>

ጥቅምት 2 መስቀል አደባባይ እንገናኝ፤ ስለ አፓርታይዳዊው አገዛዝም ድምጻችንን እናሰማ!!! (ባልደራሱ)

ጥቅምት 2 መስቀል አደባባይ እንገናኝ፤ ስለ አፓርታይዳዊው አገዛዝም ድምጻችንን እናሰማ!!!

ባልደራሱ
የአዲስ አበባ ህዝብ ጥቅምት 2 ቀን ጧት 3ሰዓት ላይ መስቀል አደባባይ በመገኘት አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እየተተገበረ ያለውን ህገወጥ ስራ ተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ ተጠርቷል። 
* በአዲስ አበባ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን እና አረንጓዴ ስፍራዎችን ለቄሮዎች ህገ ወጥ ካርታ በማደል ማከፋፈል እንዲቆም፣
* ህዝብ ለዓመታት ገንዘብ የቆጠበባቸውን የጋራ መኖሪያዎች በልዩ ጥቅም ስም ለአንድ ጎሳ ያለእጣ ጠቅልሎ መስጠትን ለማስቆም፣
* በህገ ወጥ መንገድ ከባለቤቶቹ እውቅና ውጭ የቤተሰብ ፎርም ላይ ሰዎችን እየሞሉ መታወቂያ ማደል እንዲቆም ፣
* በየ መንግስታዊ ተቋማቱ እየተተገበረ ያለውን የዘር መድሎ የሚታይበትን አሰራር ለማጋለጥ፣
* በይፋ ከዜግነት መስመር ተገፍቶ አፓርታይዳዊ መስመር ውስጥ እንዲገባ በተፈረደበት የአዲስ አበባ ህዝብ እና ስለአዲስ አበባ እጣ-ፈንታ ድምጻችንን እናሰማ።
Filed in: Amharic