>

ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር ምጠሚር ደመቀ መኮንን (መስፍን አረጋ)

ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር ምጠሚር ደመቀ መኮንን

መስፍን አረጋ

ለክብር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የጦቢያ ምጠሚር (ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር)፡፡ ይህን ግልጽ ደብዳቤ የምጽፍልወ ‹‹ለውጥ›› ለሚባለው ክስተት ወሳኝ ሰዓት ላይ ያንበሳውን ሚና የተጫወቱት በቁርጥ ቀን ማጀት የተደበቀው ዐብይ አህመድ፣ ጌታቸው አሰፋን እንደ ጦር የሚፈራው ለማ መገርሳ፣ ወይም ደግሞ በባሩድ ጭስ በርግጎ ገደል የሚገባው የቄሮ መንጋ ሳይሆን ርስወ መሆንወንና፣ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ዐብይ አህመድ ከባሕር ዳር ጭፍጨፋ በኋላ ቁመው የማያወርዱት መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡

ራስወን ለከፍተኛ አደጋ በማጋለጥ ዐብይ አህመድን ለስልጣን ያበቁት፣ ጦቢያና የጦቢያ ብሔርተኞች (በተለይም ደግሞ አማሮች) ባማራ ጥላቻ ባበደው በጎጠኛው ወያኔ ከሚደርስባቸው መከራና ስቃይ ለመታደግ ነው ብየ አምናለሁ፡፡ ለውጡ ግን ለጦቢያ ብሔርተኞች (በተለይም ደግሞ ላማሮች) ትሻልን ሰድጀ ትብስን አመጣሁ የሚያስብል ከእሳት ወደ ረመጥ እንደሆነ ለርስወ መንገር አያስፈልግም፡፡

ወንጀለኛውን ኦነግን እየተንከባከበ፣ ሰላማዊውን አብንን የሚያዋክበው የእርስወ አለቃ ብቸኛ ዓላማ የኦነጋውያንን እቅድ ማሳካት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ጃዋር ያስባል፣ ዐብይ ይፈጽማል፡፡

ጃዋር ማሰብ ይችላል፣ መብቱ ነው፡፡ ዐብይ መፈጸም የሚችለው ግን በእርስወ ድርጅት አዴፓ አማካኝነት አማራውን እስካዳከመ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም የአማራ ጠላት ወያኔ ወይም ኦነግ ሳይሆን አማራ የለም የሚሉ ያንዳርጋቸው ጽጌ ፀራማራ ምልምሎች በብዛት የተሰገሰጉበት እርስወ የሚመሩት ድርጅት ነው፡፡ ወያኔ ለሃያ ሰባት ዓመታት ባማራ ላይ የተዘባነነው፣ ተረኛው ኦነግ ደግሞ ባማራ ላይ የሚጨማለቀው በስሙ ያማራ የሆነው የርስወ ድርጅት በግብሩ ፀራማራ በመሆኑ ብቻና ብቻ ነው፡፡

ስለሆነም የጦቢያ ብቸኛ ችግር እርስወ የሚመሩት ድርጅት አዴፓ እንጅ ወያኔ ወይም ኦነግ ወይም ሁለቱም አይደሉም፡፡ ሁነውም አያውቁም ወደፊትም አይሆኑም፡፡ አማራው በጠንካራ ድርጅትና በቆራጥ መሪ ከተመራ የነዚህ ጎጠኛ ድርጅቶች እድሜ ከወራት እንደማይዘል እነሱ ራሳቸው በደንብ ያውቁታል፡፡ የርስወን አለቃ እንቅልፍ የሚነሳው የኦነግ ሚሊዮኖችን ማፈናቀል ወይም ደግሞ የወያኔ እስካፍንጫው መታጠቅ ሳይሆን፣ ያማራ ብሔርተኝነት ማቆጥቆጥ መጀመሩ መሆኑን እሱ ራሱ እንዲናገር ያስገደደውም ይህ ግንዛቤው ነው፡፡

ኦቦ ዐብይ አህመድ ከርስወ ድርጅት ጋር እንተባበር ወይም እንጣመር የሚለው አማራውን ለማዘናጋት እንጅ፣ እውነተኛ ትብብሩና ቅንብሩ ካማራ ጠላት ከወያኔ ጋር እንደሆነ የሚጠፋወት አይመስለኝም፡፡ ከእርስወ አለቃ ጋር አንዴ መቀሌ ሌላ ጊዜ አክሱም የሚሞዳሞደው ወያኔ፣ እርስወንና አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ነክሶ የያዘበትን ምክኒያት ለርስወ መንገር አያስፈልግም፡፡

