>

አያቶላህ ጃዋር ግራኝ መሐመድ ከወንጀሉ ለመደበቅ የሚከተላቸው  ስልቶች!    (አቻምየለህ ታምሩ)

አያቶላህ ጃዋር ግራኝ መሐመድ ከወንጀሉ ለመደበቅ የሚከተላቸው  ስልቶች! 
 
አቻምየለህ ታምሩ
ጆርጅ ኦርዌል ‹‹Notes on Nationalism›› በተባለው ዝነኛ ጽሑፉ ብሔርተኛ ልሂቃን የራሳቸው ወገን የፈጸመውን ግፍ አለማውገዝ ብቻ ሳይሆን ግፉን ለመደበቅ ያላቸው ችሎታም አስገራሚ ነው ይላል። የአያቶላህ ጃዋር መሐመድ  ወታደሮች በትናንትናው እለት በሐረርጌ ውስጥ  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱትን ውድመት ለመደበቅ ኦ.ኤም.ኤን. የተባለው  የአያቶላህ ጃዋር መሐመድ ቴሌቭዥን የሄደበት ርቀት ለጆርጅ ኦርዌል ጽሑፍ አይነተኛ ምሳሌ ነው።
ኅዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. በጃዋር መሐመድ መንጋ  በሐረርጌ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያኖች መቃጠላቸውን የነገረችን ባለቤቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። የእምነት ቤቱ ባለቤት ቤቷ መቃጠሉን የነገረችንን ነው እንግዲህ  የአያቶላህ ጃዋር ቴሌቭዥን አልተቃጠለም ውሸት ነው የሚለን። ነገሩ  የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ተናገር ተናገር ይለዋል ነው።  የኦ.ኤም.ኤን. የክህደት ዘገባ በቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ጀርባ ያለው አካል ወንጀሉን ለመደበቅ የሚያደርገው እቅድ አካል ነው።
ባገራችን መንግሥት ስለሌለ ከ100 በላይ ንጹሐንን በሃይማኖታቸውና በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ያስጨፈጨፈው  ቀንደኛ ወንጀለኛ ያላንዳች ጠያቂ መንግሥት ነኝ በሚለው አካል ጠባቂ ተመድቦለት ደልቶት ተዘባኖ እየፏለለ ይገኛል። ወንጀል ከሕግ በላይ ሊሆን የሚችለው መንግሥት በሌለበት አገር ነው። በዐቢይ አሕመድ  ኢትዮጵያ አያቶላህ  ጃዋር ከሕግ በላይ ነው። ምንም ቢያደርግ ተጠያቂነት የለበትም። በርግጥ በዚህ ተጠያቂው ቀንደኛ ወንጀለኛው ጃዋር ሳይሆን ቀዳማዊ ተጠያቂው ወንጀለኛው አገዛዝ ነው።
ባጭሩ አያቶላህ ጃዋር ተራራ ከሚያክለው ወንጀሉ ለመደበቅ የሚጠቀማቸው ሁለት  ዋና ዋና ስልቶች አሉት። አንደኛው ጆርጅ ኦርዌል  እንዳለው  በሚቆጣጠረው ሚዲያና በሚያሰማራቸው እንደ በቀለ ገርባ አይነት  ነውረኞች ወንጀሉን መደበቅ ሲሆን ሁለተኛው ስልት ደግሞ  የሚፈጽመውን  አሰቃቂ ወንጀል ከራሱ  በተቃራኒ ነው በሚለው አካል  እንደተፈጸመው ወደ ውጭ መግፋት [externalize ማድረግ] ወይም  በተቃራኒ ያለ አካል ለመፈጸመው የተሰጠ ግብረ መልስ አድርጎ false equivalance መፍጠር ናቸው።  የሐረርጌውን የቤተክርስቲያን ቃጠሎ  የካደው የዛሬው የኦ.ኤም.ኤን. ዘገባ ከመጀመሪያው ስልት የሚመደብ ነው።
Filed in: Amharic