>

አገሩም ምድሩም የኛ ነው ጠላቶቻችንን ጠራርገን እናስወጣለን.....!"  የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር

አገሩም ምድሩም የኛ ነው ጠላቶቻችንን ጠራርገን እናስወጣለን…..!” 

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር
ያሬድ ሃይለማሪያም 
“ጀዋርም ልጃችን ነው ዐቢይም ልጃችን ነው እኛን እያባሉን ያሉት ነፍጠኞች ናቸው ኦሮሞም እራሱን ከወራሬዎች እንዲከላከል መሣሪያ እናስታጥቃለን አገሩም ምድሩም የኛ ነው ጠላቶቻችንን ጠራርገን እናስወጣለን…..!” ይሄንን ያለው ኦሮሚያ የሚሉት ፖሊስ ኮሚሽነር ነው፡፡
—-
ከዚህ በታች የምታዩት ቪዲዮ ላይ የኦሮሚያ ክልል የፖሊስ ኮሚሽነር እንደሆኑ የተገለጸው ግለሰብ በአዳማ ከተማ ወጣት ቄሮዎችን ሰብስበው እጅግ አስደንጋጭ የሆኑ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ንግግራቸው በኦሮሚኛ ቢሆንም በታመነ ሰው በትክክል ተተርጉሟል። ባለስልጣኑም ለሰበሰቧቸው ሰዎች ከዚህ የሚከተሉትን መመሪያዎችና መልዕክት አስተላልፈዋል፤
+ በአዳማ/ናዝሬት ያሉትን ቄሮዎች፤ እናንተን ጠመንጃ እናስታጥቃችኋለን
+ ከፋኖ ላይ ግን ጠመንጃ ቀምተን ወደ እስር ቤት እናጉራቸዋለን
+ ቄስ ትሁን ጳጳስ ቀጥቅጠን እስር ቤት እናስገባቸዋለን
+ የቤተክርስቲያን ደውል ደውለው ሕዝቡን እንዲሰበሰብ ያደረጉ ቄሶችን ጠራርገን ወደ እስር ቤት እናስገባቸዋለን
+ ይሄ የኦሮሞ ሀገር ነው ማንም እንደፈለገ መፈንጨት አይችልም
+ ከአሁን በኋላ አንድም ፋኖ እናንተን አይተናኮላችሁም
ጎበዝ ወዴት እየሄድን ነው። የዛሬ አመት ቡራዩ ላይ ሰው ሲጨፈጨፍ እንዲሁ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ለምን የድረሱልን ጥሪ ተደርጎላችው እያለ ጭፍጨፋውን አላስቆማችሁም ሲባሉ ባለሥልጣናቱ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ ተራራማ ስለሆነ የፖሊስ ኃይል የሚችልበት አይደለም የሚል ስላቅ መሰል ለመገናኛ ሚዲያዎች መስጠታቸው ይታወሳል። ይህ የሚያሳየው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች የተደገፈ ጭምር መሆኑን ነው። ይህን የሚያሳዩ ሌሎች መረጃዎችም እየደረሱን ነው።
ክልሉን እየመራ ያለው ማን ነው? ከዚህ ሁሉ ጥፋት ጀርባ ያለው ጃዋር መሃመድ? ወይስ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ እያሉ ስለ ሰላም እና እርቅ የሚደሰኩሩት የኦዴፓ አመራሮች?
አሁንም ወደ ከፋ እልቂት ሳይኬድ በፊት መንግስት እንደ እነዚህ ያሉ ኃላፊነት የጎደላቸው የመንግስት ባለሥልጣናትን ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል።
Filed in: Amharic