>
5:14 pm - Sunday April 20, 3434

ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ሊሰየም ይገባል! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ሊሰየም ይገባል!
ያሬድ ሀይለማርያም
በቡራዩ፣ በሲዳማ፣ በቅማንት፣ በጉሙዝ እና በቅርቡ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተፈጸሙትን የመብት ጥሰቶች የሚያጣራ ገለልተኛ ቡድን ሊሰየም ይገባል። መንግስት እንዲህ ያሉ ችግሮችን አጣርቶ ትክክለኛ ሪፖርት ለማቅረብ አቅም ወይም ፍላጎቶ የሌለው መሆኑን በተደጋጋሚ በተከሰቱት ጥሰቶች አሳይቷል። ፖሊስ እና ዓቃቤ ሕግ ሥራቸውን በአግባቡ እየሰሩ አይደለም። በአዲስ መልክ እየተቋቋመ ያለው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ብቻውን እነዚህን ሁሉ ጥቃቶች በአጭር ግዜ ሊያጣራ አይችልም።
በእነዚህ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ተገድሏል፣ ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ ቤት ንብረታቸው ተዘርፎ ወድሟል። ነገም ተመሳሳይ ጥቃቶች ላለመፈጸማቸው ምንም ዋስትና የለም።
መንግስት፤ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን በማቋቋም እና ወንጀል ፈጻሚዎቹንም ለፍርድ በማቅረብ በሕግ የተጣለበትን ግዴታ በአፋጣኝ ሊወጣ ይገባል።
+ ፍትህ በቡራዩ በግፍ ለተገደሉ፣
+ ፍትሕ በሲዳማ በግፍ ለተገደሉ፣
+ ፍትሕ በቅማንት በግፍ ለተገደሉ፣
+ ፍትህ በቤኒሻንጉል ጉምዝ በግፍ ለተገደሉ፣
+ ፍትህ በቅርቡ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻን፤
እነዚህ ጥቃቶች በጥቂት ቡድኖች አቀነባባሪነት እና ተደጋጋፊነት እየተፈጸሙ እነሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። መንግስት ፍትህን እስኪሰጥ እና ወንጀል ፈጻሚዎቹን ለፍርድ እስከሚያቀርብ ድረስ በየቀኑ ስለ ፍትህ እንጮኻለን።

ፍትሕ፣ ፍትሕ፣ ፍትሕ፣ ፍትሕ፣ ፍትሕ

Filed in: Amharic