>

ዛሬ በኢትዮጵያ እንዲህ ሆነ  !!  (ዘመድኩን በቀለ)

ዛሬ በኢትዮጵያ እንዲህ ሆነ  !!
ዘመድኩን በቀለ
አቤት የምኒልክ አምላክ ሥራ !! ግሩም ነው!!!ዕፁብ ድንቅ ነው!!!
 
ሀ ፥ በአዲስ አበባ 
በእቴጌ ጣይቱዋ አዲስ አበባ በ4 ኪሎ እንዲህ ሆኗል። የታላቁ መሪ፣ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሥራች የእምዬ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት የጎረቤት ሀገራት መሪዎች በተገኙበት የንጉሠ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት እጅግ ከፍተኛ በሆነ ወጪ ታድሶ አምሮና ተውቦ ተመርቆ ለህዠዝብ ዕይታ ክፍት ተደርጓል።
★ ለዚህ ቅዱስ ተግባር ለዛሬ ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድን አለማመስገን ሲበዛ በደል ነው። ገለቶሚ አቢቹ ኬኛ። የእምዬ ሚኒልክ አምላክ ይጠብቅህ። መንፈሳቸውም ቆራጥነታቸውም፣ ሀገር ወዳድነታቸውም ይደርብህ።
ውዳሴዬ እንደተጠበቀ ሆኖ ጥያቄዎች አሉኝ?!?
 
ሃውልቱ የማርያም ወዳጁን ክርስቲያኑን፣ ቆራቢውን  እምዬ ምኒልክን አይወክልም!!!
ብዙ ሰዎች ዛሬም በኖቤል ሽልማቱ ስካር ላይ ናቸው። እኔም በሽልማቱ ተቃውሞ የለኝም። የተጠራው የሀገሬ ስምና መሪዬ ስለሆነ ደስተኛ ነኝ። አቢቹን እንኳን ደስ አለህ ለማለትም ቅሽሽ አይለኝም። ግን ግን ደግሞ ጥያቄ አለኝ። ጠቅላዩ የተሸለሙት በሰላም ጉዳይ ነው ከተባለ ወዲ አፎም ከዚህ ሽልማት ተለይቶ የእኔው አቢቹ ለብቻው የተሸለመው ለምንድነው? ሰላሙ የአቢቹ ብቻ ነው እንዴ? አቢቹ ምን ዓይነት የተለየ ተልዕኮ ቢፈጽምላቸው ነው ፈረንጆቹ የሸለሙት ብዬ ብጠይቅ ኃጢአት አይሆንብኝም። ምቀኛም አያስብለኝም። በዚህ ጉዳይ የራሴን ዕይታ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ። አሁን ግን ጠዋት ወደ ጀመርነው ጥያቄ እንመለስ።
*  ጨፍኑ ላሞኛችሁ ነገርማ ደስ አይልም። የምን ሿሿ ነው? 
•••
በትናንትናው ውሎአችን ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ ከሙሐዘ ጥበባት ዲን ዳንኤል ክብረት ጋር ተመካክረው ከዓረቦቹ ተገኘ በተባለ የምጽዋት ብር የእምዬ ምኒልክ ቤተ መንግሥት እንዲታደስ ማድረጋቸውን አስመልክተን ስናመሰግናቸው ውለናል አምሽተናልም። ያጠፋን መውቀስ፣ የሠራ ያለማን ደግሞ ማወደስ የቆየ ሥራችን ባህልና ወጋችን ካደረግነውም ሰነባብቷልና ነው ያንን ማድረጋችን። ዛሬ ደግሞ ነግቷል። አዲስ ቀንም መጥቷል። ደስታችንም ስካራችንም በረድ ብሏል። እናም አንጎበሩ ሲለቀን ሰከን ብለን እነ ዳንኤል ክብረትንና አቢቹን ወሳኝ ጥያቄዎችን በትህትና እንጠይቃቸዋለን።
•••
ቦታው ሳይቀየር ስሙን መቀየሩ ለምን አስፈለገ???
 
