>

"...አግላይ ጠቅላይነት  ወደፊትም ቢሆን መሰበሩ አይቀርም!!!'' (አቶ ሙሼ ሰሙ)

“…አግላይ ጠቅላይነት  ወደፊትም ቢሆን መሰበሩ አይቀርም!!!’
አቶ ሙሼ ሰሙ
* ”ነፍጠኝነት የመንደረተኝነት ታሪክ የለውም። ነፍጠኝነት ኦሮሞነት ነው፣ አማራነትም ነው፣ ትግራዮ፣ ሱማሌው፣ አፋሩ፣ ጉራጌው ወዘተ…ሳይቀር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነፍጠኛ ነው!!! 
—-
ነፍጠኛ የሚባል ስርዓትም ሆነ አገዛዝ አልነበረም፣ የለምም። ነፍጠኝነት ኢትዮጵያዊነትን ከኮሎንያሊዝም የታደገ የኢትዮጵያዊነት ከፍታ ነው። ነፍጠኞች በዱር፣ በገደል ከፋሽስት፣ ከወራሪና ከተስፋፊ ጋር ታግለው ሀገራቸውን የታደጉ የመላው ኢትዮጵያዊያንና የጥቁር ሕዝቦች ኩራትና ተምሳሌት ናቸው።
ትናንት በጠራራ ጸሃይ ተሰበሯል ተብሎ የተዘለፈው ሌላ ነገር ሳይሆን ይህው ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነው ሁሉን አቀፍ አዲስ አበቤነት ነው። ለኢትዮጵያዊነትና አዲስ አበቤነት መዘለፍና ለአግላይ ጠቅላዮች ጣራ መንካት መንስኤው ደግሞ “ኦሮማራ” የሚባል በራሱ ላይ ስለት ያነሳ መርህ አልባ ስብስብና “ለውጥ” እያለ ላለፈው ሶስት ዓመት በራሱ ላይ ውርደትን የጋበዘው ሃይል ነው።
እውነት ነው። “ኦሮማራ” ና “ለውጥ” እያልክ በነቂስ የታገለከው ሁላ ኢትዮጵያዊነትንና ሁሉን አቀፍ አዲስ አበቤነትን ባትሰብረውም ሳታውቀው አቁስለህዋል። በኢትዮጵያዊነትና አዲስ አበቤነት ላይ ምን እየተደገሰ እንደሆነም ከትናንትናው ዘለፋ ተረድተሃል።
አሁንም ኢትዮጵያዊነትና ሁሉን አቀፍ አዲስ አበቤነት ፈጽሞ እንደማይሰበር ከወዲሁ ተገንዝበህ ለኢትዮጵያዊነትህና ለአዲስ አበቤነት ዘብ ቁም። አግላይ ጠቅላይነት ግን ወደፊትም ቢሆን መሰበሩ አይቀርም።”
ምሁራን ተናገሩ፣ ዝምታችሁን ስበሩ!
Filed in: Amharic