>

በአኖሌ ተረክ ሀገር መምራት ፈፅም አይቻልም!!! (የሽሃሳብ አበራ)

በአኖሌ ተረክ ሀገር መምራት ፈፅም አይቻልም!!!
የሽሃሳብ አበራ 
 
“መንገድ መዝጋት፣ ማቃጠልና ማፈናቀል የአኖሌ ትርክት ውጤት ስለሚሆን ቀድሞ መዘጋጀት ያስፈልጋል!”
ከአሁን በኃላ የአኖሌ የጭፍጨፋ ታሪክ ውሸት ነው ማለት አይጠቅምም፡፡ ከ 160 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከ5 ሚሊየን አይበልጥም፡፡ በወቅቱ የኦሮሞ ህዝብ ከአንድ ሚሊየን ሊዘል አይችልም፡፡ ምኒሊክ ከአንድ ሚሊየኑ  5 ሚሊየኑን ጨፍጭፏል፡፡ እንደዚህ ተብሎ ብሄርተኝነት ተሰርቷል፡፡ እንዲህ አይነት ብሄርተኝነት  አደጋው ጨቋኝ ተባለው አካል ሳይሆን ተጨቁኛለሁ ለሚለው ይሆናል፡፡
ምክንያቱም፦
1) ብሄርተኝነቱ ውሸት ስለሆነ ያለምክንያት እንዲኖር ስለሚያደርግ ደቦዊ(መንጋዊ)አስተሳስብን ያሰርፃል
2) ተሸናፊነትን  ስለሚያወርስ ግጭት፣ መጠራጠር ፣ሁሌም አለ፡፡
3) በውሸት የተገነባ ብሄርተኝነት ዴሞክራሲያዊ መሆኑ ይቅርና የማይመለስ ጥያቄ ያዝላል፡፡ ስለዚህ የአኖሌ ብሄርተኞች መመለስ አይቻልም፡፡
 ለምሳሌ፦
 አክሱም ተነቅሎ በአኖሌ ቢተካ፣ጣና እትጌ ጣይቱ መናፈሻ ላይ ኢሬቻ ቢከበር፣ምስራቅ አፍሪካ የአንድ ዘውግ ግዛት ብቻ ቢሆን እርካታ ብሎ ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ግጥሚያው ካለፈ ታሪክ ጋር ነው፡፡ ያለፈ ታሪክ ይሁንም አይሁንም ሊታረም አይችልም፡፡ የእነ አኖሌ ብሄርተኞች  ቅራኔም ኢ-ተፈጥሮአዊ መልክ አለው፡፡
ጆሴፍ ስታሊን በተግባር 15 ሚሊየን ሩሲያውያን፣ ማኦ ዘዱንግ 20 ሚሊየን ቻይናውያን፣ አዶልፍ ሂትለር አይሁዳውያን፣ጂፕሲ፣ፖሊሽን በአጠቃላይ 10 ሚሊየን አካባቢ ህዝብ ጨፍጭፈዋል፡፡ ግን ቻይና የማኦ ጭፍጨፋ ላይ አልቆመችም፡፡ ሩሲያም ከስታሊን ጭፍጨፋ ላይ ቆማ ብታላዝን ኑሮ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ገብታ በአሜሪካ እጅ እንደገና ትሰራ ነበር፡፡
ጃፓን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሄሮሽማ እና ናጋሳኪ ግዛቶች  በአሜሪካ ጦር ሰዎቿ ብቻ ሳይሆን መሬቷ ሁሉ ተቃጥሏል፡፡ ግን ጃፓን ሄሮሽማ ላይ ቁማ አሜሪካ ላይ አልቆዘመችም፡፡ የጃፓን ንግድ 30% ገበያው አሜሪካ ነው፡፡ እነ ቲዮታ የመሳሰሉ የተሽከርካሪ ኩባንያዎች የአሜሪካ ስጦታዎች ናቸው፡፡
 የአኖሌ ግን አንድ በተግባር ላልተፈፀመው 160 ዓመት ወደ ኃላ እየተመለሱ በበቀል ማንባቱ  ትውልድን በዛሬው ላይ ትናንትን እንዲኖርበት ያደርጋል፡፡ ይህ ሁሉ ይቅር ምኒሊክ የተባለውን ያህል ቢጨፈጨፍ እንኳን በሀቅ ከተሄደ 150 ዓመት ወደ ታች ተንሸራቶ ማልቀሱ እርባና ቢስ ነው፡፡
 በእርግጥ የአኖሌ ተረክ መነሻው ምኒሊክ 5 ሚሊየን ጨፍጭፎ ወረረኝ እንጂ እኔ በራሴ ሀገር ነበርኩ የሚል መነሻ አለው፡፡ ስለዚህ አኖሌን ማንገስ ነፃይቱ  ኦሮሚያን የመፍጠር ርዕይ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል አዲስ አበባ፣ ሀይማኖቶች፣ ደቡብ ውስጥ ያሉ ብሄር ብሄረሰቦች ዘውጋዊ ክልል እንዲሆኑ እነ አኖሌ ብሄርተኞች የሚቀሰቅሱት፡፡
የእነ አኖሌ ብሄርተኝነት ከአኖሌ ተረክ ውጭ እንዳይኖር ተደርጎ ተሰርቷል፡፡ አኖሌ ለኦነጋዊ ብሄርተኝነት የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ኦዴፓም ከመሃል ፖለቲካው ወደ ዳር እየወጣ ነው፡፡ ኦዴፓ መንግስት ሆኖ እንኳን በአኖሌያዊ ትርክት ምክንያት ተቅበዝባዥ እና ምክንያት አልባ ሆኗል፡፡ ይህ ትርክት ደግሞ ወይ ከመሰረቱ ካልተሻረ አሊያም ግንጠላ ካልተፈፀመ በስተቀር አብሮ ይኖራል፡፡
1) ስለዚህ መንገድ መዝጋት፣ ማቃጠል፣ ማፈናቀል፣ የአኖሌ ትርክት ውጤት ስለሚሆን ቀድሞ መዘጋጀት ያስፈልጋል
2) በደንብ መደራጀት እና ከፊስቡክ ጫጫታ ባሻገር መሬት ላይ የሀገር ህልውናን ለማዳን መደራጀት ያስፈልጋል
3) ውጮቹ በአኖሌ ብሄርተኞች ተስፋ እየቆረጡ ስለሆነ  ከፍ ብሎ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት ካልተቻለ በአኖሌ ተረክ ሀገር መምራት ፈፅም አይቻልም፡፡
Filed in: Amharic