>

በሽብር ወንጀል ተጠርጥሬ መታሰሬ አስገርሞኛል.. የእውነት አምላክ ፍርዱን ይሰጣል ! " (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ )

በሽብር ወንጀል ተጠርጥሬ መታሰሬ አስገርሞኛል “
      ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ  
–  “የእውነት አምላክ ፍርዱን ይሰጣል ! “
በተለያዩ መጽሔት እና ጋዜጣ ላይ በዋና እና በምክትል አዘጋጅነት እንዲሁም በሪፖርተር ያዥ በጋዜጠኝነት የሰራ ሲሆን ፤ በተለያዩ መጽሔት እና ጋዜጣ ላይ አምደኛ በመሆን በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ በነጻ ሚዲያ ውስጥ የላቀ ተሳትፎ በማድረግ ይታወቃል ።
     በተለይ የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ ሥርዓት ፤  ጋዜጠኞች ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር እና አባላት ፣ እንዲሁም የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሜት አባላትን ፤ በግፍ አስሮ በሚያሰቃይበት በዚያ ፈታኝ ወቅት ፤ ከማዕከላዊ እስር ቤት እስከ ተለያዩ የማጎሪያ እስር ቤቶች ድረስ በመሄድ፤  እንዲሁም የፍርድ ቤት ውሎ መረጃዎችን በማጠናከር በማህበራዊ ድረገጽ የእስረኞች ድምጽ በመሆን የተቻለውን ሁሉ አድርጎ እንደነበረ የሚታወቅ ነው።
     በቅርብ ደግሞ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቀው ፣ በጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ በሚመራው “የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ” ውስጥ  በፀሐፊነት እያገለገለ ይገኝ ነበር።
      ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረገ ሲሆን ፤ ፖሊስ ጣቢያ ፣ ማዕከላዊ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በተለያየ ጊዜ የታሰረበት ቦታ ነው።  ሁሌም ለፍትሕ ወደኋላ የማይለው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ  !  ከሙያው ባሻገር በማህበራዊ ህይወትና በመልካምነቱ ብዙዎች ይመሰክሯለታል ።
      ጋዜጠኛ ኤልያስ ፤ ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ .ም ፤  ወደ ቤቱ እየሄደ 4 ኪሎ አካባቢ ምሽት በግምት 2፡30 ላይ በደህንነት ሰዎች የተያዘ ሲሆን ፤ ኤልያስ ገብሩን ጨምሮ 13 ግለሰቦችን በአንድ መዝገብ በማደራጀት፣ ፖሊስ ከሰኔ 15 አሳዛኝ ክስተት ጋር በተገናኘ ” በሽብርተኝነት ድርጊት “
ጠርጥሪያቸዋለው በማለት ለባለፉት ሦስት ወር ታስረው  ይገኛሉ ። ( ከኤልያስ ጋር ታስረው በአንድ መዝገብ የነበሩ 10 ሰዎች በተለያየ ወቅት ከእስር የተፈቱ ሲሆን ፣ ኤልያስ ጨምሮ 3 ብቻ ቀርተዋል ።)
     ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፤   ስለ-ተጠረጠሩበትና ታስረው ስለሚገኙበት የሽብር ክስ በተመለከተ ፤ ከዚህ ቀደም እንደገለጸልኝ እንዲሁም  አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሊያውቁልኝ ይገባል በማለት ሃሳቡን እንዲህ አጋርቶኛል ፦
      ” በስመአብ” በማለት የአግራሞት ሳቅ በመሳቅ ፤ ” ከእኔ ጋር ተከሳሽ የሆኑት 13ቱ ተከሳሾች አንዳቸውንም  ከዚህ ቀደም አይቼቸው አላቅም ፣አያውቁኝም አላውቃቸውም ፤ ነገር ግን ከእነሱ ጋር በመሆን ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገሃል ተብዬ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሬ መታሰሬ አስገርሞኛል። በዶ/ር ዐቢይ የሚመራው መንግስት እንዲህ አይነቱ የሐሰት ውንጀላ ውስጥ በዚህ ፍጥነት ይገባል ብዬ አልገመትኩም ነበር ፤ በእኔ ላይ የተፈጸመው መንግስታዊ በቀል ነው ፤ ሃሳቡን በነፃነት የመግለጽ መብቴን ተጠቅሚ ለአገር እና ለወገን ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ሁሉ፣ የሌላውን መብት ሳልጋፋ በአገኘሁት አጋጣሚ  ከመግለጽ ወደኋላ አላልኩም ።
       በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሃሳብና ትችት ከመስጠት ባለፈ ፣ የእኔን ሃሳብ ከሚጋሩ ጋር በመሆን  የበኩሌን በጎ አስተዋጽኦ፣በህጋዊ መንገድ ለማድረግ ጥረት አደርግ ነበር። እነኚህ እንቅስቃሴዎቼ በሙሉ አሁን ላይ በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት ደስ አላሰኘውም ፤ ለዚህም ነው በማላውቀው ወንጀል የተወነጀልኩት” በማለት የደረሰበትን በደል በመግለጽ ፤ “የእውነት አምላክ ፍርዱን ይሰጣል ! ” የሚል መልዕክቱን አስተላልፏል ።
ጋዜጠኛ ኤልያስ’ን ጨምሮ ስለ ፖለቲካ እስረኞች አሁንም ፤ ስለ-ፍትሕ ዝም አንልም ፤ ፍትሕ ፣ፍትሕ ፣ ፍትሕ !!!