ምዕራባውያን በቦሪስ የልትሲን አማካኝነት ሩሲያን አዋረዷትና በሩሲያውያን ላይ ለተወሰኑ ዓመታት ተጨማለቁባቸው፡፡ በዘበዟቸው፣ አደኸዩዋቸው፣ ተሳለቁባቸው፡፡ የልትሲን ሩሲያን ለምዕራባውያን የቀን ጅቦች አሳልፎ ቢሰጣትም፣ በስተመጨረሻ ግን ከቀን ጅቦቹ የሚያስጥላትን ሩሲያዊ አንበሳ በቦታው ተክቶ፣ ላገሩ ትልቅ ውለታ ውሎ፣ የቆሸሸውን ታሪኩን አጽድቶ፣ በክብር አለፈ፡፡ ሩሲያም ባጭር ጊዜ ውስጥ አንሰራራችና፣ ያምሷት፣ ያተራምሷት የነበሩት ምዕራባውያን አመሰችን፣ አተራመሰችን እያሉ ይወቅሷት፣ ይከሷት ጀመር፡፡ የተሳለቁባትን ተሳለቀችባቸው፡፡

እኔም መስፍን አረጋ እርስወን ክቡር አቶ ደመቀ መኮንንን የምማጸንወ የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) ቦሪስ የልትሲን በመሆን፣ ለኦነግ ጅብ የሰጧትን ጦቢያን ከጅቡ ለሚያስጥላት ጦቢያዊ ፑቲን ቦታወን እንዲለቁ ነው፡፡ ይህን ታሪካዊ ሥራ ከሠሩ የጦቢያ ችግር ባጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈታ በርግጠኝነት እነግርወታለሁ፣ ወያኔና ኦነግ የወረቀት ነብሮች ናቸውና፡፡

ለሚተካወት ጥቁር አንበሳ እንዲለግሱት የምፈልገው ምክር ደግሞ የሚከተለውን ነው፡፡

የጦርነት ማምከኛው ጦርነት ነው፣ የዘረኝነትም እንደዚሁ፡፡ የሚጠላህን እንዋደድ እያልክ ከተለማመጥከው ይሸሽሃል፡፡ እኔም እጠልሃለሁ ካልከው ግን ቢያንስ ባለበት ይቆማል፡፡ አንተ ከምትጠላኝ የባሰ እኔ እጠላሃለሁ ካልከው ደግሞ ወዳንተ ማዝገም ይጀምራል፡፡ ፍቀር የሚያሸንፈው በቀና መንፈስ ሲታገዝ ብቻ ነው፡፡ ጎጠኛን ጎጠኛ ያደረገው ደግሞ ከዝቅተኝነት ስሜቱ የመነጨው የቀና መንፈስ ድኻነቱ ነው፡፡

የመለማመጥ ትርፉ መከራን ማርዘም፣ ፍዳን ማብዛት፣ አበሳን ማባስ ብቻ ነው፡፡ የሚጠላን ሲለማመጡት በጥላቻው ላይ ንቀት ይጨምርበትና ይበልጥ ይጠላል፣ የሚጠላን ሲጠሉት ግን ጥላቸው በከበሬታ ይለዝባል፡፡ ውዴታ ቸሬታ፣ ከበሬታ ግዴታ ነው፡፡ ሰውን እንዲያከብር እንጅ እንዲወድ ማስገደድ አይቻልም፡፡ ማስገደድ ይቅርና ማስተማርም አይቻልም፡፡ ለዘረኝነት መድሐኒቱ ዘረኝነት ብቻ የሆነበትም ምክኒያት ይሄ ነው፡፡

ወያኔና ኦነግ ሊነገሩ የሚገባቸው በሚገባቸው ቋንቋ እንጅ ስላልፈጠረባቸው ከፍርሃታዊ መለማመጥ በሚቆጥሩት በትህትናና በጨዋነት አይደለም፡፡ በተለይም ደግሞ አማራ ጠል የሽብር ‹‹ኃይሎች›› የሚለው ተወግዶ፣ ጎንደርን የሚያናውጠው ወያኔ፣ መድረገኝን (ከሚሴን) የሚበጠብጠው ኦነግ መባል አለበት፣ ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታልና፡፡

