>

የአሰቦት የሴት መነኮሳቶች ገዳም በድንጋይ ሲደበደብ አደረ!!! (ኢትዮ 360)

የአሰቦት የሴት መነኮሳቶች ገዳም በድንጋይ ሲደበደብ አደረ!!!
(ኢትዮ 360 )
በአሰቦት የሴት መነኮሳቶች ገዳም በድንጋይ ሲደበደብ ማደሩ ተሰማ።
ኢትዮ 360 ወደ ስፍራው ደውሎ ያነጋገራቸው መነኮሳት ለሚመለከተው አካል የአስቸኳይ የድረሱልን ድምጻቸውን አሰምተዋል። መነኮሳቱ እንደሚሉት ምሽት 2 ሰአት ከ30 አካባቢ የጀመረው ድንጋይ ውርወራ እስከ ምሽት አራት ሰአት ድረስ ዘልቋል። በመሃሉም ለትንሽ ሰአታት ካቆመ በኋላም በድጋሚ ከለሊቱ 10 ጀምሮ የድንጋይ ውርወራው መቀጠሉን ይናገራሉ በፍርሃት ውስጥ ያሉት መነኮሳት።
እንደ መነኮሳቱ አባባል በገዳሙ ላይ ድንጋይ ውርወራ ብቻ ሳይሆን የሴቶች መነኮሳትን ገዳም በር ሰብሮ ለመግባት ሙከራ ነበርም ይላሉ። የአንዷን መነኩሴ ቤት ለመስበር ሙከራ ማድረጋቸውንም በመጠቆም።
ገዳሙ ከባድ አደጋ አንዣቦበታል የሚሉት መነኮሳቱ በአካባቢው የጸጥታ ሃይል አለመሰማራቱ ደግሞ ችግሩን የከፋ አድርጎታል ይላሉ።
አልፎ አልፎ አካባቢውን ለመቃኘት የሚመጣውም የመከላከያ ሃይል ትንሽ አሰሳ አድርጎ ከመመለስ ውጪ ቋሚ ጥበቃ ሲያደር አይታይም ይላሉ መነኮሳቱ ።አነጋጉ ላይ ድንጋይ ውርወራው ትንሽ ጋብ ቢልም ቀጥሎ የሚከሰተው ነገር ስለማይታወቅ ስጋት ውስጥ ነን ብለዋል። የክልሉ መንግስትም ሆነ የሚመለከተው አካል በገዳሙ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለማስቆም አስቸኳይ መፍትሄ ይስጠን ሲሉ መነኮሳቱ ተማጽነዋል።
በተለይ በአቡነ ሳሙኤል አንድነት የሴት መነኮሳት ገዳም ላይ ሲፈጸም ያደረው የድንጋይ ውርወራ የተደቀነውን አደጋ አመላካች ነው ስለዚህ የሚመለከተውም አካል ሆነ ኢትዮጵያውያን ከጎናችን
ሊቆሙ ይገባል ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።ይሄ ዜና በተጠናቀረበት ወቅትም መነኮሳቱ በአንድ ላይ በአቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው ጸሎታቸውን እያደረጉ ቀጣይ ምን ይሆናል የሚለውን በስጋት እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል።
Filed in: Amharic