*
      ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፤  በተለያዩ መጽሔት እና ጋዜጣ ላይ በዋና እና በምክትል አዘጋጅነት እንዲሁም በሪፖርተር ያዥ በጋዜጠኝነት የሰራ ሲሆን ፤ በተለያዩ መጽሔት እና ጋዜጣ ላይ አምደኛ በመሆን በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ በነጻ ሚዲያ ውስጥ የላቀ ተሳትፎ በማድረግ ይታወቃል ።
     በተለይ የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ ሥርዓት ፤  ጋዜጠኞች ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር እና አባላት ፣ እንዲሁም የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሜት አባላትን ፤ በግፍ አስሮ በሚያሰቃይበት በዚያ ፈታኝ ወቅት ፤ ከማዕከላዊ እስር ቤት እስከ ተለያዩ የማጎሪያ እስር ቤቶች ድረስ በመሄድ፤  እንዲሁም የፍርድ ቤት ውሎ መረጃዎችን በማጠናከር በማህበራዊ ድረገጽ የእስረኞች ድምጽ በመሆን የተቻለውን ሁሉ አድርጎ እንደነበረ የሚታወቅ ነው።
     በቅርብ ደግሞ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቀው ፣ በጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ በሚመራው “የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ” ውስጥ  በፀሐፊነት እያገለገለ ይገኝ ነበር።
      ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረገ ሲሆን ፤ ፖሊስ ጣቢያ ፣ ማዕከላዊ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በተለያየ ጊዜ የታሰረበት ቦታ ነው።  ሁሌም ለፍትሕ ወደኋላ የማይለው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ  !  ከሙያው ባሻገር በማህበራዊ ህይወትና በመልካምነቱ ብዙዎች ይመሰክሯለታል ።
      ጋዜጠኛ ኤልያስ ፤ ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ .ም ፤  ወደ ቤቱ እየሄደ 4 ኪሎ አካባቢ ምሽት በግምት 2፡30 ላይ በደህንነት ሰዎች የተያዘ ሲሆን ፤ ኤልያስ ገብሩን ጨምሮ 13 ግለሰቦችን በአንድ መዝገብ በማደራጀት፣ ፖሊስ ከሰኔ 15 አሳዛኝ ክስተት ጋር በተገናኘ ” በሽብርተኝነት ድርጊት “
ጠርጥሪያቸዋለው በማለት ለባለፉት ሦስት ወር ታስረው  ይገኛሉ ። ( ከኤልያስ ጋር ታስረው በአንድ መዝገብ የነበሩ 10 ሰዎች በተለያየ ወቅት ከእስር የተፈቱ ሲሆን ፣ ኤልያስ ጨምሮ 3 ብቻ ቀርተዋል ።)
     ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፤   ስለ-ተጠረጠሩበትና ታስረው ስለሚገኙበት የሽብር ክስ በተመለከተ ፤ ከዚህ ቀደም እንደገለጸልኝ እንዲሁም  አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሊያውቁልኝ ይገባል በማለት ሃሳቡን እንዲህ አጋርቶኛል ፦
      ” በስመአብ” በማለት የአግራሞት ሳቅ በመሳቅ ፤ ” ከእኔ ጋር ተከሳሽ የሆኑት 13ቱ ተከሳሾች አንዳቸውንም  ከዚህ ቀደም አይቼቸው አላቅም ፣አያውቁኝም አላውቃቸውም ፤ ነገር ግን ከእነሱ ጋር በመሆን ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገሃል ተብዬ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሬ መታሰሬ አስገርሞኛል። በዶ/ር ዐቢይ የሚመራው መንግስት እንዲህ አይነቱ የሐሰት ውንጀላ ውስጥ በዚህ ፍጥነት ይገባል ብዬ አልገመትኩም ነበር ፤ በእኔ ላይ የተፈጸመው መንግስታዊ በቀል ነው ፤ ሃሳቡን በነፃነት የመግለጽ መብቴን ተጠቅሚ ለአገር እና ለወገን ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ሁሉ፣ የሌላውን መብት ሳልጋፋ በአገኘሁት አጋጣሚ  ከመግለጽ ወደኋላ አላልኩም ።
       በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ሃሳብና ትችት ከመስጠት ባለፈ ፣ የእኔን ሃሳብ ከሚጋሩ ጋር በመሆን  የበኩሌን በጎ አስተዋጽኦ፣በህጋዊ መንገድ ለማድረግ ጥረት አደርግ ነበር። እነኚህ እንቅስቃሴዎቼ በሙሉ አሁን ላይ በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት ደስ አላሰኘውም ፤ ለዚህም ነው በማላውቀው ወንጀል የተወነጀልኩት” በማለት የደረሰበትን በደል በመግለጽ ፤ “የእውነት አምላክ ፍርዱን ይሰጣል ! ” የሚል መልዕክቱን አስተላልፏል ።
ጋዜጠኛ ኤልያስ’ን ጨምሮ ስለ ፖለቲካ እስረኞች አሁንም ፤ ስለ-ፍትሕ ዝም አንልም ፤ ፍትሕ ፣ፍትሕ ፣ ፍትሕ !!!
Filed in: Amharic