>

በቤተክርስቲያን ላይ የተወረወረው ሌላኛው ቀስት!!! (ሀብታሙ አያሌው)

በቤተክርስቲያን ላይ የተወረወረው ሌላኛው ቀስት!!!
ሀብታሙ አያሌው
ጃ – ዋር “በሜንጫ አንገታቸውን እንቆርጣለን!!” ካለው ዛቻና ድፍረት ጋር የሚተካከል ዘመቻውን ቀጥሏል ! ዛሬ በይፋ “ምን እንደሚያጨሱ ማወቅ እፈልጋለሁ” ሲል ለመሳለቅ ሞክሯል።
የቤተክርስቲያንን ቃጠሎ እናወግዛለን የሚል ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች በታሰሩበት አገር የእምነቱን አስተምህሮ በይፋ መሳለቂያ ለማድረግ እየሰራ ያለው ይህ ግለሰብ በመንግስት ጠባቂ ታጅቦ የፈለገውን ሁሉ ያደርጋል።
ይህ ለቤተክርስቲያንና ለአማንያኑ ትልቅ መልዕክት ነው። የቤተክርስቲያኒቱን ህልውና የሚፈታተነው የሰይጣን ፈረስ በይፋ ደምቆ ወጥቷል። ሳምንት ደግሞ ኢሬቻ ለማክበር የመንግስት ስልጣን ከያዙት ቱባ ባለስልጣናት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ይቆማል።
ይህ ፅሑፍ ሌላም አላማ ያዘለ ነው። የህዝበ ክርስቲያኑን እምነት በይፋ ሳንቋሽሽ አማንያኑ በብስጭት የአፀፋ ምላሽ ይሰጣሉ በዚህም መዘላለፉ በኢሬቻ አክባሪዎች እና በህዝበ ክርስቲያኑ መካከል ይሆናል፤ ምናልባትም ወደ ብሔረሰብ ተኮር ከፍ ይላል የሚል እኩይ አላማ ያነገበ ነው። ሁሉም ነገር ጥንቃቄ ይፈልጋል…!
እርግጥ ነው” ወፍ ዘራሽ ፈላስፋው ” “መንጋው ” ከዚህ በላይ ሊያስብ አይችልም !!
Filed in: Amharic