>
5:13 pm - Saturday April 19, 5208

መንጋ ነጅ ከሰገነት ወርዶ የሃሳብ መሪ ወደ መንበሩ ይመጣል!!! (መስከረም አበራ)

መንጋ ነጅ ከሰገነት ወርዶ የሃሳብ መሪ ወደ መንበሩ ይመጣል!!!
መስከረም አበራ
ናሁ ቴሌቭዥን አቶ እስክንድር ነጋን እና ኦቦ በቀለ ገርባን በአንድ ሃገር ልጅነት አገናኝቶ እንደ አምባሰል ገደል የራቀ እሳቤያቸውን፣ርዕዮታቸውን፣የፖለቲካ ግንዛቤያቸውን ጥልቀት ታዝበናል፨ ይህ ሁሌ የምመኘው ነገር ነበር።በየሚዲያው ብቻውን ብቻውን ተንሰራፍቶ  የሚያቅራራ አወቅኩ ባይ ሁሉ ከቢጤው ተፃራሪ ባለ ሃሳብ ጋር ፊት ለፊት ተገናቶ ቢነጋገር የፖለቲካችን የፈውስ መንገድ አሃዱ ይባል ነበር የሚል የቆዬ ጉጉት ነበረኝ!
ይህንኑ ምኞቴን በአንድ ወቅት ኢሳት ቲቪ ላይ “ኢትዮጵያ ነገ” በሚባል ፕሮግራም ላይ በተጋበዝኩበት ወቅት ተናግሬ ነበር።የሃገራችን ፖለቲካ  ለእግዜር እንኳንአስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ቋንቋው የተደባለቀው በግንዛቤ ከሚቀራረበን የሃሳብ ተፃራሪያችን ጋር ቀርቦ ፊት ለፊት መነጋገር ስለማንወድ ነው።
መናገር(መናገር እኩል አይሆንም ከመነጋገር)የምንወደው በእውቀትም፣በልምድም ለሚያንሱን፣ነገራችንን “አዎአዎ” እያሉ የሚቀበሉ፣እውቀት ጢቅ አድርገው ለሚያስቡን፣አንዳንዴም ሊያመልኩን ለሚቃጣቸው ፣ገደል ግቡ ብንላቸው ገደል ለመግባት ለማይመለሱ የዘውጋችን ጎረምሶች ነው።አንድ ሚዲያ ላይ ለብቻ ተከስቶ ሃላፊነት በዞረበት ያልዞረ እሳቤን እንደ ሙሶሎኒ እጅ እያወናጨፉ፣መላ አካልን እያርገፈገፉ፣አይን እያፈጠጡ አውርቶ መውረድ የዘውግ ፖለቲከኞች ከመንፈስ አባታቸው ከመለስ ዜናዊ የወሰዷት የክርክር ባዶነትን መደበቂያ መንገድ ነች!
 ይህ ደግሞ የፖለቲካችንን ህማም ወደ ነቀርሳነት ቀይሮ አሰልስሎ ይገድለናል እንጅ ለጤና አይሆነንም።ሃሳብ ወዲያውኑ በሌላ ሃሳብ ተመክቶ ሲፋጭ ሶስተኛ ቀና መንገድ ብልጭ ማለቱ አይቀሬነው፣አሰፍስፎ ሊነዳ የተዘጋጀን መንጋም ይበትናል።በባዶ ሃሳብ መንጋ መንዳት ውሃ ይበላዋል።ሃሳብ ያለው ብቻ ሃሳባዊውን የፖለቲካችንን የድህነት መንገድ ገቢራዊ ያደርገዋል።ባለ መንጋ ነጅ ከሰገነት ወርዶ ባለ የሃሳብ መሪ ወደ መንበሩ ይመጣልባለ።
ይሄኔ ፖለቲካችን የሃሳብ እና የሰው ይሆናል!ይህን ለማድረግ መንገድ የጠረገው ናሁ ቲቪ እና አዘጋጅ ጋዜጠኛው ምስጋናዬ ይድረሳቸው።
 በቀጣይ እንዲሆን የምመኘውን ክርክር ምድብ እንዲህ እንዲህ ባቀርብስ?
ጃ-war  መሃመድ #Vs ታምራት ነገራ
ፀጋዬ አራርሳ  #Vs አቻምየለህ ታምሩ
ግርማ ጉተማ #Vs አቤል ዋበላ
ዳንኤል ብርሃኔ #Vs ስዩም ተሾመ
ብርሃኑ ሌንጅሶ #Vs ታዬ ቦጋለ
ደሳለኝ ጫኔ #Vs አገኘሁ አሰግድ
እዝቅኤል ገቢሳ #Vs አበባው አያሌው
ሙክታር ኡስማን #Vs አፈንዲ ሙተቂ
ኢታና ሃብቴ #Vs ቬሮኒካ መላኩ
ሊበን ዋቆ #Vs ተክሌ የሻው
ሄኖክ የሽጥላ #Vs እኔ (“የወዳጅነት ግጥሚያ ነው?” የሚል የተረገመ ይሁን 😉 ሄኖክን የመረጥኩበትን ምክንያት ሌላ ቀን አስረዳለሁ።
የሞት ምድብ
Filed in: Amharic