ቆረጡኝ ፈለጡኝ የሚላቸው አጼ ምኒሊክ ያሠሩት ሐዲድ የፈጠሯቸውን የጦቢያውያን ከተሞች፣ ኦነግ የኔ የኦሮሞው ብቻ ናቸው ብሎ ቢሸፍቱ፣ አዳማ ስላላቸው፣ አጸፋውን ማግኘት አለበት፡፡ ይህ አጸፋ /መጀመር/ ያለበት ደግሞ ግራኝ በቀደደው በር የገባው ጅብ ‹‹ወሎ›› ብሎ ከጠራው የአማራነት ማዕከል ከሆነው ምድር (ምድረ አምሃራ) ነው፡፡ ላማራ ህልውና ወሳኝ የሆነው ይህ የአማራ ቅዱስ ምድር ‹‹ማሕበረ ላኮመልዛ›› ወይም ባጭሩ ‹‹ማላ›› ሲባል፣ ነዋሪወቹም ‹‹ማላየ›› ሊባሉ ይችላሉ፡፡ ወረኢሉ በቀድሞ ስሙ ዋሰል፣ ወረሂመኖ በቀድሞ ስሙ ሰገነት፣ ከሚሴ በቀድሞ ስሙ ምድረገኝ ወዘተ. እየተባሉ ተሰይመው ስያሜው በሕግ መደንገግ አለበት፡፡ ሕጉን የሚጥስ ማናቸውም መገናኛ ብዙሃን ደግሞ አይቀጡ ቅጣት መቀጣት አለበት፡፡

ኦነጋውያን አገሩን ሁሉ የኦሮሞ፣ ሰውን ሁሉ ኦሮሞ የሚሉት በኦሮምኛ የተሰየመውን ሁሉ የኦሮሞ እያስመሰሉ በማታለል ስለሆነ፣ ይህን ማታለያ ማምከን ይዋል ይደር የማይባል ብርቱ ጉዳይ ነው፡፡ የኦሮሞ ምድር ሰፊና ለም ነው፣ ኦሮሞ ብዙሃን ነው የሚባለው አለቅጥ ተነፋፍቶ ዝሆን ያከለው የነታከለ ፊኛ ተንፍሶ ካይጥ ማነስ አለበት፡፡ በበራራ (አዲስ አበባ) ዙርያ የሚኖረው ኦሮሞ ነው የሚባለው በደሙ ኦሮሞ ያልሆነው ሕዝብ የደርግ የመሬት አዋጅ ባለመሬት ያደረገው ቅጥረኛ ጭሰኛ እንደነበር በግልጽ መነገር አለበት፡ አዲስ አበባ ‹የጥጃቸው ማሰርያ›› የነበረችው የአቶ ያንዳርጋቸው ጽጌ አያት ‹‹ቂጢሳ›› መባላቸው ብቻ ኦሮሞነታቸውን የሚያረጋግጠው ላንዳርጋቸው ዓይነቶች ብቻ ነው፡፡ የነ አስመሮም ለገሰና ሐሰን አህመድ ውሸት ለጊዜውም ቢሆን ያሸነፈው ተጋጣሚው ቀርቶ በፎርፌ መሆኑን መዘንጋት አይገባም፡፡

ሮማን ፕሮቻዝካና (Roman Prochazka) መሰሎቹ በትክክል እንዳስቀመጡት ነጭ ጅብ የጥቁር አንበሶችን ገዳም ጦቢያን ሊፈነጭባት የሚችለው በጥቁር ጅቦቹ ወያኔና ኦነግ አማካኝነት አማራን ካዳከመ ብቻና ብቻ ነው፡፡ አማራ በጠንካራ ድርጅትና በቆራጥ መሪ ከተመራ ነጭም ሆነ ጥቁር ጅብ ከፊቱ አይቆምም፡፡ ስለዚህም ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ለራስወ መሽቶብወት ጦቢያን ሳያስመሹባት በፊት እባክወትን ምክሬን ይቀበሉኝና የቦሪስ የልትሲንን ፈለግ በመከተል የአማራ የሚባለውን ድርጅት መሪነትወን ላማራ ፑቲን ይልቀቁና እውነተኛ ያማራ ድርጅት ያድርጉት፡፡

መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic