>

የኦነጋውያን መሰባሰብ. . . (አቻምየለህ ታምሩ)

የኦነጋውያን መሰባሰብ. . .
አቻምየለህ ታምሩ
በመርኅ ደረጃ ማንኛውም አይነት መሰባሰብ ጥሩ ነው። ጥሩነቱም መሰባሰብ የሃሳብ ብዝሃነት ስለሚኖረውና የሃሳብ ብዙሃነት ካለ ደግሞ ለዘብተኛ [moderate] የሆነው ስለሚያሸንፍ ነው። በኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅቶች ዘንድ የሚደረግ መሰሳሰብ ግን ብሔርተኞቹ የሃሳብ ብዝሃነት ስለሌላቸው ከመሰባሰባቸው የሃሳብ ብዝሃነት የሚያስገኘውን ትሩፋት ማግኘት አይቻልም። የኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅቶች መሰባሰብ አሁን ላይ በብዙ የአገራችን አካባቢ ጽንፈኛ የኦነጋውያን ድርጅቶች የስጋጭ ምንጭ የሆኑበትን ነባራዊ ሁኔታ ሊለውጠው አይችልም።
የኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅቶች መሰባሰብ ለሌላው ስጋት ከመሆናቸው በስተቀር በመሰባሰባቸው ከሀሳብ ብዝሃነት ሊገኝ የሚችለውን ትሩፋት ማግኘት እንደማይቻል ለመገንዘብ በመንግሥትነት የተሰየመው ኦሕዴድ የሚባለው ተረኛ በመንግሥትነት መሰየሙ ሳያስጨንቀው ንጹሐንን ሲጨፈጭፍ ከሚውለውና ሀያ ባንክ ከዘረፈው አሸባሪው ኦነግ ጋር አብሮ ለመስራት ሲፈራረም ማየቱ በቂ ነው። ኦሕዴድ ኦነግ ለምኖ አብሮ ለመስራት ሲስማማ የሚውለው በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ የሃሳብ ልዩነት ስለሌለው ነው።
በርግጥ የኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅቶች መሰባሰብ በሌላው ላይ አደጋ ሊሆን የሚችለው ሌላው ለመብቱ የማይቆም ከሆነ ብቻ ነው። አንድ ድርጅት ደካማ ሲሆን እንኳን የሌላውን ለመውረስ፣ ለመዝረፍና ለመግደል እንደ ዓላማ ይዘው የተቋቋሙት ኦነጋውያን ይቅርና ማናቸውም የፖለቲካ ኃይል መፈጠሩን ይረሳዋል።
አንድ እውነት የማይታለፍ እውነት አለ። ለክፋት የተሳባሰቡ፣የሃሳብ ብዝሃነት ሳይኖራቸው እንደአሜባ እየተቆራረጡ ሲራቡ ከርመው ዛሬ ተሰባሰብን የሚሉን ኦነጋውያን በስልጣንና የሌላውን ወርሰው ሲቀራመቱ መጣላታቸውና የኋላ ኋላ ርስ በርስ ተያይዘው መጠፋፋታቸው የማይቀር ነው። የሌላውን ለመቀማት የተሰባሰቡት ኦነጋውያን የኋላ ኋላ የወረሱትን ሲቀራመቱ መጠፋፋታቸው የማይቀር ቢሆንም ራስህን ለመከላከል ለመብትህ የማትቆም ከሆነ ግን የሌላውን ወርሰው ሲቀራመቱ በሚፈጥሩት ጠብ ተያይው እስኪጠፋ ድረስ ግን በሌላው ላይ የሚያደርሱት አደጋው የከፋ ይሆናል።
ባጭሩ አንድ አይነት ሃሳብ ያላቸው የአንድ መንደር ናዚስት ሥልጣን ፈላጊውዎች የሌላውን ሊወርሱ ሲሰባሰቡ ቢውሉ አደገኛ የሚሆኑት መድረኩን ለብቻቸው ሲቆጣጠሩ ብቻ ነው። የማይናወጥ አላማ ይዘህ ለኅልውናና ለመብትህ ከቆምህ አንድ አይነት ሃሳብ ይዘው የተነሱት ናዚስቶች ቢሰባሰቡም ተለያይተው የሚያንሸራሽሩት ሃሳብ ተሰባስበው ከሚያንሸራሽሩት ሃሳብ ስንቱንም ያህል የሚልቅ መርዛማ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም።
Filed in: Amharic