>
5:18 pm - Monday June 15, 3891

የወቸገሉ ግንብ እና የ"ጉዛራ"ግምብ፤ እንደ... (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

የወቸገሉ ግንብ እና የ”ጉዛራ”ግምብ፤

እንደ”በርሊን ግምብ” እና “የቻይና ግምብ”

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

 

 

“ክልል” ነው መጋኛ።
ዜጎችን ከፋፍሎ የሚያደርግ መናኛ፤
ክፍለ ሐገር ገዳይ “ክልል”ነው መጋኛ።
ወደእዚያ ያንተ ነው፣ ወደእዚህ ግን የእኔ፤
ያባባለንን ሰው እንወቅ ወገኔ።
እናም ከፋፋዩ ጠላታችን ለእኛ፤
ሕዝብን የሚያለያይ፣

“ክልል” ነው መጋኛ።

በጀርመን አገር የበርሊን ግንብ(የበርሊን ግድግዳ)በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ከ፲፱፻፶፫ እስከ ፲፱፲፻፹፪ ዓም ድረስ በምዕራብ በርሊን ዙሪያ የምሥራቁን ከምዕራቡ ጀርመን የለየ ግድግዳ ነበረ።ይህ ለሠላሳ ዓመታት ያህል የጀርመን ቤተሰቦችን የነፃነት ዕድሜ ዘርፎ አሳዛኝ ዓመታትን እንዲያሳልፉ ያደረገ፤አባት ከልጁ፣እናት ከቤተሰቦቿ ተለይታ፣ሁሉም ለሠላሳ ዓመታት የትም ተበትነው የቀሩበት ሥርዓት አሳዛኝ ግፎች የተፈፀሙባቸው የመከራ ዓመታት ናቸው።የዚያን የዘረኝነትን የመከራ ዘመን ከጀርመኖች የበለጠ ገፈቱን በመጋት በሕሊና የሚያውቀው ሰው የለም፤እኛም ኢትዮጵያውያን የገፈቱ ቀማሾች እንደሆንን ከጀግናው አብዲሳ አጋ ታሪክ ብንመለከት በ፲፮ ዓመቱ ወራሪውን ጦር መዋጋት ጀመረ። ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤቱ በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሶማሊያ በኩል ወደ ጣልያን ተወስዶ በሲሲሊ ደሴት በሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ተደረገ፤ሌሎቹ ፴፯ቱ የት እንደደረሱ የሚያውቅ የለም።

በወቅቱ እየተጋጋለ የመጣው የጀርመን ናዚ ሥርዓት ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ሲጀምር ፋሺስት ሙሶሎኒ ከጀርመኖች ጋር ሲያብር እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ አገሮች የሕብረት ጦር መስርተው የሙሶሎኒን ጦር መውጋት ጀምረው ነበር። በወቅቱ ይህ የሕብረት ጦር የአብዲሳን ዝና በመስማታቸው ጣልያንን ለማዳከም ለአብዲሳ ጦር የቁሳቁስ ድጋፎች ማድረግ ጀመሩ። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋ ሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር። ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግሥታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። አብዲሳ ግን ኢትዮጵያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ሕዝቡን እና መንግሥቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ሳይቀበል ቀረ።ባንዳዎቹና የባንዳዎቹ የልጅ ልጆች ወደዱትም ጠሉትም በድል ታሪክ በሚገባ መዝግቦልን።

እንግዲህ ጀርመንን ምዕራብና ምሥራቅ አድርጎ ሁለት ቦታ ከፍሏት የነበረው ያ!የበርሊን የዘረኞች ግምብ በትግል ክርን ተደቁሶ፤በሕዝብ ክንድ የተደመሰሰበትን እና እንዲፈርስ የተደረገበትን ሠላሳኛ ዓመት ለማክበር ሰሞኑን በኤሮፕና በመላው ጀርመን ከፍተኛ የደስታ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።በሌላ በኩል ደግሞ የቻይና ታላቁ ግምብ ከ፰፻ ኛ እስከ ፲፮፻፴፮ ዓ/ም የተገነባው ይህ ግምብ በአለም አቀፍ ቱሪስቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ በጎብኚዎች ተጥለቅልቆ አድናቆት እያገኘ ይገኛል።እነዚያ ቻይናውያን አያቶቻቸውና ቅድመ አያቶቻቸው ቻይናን በነፃነቷ ለመጠበቅ ይህንን የግምብ ሥራ የዘየዱላት መሪዎች የስሜኑን ነገዶች ለመከላከል ያሰሩት ግድግዶች ናቸውና ትውልድ እስከዛሬ በአለም ደረጃ ሲያመሰግናቸው እና ሲመርቃቸው ይኖራል።

