>
5:13 pm - Friday April 20, 3584

የኢትዮጵያ መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው!  (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

 

የኢትዮጵያ መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው!

 

 

ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

 

ዕድሜ ልካችንን በመከራ ውስጥ አልፈን ስናበቃ፥ የብርሃን ጭላንጭል አሳይቶ እንቁልጭልጭ የሚጫወትብን ጨካኝ አምላክ የለንም። እግዚአብሔር በምድራችን የጀመረውን መልካም ሥራ ዳር ሳያደርስ መንገድ ላይ አይጥለንም።  

 

እግዚአብሔር ያያል። 

እግዚአብሔር ይፈርዳል። 

ፈጥኖ ይፈርዳል። 

በቀናት ውስጥ ክብሩን ይገልጣል።

ዲያብሎስ የደገሰልን የዕልቂት እኩይ ሤራ ይገለበጣል። ኢትዮጵያ ወጀቡን አልፋ ትሻገራለች።  ታበራለች። 

መከራ ያየነው ከዓለም በኃጢአት አንደኛ ስለሆንን አይደለም።  የቃል ኪዳን ሀገር የሆንነው ከዓለም በፅድቅ አንደኛ ስለሆንን አይደለም።  ያለፈው መከራችንም ሆነ የሚመጣው ጉብኝታችን ምክንያቱ የኢትዮጵያ አምላክ ክብር እንዲገለጥብን ብቻ ነው።  

ጠላት ለኢትዮጵያ መበታተን ያጠመደው ክፉ ወጥመድ ለእኛ ጭንቀት ቢሆንብንም፥ ለፈጣሪ ክብሩን እንዲገልጥ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ምድር ሁሉ በኢትዮጵያ አምላክ አለ እስኪል ድረስ ሥራውን ሊሰራ ፈጣሪ ራሱ ይወርዳል። ወጥመዱን ይሰብራል። ኢትዮጵያንም ያስመልጣል። 

ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡

  • የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ
  • አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
  • ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
Filed in: Amharic