እደግመዋለሁ በቤተ መንግሥቱ እድሳት ምንም ተቃውሞ የለኝም። ሥዕለ ማርያምና ጥንታዊና ታሪካዊም ቅርሳቅርሶች በምን አግባብ እንደተያዙ፣ የትስ እንደደረሱ ወደፊት የምንጠይቀው ይሆናል። በእድሳቱ ግን  በእኔ በኩል እንዲያውም ቆሜ ነው ያጨበጨብኩት። ታቃውሞዬ የሚመጣው ዛሬ ነው። በቦታው ላይ ለተሠራው ሥራ ቦታው ሳይቀየር ስሙን መቀየሩን እንዳልወደድኩት በቀዳሚው ጦማሬ በሰፊው ጠይቄያለሁ። አሁን ደግሞ ወደ ሁለተኛው ጥያቄዬ እመጣለሁ።
•••
ይህ የምታዩት የእምዬ ምኒልክ ሃውልት ነው ተብሎ የተሠራ ሃውልት በትናንትናው ዕለት ለዕይታ ከቀረቡ ምሥሎች አንዱ ነው። ይህ ጓደኛዬና ወዳጄ ያሬድ ሹመቴን የመሰለ ሃውልት እምዬ ምኒልክን ወክሎ ለዕይታ ቀርቧል። ነገር ግን ምሥሉን በሚገባ አተኩራችሁ ስታዩት እምዬን እንደማይወክል በሚገባ ታረጋግጣላችሁ።
•••
ሲጀመር እኒያን ክርስቲያን ንጉሥ የሚገልጣቸውን፣ የሚታወቁበትን አንዱንም መስፈርት አያሟላም።
• ሀ ፥ ከዘውዱ እንጀምር!
ቅባቱ ያለው፣ ኃይሉ ያለው፣ ሞገሱ፣ መፈራቱ፣ መከበሩ ያለው ከዘውዱ ላይ ነው። ዘውዱ ደግሞ መስቀለ ክርስቶስ የተቀረጸበት ነው። መስቀል ድግሞ ፦
• ኃይላችን ነው !
• ኃይላችን መስቀል ነው !
• የሚያፀናን መስቀል ነው !
• መስቀል ቤዛችን ነው !
• መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው !
አይሁድ ይክዱታል። እኛ ግን እናምነዋለን። ያመነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን። ድነናልም። እያልን ነው በዘወትር ጸሎታችን የምንጸልየው። እናም ዘውዱን አንስቶ የአሜሪካ እረኛ፣ የቴክሳስ ገበሬ ኮፍያ ማድረጉ ንጉሠ ነገሥቱን አይወክልም። በጭራሽ አይወክልም።
• ሁ ፥ ስለ ካባቸውን እንቀጥል!
• የኢትዮጵያ ነገሥታት ከዘውዱ ጋር አብረው ከሚጣየልቁት ምሥጢራዊ ልብስ መካከል የንግሥና ካባ አንደኛው ነው። በካባው ላይ ደግሞ በጠልሰም መልክ ከሚዘጋጁ ከህቡዕ ስመ አምላክ ጨምሮ በበርካታ መስቀል የተንቆጠቆጠ ነው። ይሄንን ለማረጋገጥ የነገሥታቱን ጥንታውያን ምሥሎች ፈልጋችሁ ተመልከቱ። እዚህ ጦማሬ ላይ ያቀረብኩትንም መመልከት ትችላላችሁ።
•••
ነገር ግን ይሄን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ጠ/ሚ/ዶኮ ዐቢይ አህመድ የሠረቱትን የእምዬ ምኒሊክ ሃውልት ተብሎ የቀረበን ካባ አቅርባችሁ እዩት። አገላብጣችሁ ተመልከቱት።  ወላሃንቲ መስቀል የለበትም። ዐቢይ አህመድ ፀረ መስቀል፣ ፀረ ኦርቶዶክስ መሆኑ ይታወቃል። እኔን አልገባ ያለኝ “የዲያቆን” ዳንኤል ክብረት እዚያ ቦታ ተቀምጦ እያሽቃበጠ፣ የታሪክ ተመራማሪ ነኝ ብሎ ታሪክ ሲጣመም እያየ ጮጋ ብሎ መቀመጥ ነው። መጠርጠር እንጀምር እንዴ? እኔ በበኩሌ ዳኒን በተመለከተ ወዳለተፈለገና አስደንጋጭ ወደ ሆነ  አቅጣጫ እየተገፋሁ እየሄድኩ እንደሆነ ይሰማኛል። ሩብ ጉዳይ ነው የቀረኝ። ቢያንስ ዳኒ በዚሁ ከቀጠለ በእኔ የተነሳ ዲቁናውን እንዳያጣ እሰጋለሁ።
• ሂ ፦ በትረ መንግሥታቸውን እንመልከት
•••
እምዬ ምኒልክ በትረ መንግሥት በእጃቸው ላይ አለ። በትረ መንግሥት። ይሄ ዲያቆን ዳንኤል ከአቢቹ ጋር ተመካክረው በአረቦቹ ብር ያሠሩት ሃውልት ግን የለውም። ሃውልቱ ለጠንቋዩ ታምራት ገለታ የቀረበ ምስል ነው ያለው። ካዳሚ ይመስላል። በፍጹም የንጉሡ ሃውልት አይመስልም።
• ሃ ፥  በዙፋኑ ስር የሚታዩ ሁለት ህፃናት 
•••
ይሄ በፍጹም በየትኛውም የእምዬ ምኒልክ ዙፋን ላይ የሚታይ ምስል አይደለም። አንዱን ህፃን በእጃቸው ሲያቀርቡ፣ አንደኛውን ደግሞ ሲገፉ ተደርጎ የተወከለ ምስል ነው። እናም ይሄም ንጉሡን አይወክልም። ይሄ የኢሉሚናንቲው ሰይጣን የዘንዶው ሃውልት ነው። የተኮረጀውም ከዚያው ከ666 ቱ ከዘንዶው ከሃውልቱ ነው። አቢቹ ኖቬል ያሸለማትም ይሄው ተግባሯ ነው። እናም በፍጹም ሃውልቱ የእምዬ ምኒልክን ስብዕና፣ ሃይማኖት አይወክልም። በጭራሽ፣ በጭራሽ።
•••
ሰውየው ግን በኬክ ውስጥ መርዝ በማቅረብ የተካነ ሰው ነው!
 