እንደው የግምብን ነገር አንስተን ወደ ኢትዮጵያ ስንመለከት ሁለቱንም ዓይነት የሚያሳዩ ግምቦች እናገኛለን እና በአንጻራዊነት እንመልከታቸው። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ዋናው ተዋናይ ዘረኛውና ቀንደኛው ሠይጣን  አዶልፍ ሂትለር ነበር።የዘረኝነትን ግምብ(ክልል)የበርሊኑን ዓይነት የሚመስል የዘረርኝነትን ግንብ ከመሠረቱ የጠነሰሰውና ኋላም ሊያስቀጥል ድሃዎችና ወጣቶችን በማስገደል ላይ ያለው የወቸገል ዜናዊ መሠሪ ተከታይ ጅኋር የዘረኝነት ሀሳብ ግምብ ሊያስቀጥል የሚልከሰከስ የሰው ደም የጠማው ፍጡር ነው።

በተቃራኒው እንደቻይናዎቹ ራስን ለመከላከል እና ለአገር ጉዳይ ለማዋል የ”ጉዛራ ግምብ”ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፤ይሄውም በጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ከጣና ሐይቅ በስተ ስሜን ምስራቅ መሆኑ ነው።በየጉዛራ ቤተመንግስት ከእምፍራዝ በስተደቡብ 5ኪሎሜትር ወጣ ብሎ የተሰራ ግምብ ነው።አጼ ሚናስ የክረምት ጊዜን በጉባኤ፣ጉዛራ አካባቢ ማሳለፍን ልማዳቸው ማድረጋቸው በታሪክ ይጠቀሳል።የጉዛራ ግምብ 18ሜትር በ12 ነው፤የዱባና የቅል ነገር ሆነና ነው እንጂ የጉዛራ ግንቡ የቻይናን ግምብ ተምሳሌነትን መከተሉን ይመለከቷል፤።

በተቃራኒው ደግሞ የባቢሎንን ሥረወ-መሠረት ያደረገው ዘረኛውን ሂትለርን ጨምሮ ዘረኝነትን በዓለም ሊያስፋፉና ጀርመንን ለሁለት እንድትከፈል ያደረጉ ዘረኛ ጀርመናውያን፣በዓለም እንደተረገሙ ይኖራሉ።ይህም ብቻ አይደለም ከ፲፱፵፭ እስከ ፲፱፻፶፫ ድረስ በፈረንጅ አቆጣጠር በያመቱ ጀርመን በጦርነቱ ለጠፉት ንብረቶች ሁሉ ካሳ እንድትከፍል ከመደረጉም በላይ እንዱስትሪዎችን እንድትተካ ተደረጓል፤በአንድጊዜ ሃምሳ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብም እንድትከፍል ተደርጋለች።ትልቁ ፍርድ ደግሞ በቁም-ርሸና ከዚህች ዓለም እንዲሰናበቱና እንዲጠፉ ሲደረጉ፤በዚያን ወቅት የተባበሩ ጥበቃዎች እንኳ ሳይቀሩ እስከዘመናችን ድረስ እየታደኑ ራሳቸውንም ደብቀው በዓለም ላይ ተሸሽገው የጠፉ በአለም በቃኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲበሰብሱ ተደርገዋል።

ወደ ተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ ስንመጣ የበርሊን ግምብን እና የአገራችንን የዘረኝነት ግንቦችን እያነፃፀርን ከጥፋቶቻችን እንድንማር ለማድረግ ሀሳብ ለማካፈል ነው።ከመሠረቱ ስንነስ በሕዝቦች መካከል ለምን ግምብ ያስፈልጋል?ዋናው ምክንያት ደግሞ ለአምባ-ገነኖች የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያነት ብቻ ስለሆነ ነው፤ሕዝብን ከፋፍሎ በመንግሥት ሥልጣን መግዛት በሮማውያን ዘመን የቀረ አስተዳደር ነበር፣ዳሩ ግን ከታሪክ የማይማሩ ሁሉ ሕዝብ አያውቅም ብለው ቅርፁን እየቀያየሩ ይደጋግሙታል፤ለዚህም ማሳያው የወቸገሉ ዜናዊ ኋላቀር አስተሳሰብ በጎጥ እንደፋሺሽቶቹ ዕድሜውን ሙሉ የፎረሸው ነው፤ያውም በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን በኢትዮጵያ ላይ አርባ አራት ዓመታት ሙሉ መፈፀሙ ያሳዝናል።ሠለጠኑ ከተባሉት አገሮች ያኔ የታክሲ ሹፌርነት በሚሠራበት ወቅት ከኤሮፕ ይዞት የመጣው ርዕዮት ነው፤አብዮታዊ ዲሞክራሲ የተባለው በኢትዮጵያ ላይ ሙከራ አድርጎ የኮንከርና የሴካ ፖለቲካ መሆኑ በተግባር የተረጋገጠበት፤የፈረስ ግልቢያን መፅሐፍ ያነበበ ግልቢያን ይችላል የሚል ስሌት ነው።

ይህ የኮንከርና የሴካ ፖለቲካ በእነናፖሊዮን የወታደር ዘመን በወታደሮቻቸው ውጊያ ላይ ሰርቶላቸዋል በሃያኛው ክፍለዘመን “አይሰራም” ተብሎ ለወቸገሉ ዜናዊ ቢነገረውም:- “እኔ ብዙ መፅሐፍት አንብቤአለሁ”ብሎ በጀብደኝነት ብረት መቀጥቀጡን እስትንፋሱ እስክትሞለጭ ድረስ “እምብዬው”ብሎ ወደገሃነም ከነአዶልፍ ሒትለር ጋር ዕቃውን ተሸክሞላቸው ከሞሶሎኒ ጀርባ ከኋላቸው ኩስኩስ እያለ የተጋዘበት ነው።

ዛሬ ዛሬ…ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረኝነትን ግምብ በማፍረስ ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመመሥረት በሚታገሉበት በዚህ ወቅት፤በድምፅ ብልጫ በሕዝብ ድምፅ ብቻ የበለጠ ቁጥር ያመጣ በመንግሥትነት እንዲያስተዳድር ለማድረግ ሁሉም በግልፅ ሲወያዩ፤ከነወቸገል ዜናዊ ስህተታቸው የማይማረው እና በእስልምና ሥም በቲፎዞ ሊነግድ፣በዘረኝነት ሊያጭበረብር እና በሜንጫ ግለሰቦችን እያሳረደ አስፈራራለሁ የሚል በመቀጣጫነት ሰማንያ ሰባት ሰዎችን በአንዲት ጀምበር አስገድሏል።በሌላ በኩል የ”ጉዛራ”ግምብ እና”የቻይና ግንብ”ሕዝባቸውን በኢኮኖሚያቸው ግንባታ ላይ እያገለገሉ ይገኛሉ።
ጅኋር ግን የወቸገሉን ግንብ ሊጠግን ይሯሯጣል፤አሁን አሁን “ላቱን ውጭ ያሳድራልiii…” ማንን ተማምኖ እንደሆነ በጥንቃቄ መርምረን እስከምንደርስበት ድረስ እና መደበቂያ እስኪያጣ፣እንዲሁም ግልፅ እና ድብቅ ጓደኞቹን እስከምለይ ድረስ በጥንቃቄ እንከታተላለን።ዳሩ-ግን ሩጫውን እስኪፈፅም ዝም የሚለው ኢትዮጵያዊ አይኖርም፤የወቸገል ዜናዊም ግንብ ይፈርሳል ገንቢዎችም ቢኖሩ እያንዳንዳቸው እየተጣሩ እንደናዚዎች ይታደናሉ።

 

Filed in: Amharic