>

ውርደት እንደማንነት (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)

ውርደት እንደማንነት

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

አንድ የትግሬ ተረት ብዘመነ ግርምቢጥ ማይ ናዓቅብ ይላል፤ በዘመነ ተገላቢጦሽ ዝናብ ወደላይ ይዘንባል፤ ማለት ነው መሰለኝ፤ የአጥቢያ ዳኛ ንጉሥ ፕሬዚደንት ተባለ፤ አንበሳው ጅብ ተባለ፤ አርበኛው ባንዳ፣ ባንዳው አርበኛ ተባለ፤ እግዚአብሔር የሾመው ተሻረ፤ ሺፍታ የጎለተው ነገሠ፤ ገንዘብ ያለው ጸደቀ፤ ደሀው ተኮነነ፤ መኮላተፍ ባህል ሆነ፤ እናት፣ አባት፣ ወንድም፣ እኅት የሚሉ ቃለት ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተሰርዘው ፋዘር፣ ማዘር፣ በራዘር፣ ሲሰተር በሚባሉ ተተክተዋል፤ የረከሱና የተዋረዱ ቃላት ሀሳቦችንም አዋረዱ፤ የክልል ‹‹መንግሥት››፣ የክልል ‹‹ፕሬዚደንት››፣ የመንደር ‹‹ሕገ መንግሥት››፣ ‹‹ዩኒቨርሲቲ››… ወዘተ. ከሁሉም በላይ ‹‹ሰው›› የሚለው ቃል ከጥቅም ውጭ ሆነና እንእንስሳ ተበታተንን፤ ዳዊትን እንደገና ልጥቀስ፤ ‹‹ሰብእሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ፤ ወኮነ ከመ እንስሳ ዘአልቦ ልብ፤› ።

Filed in: Amharic