይመስለኝም ፡፡ አገር ማለት ኢትዮጵያ እንጂ ኦሮሚያ፣ አማራ ወይም ሶማሌ ወዘተ አይደለም፡፡ በዓለም ካርታም ሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ኦሮሚያ የሚባል አገር የለም! አማራ፣ አፋር ወይም ደቡብ … የሚባል አገር የለም! ወደፊት አገር እንሆናለን የሚባል ነገር ካለ እሱ ሌላ ጉዳይ ነው፤ ሌላ ሀሳብ ነው፡፡
የሰውን ልጅ ለምን አሰብክ? ብሎ መክሰስ ፀረ-ዴሞክራቲክ ነው፤ የቀዳማዊ ኢህአዴግ ባሕሪይ ነው የሚሆነው ፡፡ እነዚህ ክልልም በሉት ክ/ሀገር፣ ዞንና ቀጠና ወዘተ የሚባሉ ለአስተዳደር አመችነት ሲባል የተከፈሉ ክፍለ-ሀገራት ወይም በኢህአዴግ አጠራር ክልሎች ናቸው እንጂ ሉዓላዊ (Sovereignty) ሀገር አይደሉም፡፡ ወደፊት ደሞ ሌላ ስም ይወጣላቸው ይሆናል፡፡
ሌላው ለጠቅላላ ዕውቀት የሚረዳን ከሆነ ጥቂት ነገሮ ላክልበት፦
#አገር ማለት በዓለም ውስጥ ያሉ አገራት በሙሉ፤ በዓለም አቀፉ ዕውቂና የተሰጣቸው አንድ መንግሥት፣ ሕዝብና የታወቀ ድንበር ያለው ሲሆን፤
#ሀገር ማለት ደሞ የትውልድ ሀገርሽ/ህ (homeland) ወይም ዜጋ የሆንክበት ሀገር ነው፡፡
ሳጠቃልል ከኦሮሞ ብሔርተኞች ውስጥ ጋሽ በቄ! ከእስኬው ጋር ካደረገው ሙጉት ይልቅ አቶ ጃዋር መሀመድ ወደ አዲሱ ዓመት (2012) መግቢያ ሰዓታት ሲቀሩት ከራሱ ሚዲያ ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ ቀልቤን ስቧል፡፡ ውስጥ ውስጡ የተደበቁትንና ከጀርባው የታዘሉ ነገሮችን ማጠንን ትቼው ማለቴ ነው ፡፡
በተረፈ ሜንጫ ወደ ጓዳ ሀሳብ ወደ ሜዳ! መመለሱ በራሱ ተስፋ ሰጪ ነው ፡፡ ፍርድ የሕዝብ፣ የአድማጭ ፥ ተመልካች ነው፡፡ ሰላም!
Filed in: Amharic