>

እህተ ማርያምና ኢሬቻ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

እህተ ማርያምና ኢሬቻ!!!
ዘመድኩን በቀለ
 
 በዚህ ጉዳይ ቆሜ አጨብጭቤላታለሁ።  የእነ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን፣ የእነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን ፀጋና በረከት ያሳድርብሽ። እሷን ለመተቸት እሷን በልጦ መገኘት። አከተመ!!!
—-
“…ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።”   ዘዳግም 18:10-11
•••
የኢሬቻን ሰይጣናዊ አምልኮ አንገቱ ጉሮሮው ላይ ቆማ ማንቁርቱን ይዛ ስታወግዝ ያየሁት እህተ ማርያምን ብቻ ነው። ስለዚህች ሴት በደንብ ማወቅ ሊኖርብኝ ነው ማለት ነው። እሷን ለመተቸት ምላስህን የምትዘረጋ ሰባኪ ነኝ የምትል ሁሏ እስቲ ቃል ተናገር? አንተ ዓለም አቀፍ ሰባኪው እስቲ ቃል ተናገር? አንተ ባለ ቀሚሱ፣ አንተ ባለ ወርቅ ምላሱ፣ አንተ አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤው እስቲ ቃል ይውጣህ?
•••
ጠንቋይ ናት የምትላት፣ አጋንንት ነው የሚሾፍራት የምትላት ሴት አጋንንቱን በዚህ መጠን በኃይልና በስልጣን ስታንቧርቅበት አንተ የት አለህ? እስቲ አንተ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላኸው፣ በመንበሩ ፊት በዙፋኑ ፊት ዘወትር የምትቆመው፣ አንተ ካህኑ፣ አንተ መምህሩ እስቲ በለሆሳስ፣ በቀስታ እንኳ ስለ ኢሬቻ አስከፊነት፣ ባዕድ አምልኮነት በለሆሳስ እንኳ ተናገር፣ ተናገር እንስማህ። ወፍ የለም።
•••
እኔ በሴትየዋ ላይ ብዙ ጥያቄዎች ቢኖሩኝም በሁለት ጉዳይ ላይ ግን ቀልቤን ሰብስቤ ትንፋሼን ውጬ ቆሜ አጨበጨብኩላት። የምወደውን የጣና ቂርቆስን ገዳም ወደብና ሰባ ደረጃን የሚያስንቅ መወጣጫ አሠርታ የገዳሙን ችግር ስትፈታ ባየሁ ጊዜ፣ በገዳሙ ዙሪያ የነበረውን የእምቦጭ ተክል አጽድታ የገዳሙን ዙሪያ ከወራሪው አረም ነፃ ማድረጓን ባየሁ ጊዜ፣ የገዳሙ አባቶችም ደውለው በተደረገላቸው ነገር እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ባየሁ ጊዜ ለሁለቱ ጉዳይ አመስግኛታለሁ።
•••
እናም ኦቦሌሶ አፍ የለህም ዝም በል፣ ጭጭ በል፣ ጮጋ በል። እህተ ማርያም በለጠችህ። አንተ የቲዎሎጂ ምሩቁን፣ አንተ ምሑር ሰባኪውን በለጠችህ። አንተ በቤ ተክርስቲያን ስም ቱጃር የሆንከውን፣ ዐውደ ምህረቷ ላይ ቆመህ ሃብታም መርጠህ ያገባኸውን ነጋዴ ሰባኪ በለጠችህ። በለጠችህ ነው የምልህ። አፍ የለህም። ዝም በል። ዝም ጭጭ።
•••
ደግሞ እኮ አታፍርም የሚቀጥለው እሁድ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምህረቱ ላይ ቆመህ ልስበክ ትላለህ? አንተ እኮ አታፍርም ስለ ጎተራ፣ ስለጓዳ፣ ስለ መሶብ፣ ስለ ሌማት፣ ስለ ማድጋ፣ ሞላልሽ፣ ጎደለልሽ ብለህ ትንበጫበጫለህ። እስቲ ወንድ ከሆንክ እንደ እህተ ማርያም ተናገር፣ እስቲ ሰባኪ፣ ሐዋርያ ከሆንክ እንደ እሷ መስክር። አታደርገውማ። አትሞክራትም። አጋንንታም ሁላ  !!
•••
እህቴ እግዚ አብሔር ያክብርሽ። ስለ አንቺ መስማትም ባለመፈለጌ ጉዳዬ ብዬ እስከዛሬ ተከታትዬሽም አላውቅም። እዚህ ያሉ የአንቺ ወዳጆች የሚልኩልኝን ቪድዮዎችንም ከፍቼ የማየት ፍላጎትም የለኝም ነበረ። ሄራን የምትባል የአንቺ ወዳጅ አንቺ አዲስ አበባ ከመጣሽ ጀምሮ ስለ አንቺ አጫጭር ማስታወሻዎችንም ትነግረኝ ነበረ። ባንዲራው ላይ ያለውን ኮከብ በይፋ ካቃጠልሽበት ጊዜ ጀምሮ ማለት ነው።  https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=932419107122982&id=176519726046261
•••
ሻሎም !   ሰላም !
መስከረም 22/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic