>
5:13 pm - Wednesday April 18, 4925

በዶዶላ  በቄሮዎች  ጡታቸው የተቆረጠው የሁለቱ እኅትማማቾች ግፍ ተመዝግቦ ይቀመጥ!  (አቻምየለህ ታምሩ)

በዶዶላ  በቄሮዎች  ጡታቸው የተቆረጠው የሁለቱ እኅትማማቾች ግፍ ተመዝግቦ ይቀመጥ! 
አቻምየለህ ታምሩ
ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. የጃዋር መሐመድ መንግሥት ወታደሮች [ቄሮዎችን ማለቴ ነው] በዶዶላ የሁለት እኅትማማቾችን ጡት መቁረጣቸውን  እነሆ የዐይን ምስክሩ ይናገራል! ይህ ለኔ በግል ከተላከው  የጋሞ እናት ጡት መቆረጡን ከሚያሳየው ዘግናኝ ቪዲዮ ተጨማሪ ነው።
በጃዋር መሐመድ መንግሥት ወታደሮች ጡታቸው የቆረጠውና  በሁለቱ  እኅትማማቾች  ላይ  የተፈጸመው  ጭካኔ  ከጡት ቆራጮቹ  ወገን ከቆመው ከዐቢይ አሕመድ አገዛዝ  ፍትሕ ባያገኝም  ወደፊት ትውልድና ታሪክ ይፋረድበት  ዘንድ  በሰባተኛው ንጉሥ በዐፄ ዐቢይ አሕመድ ዘመነ መንግሥት በተለዋጩ መንግሥት በጃዋር መሐመድ ወታደሮች ጡት መቆረጡን  የሚያረጋግጠው ይህ የዐይን ምስክሩ ማስረጃ ለታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጣል።
በተስፋዬ ገብረአብን ልብወለድ አኖሌ ላይ የተቆረጠ ጡት ሐውልት ያቆሙትና መቆሙን የደገፉ የኦሮሞ ብሔርተኞች  እንዲህ የዐይን ምስክር ማስረጃ ላለው በጃዋር መሐመድ ቄሮዎች  ጡታቸውን ለተቆረጡ እኅትማማቾች ሐውልት ያቆሙላቸው ይሆን?
Filed in: Amharic