>
8:39 am - Saturday November 26, 2022

ኦሮሞን በጭራቅነት ኦሮሚያን ደሞ በገሀነም እሳትነት የሚያስፈርጅ እንቅስቃሴን እቃወማለሁ...!!! (ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና)

ኦሮሞን በጭራቅነት ኦሮሚያን ደሞ በገሀነም እሳትነት የሚያስፈርጅ እንቅስቃሴን እቃወማለሁ…!!!
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
* ትላንት ነፃ አዉጥቸሀለዉ ዛሬ ልዝረፍህ ንብረትህን ላዉድም መንገድ ልዝጋ ያ ካልሆነ ግን ዘቅዝቄ እሰቅልሀለዉ የሚል ቡድን በፍፁም የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ሊሆን አይችልም…!!!
“እኔ ኦሮሞ ነኝ! በኦሮሞ ስም ከሰዉነት ወርዶ የሚንቀሳቀስ ሰዉ ሳይ እናደዳለሁ…፡፡  አሁን እየታየ ያለዉ ኦሮሞን በጭራቅነት ኦሮሚያን ደሞ በገሀነም እሳትነት የሚያስፈርጅ እንቅስቃሴን እቃወማለሁ…፡፡ ትላንት ነፃ አዉጥቸሀለዉ ዛሬ ልዝረፍህ ንብረትህን ላዉድም መንገድ ልዝጋ ያ ካልሆነ ግን ዘቅዝቄ እሰቅልሀለዉ የሚል ቡድን በፍፁም የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ሊሆን አይችልም…፡፡
በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተጫነዉ ድህነት መሆኑ እየታወቀ በስንት ብድር የተገነባን ፋብሪካ ማጋየትና መዝረፍ ለኦሮሞ ጠላት መሆን እንጂ ተቆርቋሪነት አያስብልም…፡፡
ኦሮሞ በራሱ ትልቅ ታሪክና ቱፊት ያለዉ ህዝብ ሆኖ ሳለ ምክንያት እየፈለጉ ከሌሎች ወንድሞቹ  ጋር በማናከስ ራሳቸዉን በ ፓለቲካ ንግድ ላይ ያሰማሩ ግለሰቦችን መንግስት ሀይ ሊል ይገባል፡፡
“በነዚህ ልጆ እድሜ አባቶቻችን ዶሮ ወይም ፍየል ለምግብ ሲያርዱ ዐይናችን አንገልጥም፤ ፍርሀት ሳይሆን ነፍስ ስለሆኑ።የእንስሳዎቹ ህይወት ሲጠፋ ለማየት እንኳን የማይደፍር ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ጨካኝ ህሊና ስለሌለን ነው። ሰው በአጋጣሚ ሞቶ እንኳን አስከሬኑ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ቤተሰብ ሲያለቅስ እንዳንሰማ ቤት ውስጥ እንደበቅ ነበር። ባጋጣሚ እንኳን ለቅሶውን ከሰማን የተመለከትነው የቤተሰብ ሀዘን እያንዳንዷን የለቅሶ ቃላት፣ የፊታቸው ገፅታና ድርጊት እያሰብን ለወራት ያህል ከሌሎች ልጆች ስንገናኝ በዛ ቤተሰብ ሀዘን ዙሪያ እያወራን እንላቀሳለን።
 ሌት አልጋ ሆነን እንቅልፍ እስኪመጣ እያምሰለሰልን እናነባለን። በጥቅሉ ያየነው ሁሉ ለዓመታት ቢሆን ከጭንቅላታችን አይጠፋም። የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ስሜት የትም ቦታ እንደዚህ ነው። ይኼ ሰብአዊነት ነው! ተመልከቱ በተፈጥሮ የሰው ጨካኝ አይደለም። ነገር ግን ጨካኝ እንድትሆን የሚያለማምድህና የሚያበረታታህ አካል ካለ ጭካኔን ትማራለህ። እኔ በጊዜ ሂደት ዶሮም፣ ፍየልም ማረድና መበለት ለመድኩ ።
የአሁን ልጆች ደግሞ በየሄዱበት፤ በሚያድጉበት አካባቢ ሁሉ ገና ከጨቅላ እድሜያቸው ጀምሮ ከእንስሳት አልፎ በሰው ህይወት ላይ አረመኔያዊ ተግባር እንዲፈፅሙ የሚያለማምዱና የሚያበረታቱ ነገሮችን በጥላቻ መልክ ያያሉ፣ ይሰማሉ፣ ይሰበካሉ። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ለስርዓቱና ለሀገር ደንታ የሌላቸው ግለሰቦች ናቸው ።
አሁን ላይ እኔ በአደግኩበት ተመሳሳይ ቦታ እየሆነ ያለው ዘግናኝ ነገር ህፃናትንና ለጋ ወጣቶችን ከተፈጥሮአዊ (natural) ሰብአዊ ማንነታቸው ያፈነገጠ ስሜት እንዲሰማቸው እና የትውልድ ኪሳራ በፍጥነትና በብዛት እንዲፈጠር እየሰሩ ያለ ውጫዊ (nurturing) ጨካኝ አካላትና ሱሶች መኖራቸውን በግልፅ ያሳያል።
ስለዚህ ሀገርን ትውልድን ለማዳን ሲባል ለጊዜው ተጠያቂ አካላትን ለይቶ መንግስት እርምጃ መውሰድ አለበት። በዘላቂነት ደግሞ መንግስት መሰረታዊ ችግሮችን ተረድቶ የትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ ፖሊሲዎችን ማስተካከል አለበት።
ምሁራን ጉዳዩ የትውልድን ማዳን ጥሪ እንደሆነ አስበንና ትኩረት ሰጥተን የመፍትሄ ግብአቶችን ማቅረብ አለብን።መላው የኢትዮጵያ ወላጆች ለልጆቻችሁ አስተዳደግ ትኩረት መስጠታችሁን እንደ ቀላል አትዩት!
ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቃት !!!
Filed in: Amharic