ዐቢይ አህመድ ስማርት ነው። ከምር አዛኝ ቅቤ አንጓችም ነው እስከየት እንደሚያደርሰው ባላውቅም፣ እንዴት እንደሚዘልቅበት ባላውቅም ሰውየው ግን በኬክ ውስጥ መርዝ በማቅረብ የተካነ ሰው ነው። እኛም ማድረግ ያለብን ስለ ኬኩ እያመሰገንን መርዟን ግን ራሱን ማስበላት ነው። ቤተ መንግሥቱ መታደሱ በራሱ ግሩም ነው። ይጨበጨብለታልም። ነገር ግን ይሄ ለእኔ ቶርታ ኬኩ ነው። ውስጡ መርዝ የታጨቀበት ቶርታ ኬክ ነው። ሲበዛ ፈጣን ብልጣብልጥም ነው።
•••
666 ጠቅልላ ቤተ መንግሥት ገብታለች። መጽሐፍ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።” ማቴ 24፥24 እንዲል እንደተመረጡ እንቆጥራቸው የነበሩት እነ ዲን ዳንኤል ክብረት በዚህ ርጉም ሴራ ውስጥ ተዘፍቀው ስናይ ቃሉ መፈጸሙን ከማድነቅ በቀር አናንጎራግርም።
•••
ከዚህ ተነስታችሁ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የነበሩ ጥንታውያን ቅርሶች፣ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች፣ መገለጫ ቅርሶች እንዴት እንደወደሙ መጠርጠሩ ብልህነት ነው። ዘንዶው በትክክል በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ዙፋኑን ዘርግቷል።
ወደ ኦሮምያ አርሲ ( አኖሌ )  እንለፍ!
የእምዬ ምኒሊክ የደጉ ንጉሥ ኢትዮጵያዊው መንፈስ ያወካቸው ዛራቸውን የቀሰቀሰባቸው እነ አባ ሜንጫ ጃዋር መሀመድና የወተር፣ የበደኖና የአርባ ጉጉው የዐማራ ደም መጣጭ ቫንፓየሩ የመንፈስ አባቱ ኦቦ ሜንጫ ሌንጮ ለታ ወደ አርሲ አኖሌ ፈርጥጠዋል። በዚያም ኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረ አብ ፈልስሞ በደረሰላቸው ድርሰት የመቐለዋ ህወሓት በመሶቦ ሲሚንቶ ጠፍጥፋ በሠራችላቸው የፈጠራ የተቆረጠ ጡት ሥር ሲያለቃቅሱ ውለው በመጨረሻም የትአባታቸው እንደገቡ ሳይታወቅ ቀርቷል።
••• በአዲስ አበባው የቤተ መንግሥት ምርቃት ላይ ያልተገኙት የክልል መንግሥታትና የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከአሁን አለመታወቃቸው ታውቋል።
•••
• የዐማራ፣ • የደቡብ • ጋምቤላ • የአፋር • የሱማሌ
• የቤንሻንጉል እና • የሐረሬ ክልል መሪዎች መገኘታቸው ተነግሯል
••• ህወሓት ይሄን ከማይ ብላ በመቐለ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጣለች። በቀለ ገርባ የት እንዳለ አልታወቀም። ድምጹ ጠፍቷል። ህዝቅኤል ጋቢሳ የኦሮሞን ከውኃ መፈጠር ምርምር ሊያደርግ ቢሾፍቱ ሆራ አርሴዲ ሄዷል። ዶር ገመቹ ውኃ ተረጭተው ዐማራ የሆኑ ኦሮሞዎችን ቁጥር ዳታ ለመሰብሰብ ቦሩ ሜዳ ሄደዋል። 
• እነ እስክንድር ነጋ ደግሞ ለጥቅምት ሁለት አዲስ አበባን የአዲስ አበባውያን ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል።
•••
የኢትዮጵያውያኑ
• የአጼ ቴዎድሮስ አምላክ
• የአጼ ዮሐንስ አምላክ
• የአጼ ሚኒልክ አምላክ
• የአጼ ኃይለ ሥላሴ አምላክ
★ በያለንበት ይጠብቀን።
ሻሎም !  ሰላም !  
መስከረም 29/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic