>
4:28 am - Friday July 1, 2022

በአሰቃቂ ሁኔታ ቄሮ በተባለው የጃዋር መንጋ የተፈጸመ ግብረ-ሽበር !!! (ታደለ ጥበቡ)  

በአሰቃቂ ሁኔታ ቄሮ በተባለው የጃዋር መንጋ የተፈጸመ ግብረ-ሽበር !!!

 

ታደለ ጥበቡ  
እንደ ሮይተርስ ዘገባ 67 ሰዎች ሞተዋል።ከእነዚህ መካከል 5ቱ የፖሊስ አባላት ናቸው።እንደ ኒዮር ታይምስ ዘገባ ደግሞ 213 ሰዎች ቆስለዋል።አካልጉዳተኛ ሆነዋል።
 
ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. የጃዋር መሐመድ መንግሥት ወታደሮች [ቄሮዎች] የጋሞ ሴት ልጅ ጡት እንደቆረጡ የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃ እጃችን ገብቷል። የሰው ፍጡር የሆነ  በሰው ልጅ ላይ እንዲህ አይነት ጭካኔ ሲፈጸም እንደማየት ለአእምሮ የሚከብድ፣ ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ   ዘግናኝ ነገር የለም። ይህ የጃዋር መሐመድ መንግሥት ወታደሮች ጭካኔ  ዛሬ ፍትሕ ባይገኝም ትውልድና ታሪክ ይፋረድ ዘንድ በዐፄ ዐቢይ አሕመድ ዘመን የጃዋር መሐመድ ወታደሮች የሴት ልጅ ጡት መቁረጣቸውን የሚያሳየውን ይህን ዘግናኝ ታሪክ ግን ለታሪክ መዝግበን እናስቀምጠዋለን። 
 
ተጨማሪ መረጃና ማስረጃ ያለው የዘር ጭፍጨፋ
ማስረጃ.1፦ ምስራቅ ሀረርጌ በሮዳ አቶ ደረጀ ኃይሉ የተገደለው በመጀመሪያ በዱላ ከቀጠቀጡ በኋላ ብልቱን ቆርጠው አፉ ውስጥ በመክተት ነው።
ማስረጃ.2. ዶዶላ ላይ ዘምሼ ሲሳይ የተገደለችው ጡቷን በመቁረጥ ነው።ዘምሼ የሁለት ህጻናት ልጆች እናት መሆኗ ተረጋግጧል።
ማስረጃ.3. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ካራሚሌ እና ቦረዳ መሃል በምትገኝ መዲሳ በምትባል አንድ የገጠር መንደር ውስጥ የሚኖሩ 8 ክርስትያን አማራዎች ተገደው እምነታቸው እንዲቀይሩ ተደርገዋል።
ማስረጃ 4. ሰበታ “ወለቴ” በሚኖሩ የጋሞ ተወላጆች ላይ በተፈጸመው የፓስተሮችና የሌሎች ግድያ ሁለት እጃቸውን በማሰር መሬት ላይ ጥለው እንደ በግ በማረድ ነው የገደሏቸው።
የአገዳደል ሁኔታ
ግድያው ብሔርና ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ከ67ቱ ሟቾች13ቱ በጥይት ተገለዋል።የተቀሩት የአገዳደል አይነት ይለያያል።
1.በድንጋይና በዱላ እንደ ዕባብ በመቀጥቀጥ፣
2.በቆንጨራ ሆዳቸውን መተርተር፣በጦር ልባቸውን መውጋት፣
3.በገጀራ አንገታቸውን እና እጃቸውን መቁረጥ፣
4.ከገደሉ በኋላ መንገድ ላይ እየጎተቱ መጨፈር፣ፎቶ መነሳትና ሬሳውን በደጋጋሚ በድንጋይ መውገር፣
5.የወንድ ብልት እና የሴት ጡት መቁረጥ፣
6.በግድ ኃይማኖታቸውን ማስቀየር፣
7.ከነነፍሱ ቤት ዘግቶ ማቃጠል፣
በመጨረሻም ንብረታቸውን የሚችሉትን ዘርፈው ማቃጠል።
በጃዋር መንጋ አሸባሪዎች በኦሮሚያ ከተገደሉት መካከል፦ 
1.ወ/ሪት ዘኑሼ ሲሳይ- ባሌ ዶዶላ
2.አቶ ግርማ ተስፋዬ -ባሌ ዶዶላ
3.አቶ ዝናብ ጌታሁን- ባሌ ዶዶላ
4.አቶ አነጋግር ደሴ- ባሌ ዶዶላ
5.ወጣት እሸቱ ተስፋዬ – ባሌ ዶዶላ
6.ኃይሉ አሰማረ-ባሌ ዶዶላ
7.ምህረት ደጀኔ-ባሌ ዶዶላ
8.እሸቱ ግርማ-ባሌ ዶዶላ
9.አቶ መስፍን አለማየሁ-(ም/ሀረርጌ በሮዳ)
10.ደረጀ ኃይሉ- (ምስራቅ ሀረርጌ በሮዳ)
11.አቶ ደመና ኃይሉ- (የኃይሉ ወንድም)
12.ወላንሳ ፍቅሬ- (የአቶ ደመና ሚስት)
13.ወጣት እሱባለው-(ድሬዳዋ ገንደቆሬ ሰፈር)
14.አቶ ሞረዳ-( አምቦ)
15.አቶ ገላሁን- (ወለቴ)
16.ሰመር ኑሪ – ናዝሬት
17.ፍጹም ወጋየሁ – ናዝሬት
18.አቢቲ ታምራት – አርሲ ኮፈሌ
19.አቶ ታምራት ጸጋዬ – አርሲ ኮፈሌ ልጃቸውም የተገደለ
20.አብርሃም ክንዴ – ድሬዳዋ
21.ትዕግስት – ገንደሀራ ናዝሬት
22.ጥቅምት 12 እና 13 በሰበታ “ወለቴ” በሚኖሩ የጋሞ ተወላጆች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በአጠቃላይ 8 ንጹሃን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል።ቁጥራቸው ከ2 ሺህ የምልቁት ደግሞ ለዓመታት ከኖሩበት ቤታቸው ተፈናቅለው አሁንም ሜዳ ላይ ይገኛሉ።
በጥቅሉ እንደ ሮይተርስ ዘገባ 67 ሰዎች ሞተዋል።ከእነዚህ መካከል 5ቱ የፖሊስ አባላት ናቸው።እንደ ኒዮር ታይምስ ዘገባ ደግሞ 213 ሰዎች ቆስለዋል።አካልጉዳተኛ ሆነዋል።
በተስፋዬ ገብረአብን ልብወለድ አኖሌ ላይ የተቆረጠ ጡት ሐውልት ያቆሙትና መቆሙን የደገፉ የኦሮሞ ብሔርተኞች  የፎቶና ቪዲዮ ማስረጃ ላለው  በጃዋር መሐመድ ወታደሮች ጡታቸውን  ለተቆረጡ  የጋሞ እናቶች ሐውልት ያቆሙላቸው ይሆን?
“የራሔልንም ዕንባ የሰማህ አምላክ የእኛንም ዕንባ ስማ”
Filed in: Amharic