>

በአዲስ አበባ ባንዲራ ይዞ መታየት ለፖሊስ ዱላና እስር እየዳረገ ነው!!! (የአሃዱ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ትእግስት ታንቱ)

በአዲስ አበባ ባንዲራ ይዞ መታየት ለፖሊስ ዱላና እስር እየዳረገ ነው!!!
የአሃዱ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ትእግስት ታንቱ
” ባልደራስ ነው የላከሽ! ” 
መርማሪ ፖሊስ
     ጥዋት 3:00 ገደማ ቢሮ ልገባ ታክሲ ይዤ ፒያሳ ደረስኩ ኦይል ሊቢያ አካባቢ ግርግር ተፈጥሮ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል ። እኔም ሰዎች ወደ ተሰበስቡበት ተጠጋው ከዚያ ማህል ላይ አንድ ወጣት እድሜው በግምት 28 – 30 የሚሆነው ኮከብ የሌለውን ባንዲራ ይዞ ይገኛል ይህን ወጣት “ባንዲራ ለምን ያዝክ?” ከዚያሚሉ ከፖሊሶች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ነው ግርግሩ የተፈጠረው ።
     ፖሊሶቹም ልጁን ” ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንሂድና እዛው እናወራለን ” ሲሉት ” አልሄድም ምንም አላደረኩም ” በሚል ነገሩ እየተካረረ መጣና ወጣቱን መደብደብ ጀመሩ ቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች “አትመቱትም” በሚል ተከራከሩ ከዛም ከዚህም ፎቶ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ አይናቸው ያረፈው እኔ ላይ ሆነ ሶስት ፖሊሶች መጥተው ” ፎቶ ማንሳት ወንጀል ነው አንቺም ትታሰርያለሽ! ወደ ፖሊስ ጣቢያ ትሄጅያለሽ!” ብለው አዋከቡኝ ። እየገፈተሩና እየጎተቱም ወደ መኪናቸው አስገቡኝ ።
   ባንዲራ የያዘውን ወጣትና  ኔን ይዘው ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ወዳለው ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱን ።ከዚያም በቁጥር 6 የሚሆኑ ፖሊሶች እየተቀባበሉ ክፉኛ ደበደቡት! ወደ እኔም ዞረው ሁለቴ በጥፊ ከመቱኝ በኋላ ” ሴት መሆንሽ ነው ያተረፈሽ! ” ብለውኝ ተበታተኑ።
መርማሪ ፖሊስ ወደ ውስጥ እንድገባ አዞኝ ገባሁ፣ አንዱ መጥቶ ” ባልደራስ ነው የላከሽ! ” ሲላት ሌላኛው ደግሞ ” ልታስበጠብጪ ፈልገሽ ነው!” ብለው ያነሳውትን ፎቶ አጠፉ። የማስጠንቀቂያ አይነት ሰተውኝ ተለቀቅኩ። ወጣቱ ላይ የሚደርሰውን መገመት ይቻላል።
Filed in: Amharic