>

መከላከያ ተማሪዎችን  አጅቦ ወደየመጡበት መሸት ሊጀምር ነው!!!  

 መከላከያ ተማሪዎችን  አጅቦ ወደየመጡበት መሸት ሊጀምር ነው!!!
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ነው- ዘመድኩን በቀለ
• ከጀዋር መሐመዱ አክራሪ የኦሮሞ ጽንፈኛ እስላሞች ሰይፍ ለመትረፍ ሲሉ ከትምህርት ተቋሙ ጊቢ ውስጥ ብርድና ዝናብ ላይ ማደር፣ ዐቢይ አህመድ ላያድናቸው በሩን ቢዘጋባቸውም በአጥር ዘልለው ለማምለጥ ሲጣጣሩ ታይተዋል።
•••
በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እየተባባሰ እና ሃይሞኖት ተኮር እየሆነ በመምጣቱ ተማሪዎች ከተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ለቀው እየወጡ ነው፡፡
•••
እስከ ትናንት የክልሉ ፖሊስ መንዱን ዘግቶ የነበረ ቢሆንም በየዩኒቨርሲቲዎቹ የተከሠተውን ችግር አሳሳቢነት የተረዳው መከላከያ እስከምትፈልጉበት ቦታ አጅበን እንሸኛችሁ ማለቱ ለተማሪዎች ተስፋ እንደሰጣቸው ከየዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ ተማሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
•••
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ ከ70 እስከ 80 የሚደርሱ ተማሪዎች በጅማ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመጓዝ እንጂ ትምህርት ለመቀጠል የሚያስችል የደኅንነት ዋስትና እንደሌላቸው ገልጠዋል።
•••
ከጅማ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢ አንድ ተማሪ ጥቃት ደርሶበት ሆስፒታል የገባ ሲሆን የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ወደ 560 የሚሆኑ ተማሪዎች በሐረር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መጠለላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
•••
በባቲ ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ የሐሮማያ ግቢ ተማሪዎችን ፖሊስ አስገድዶ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማስገባት መሞከሩ ተገልጿል።
•••
በሌላ ዜና በመቱ ዩኒቨርስቲ ደግሞ 4 ተማሪዎች ጥቃት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል። በመዳወላቡ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ከ250 በላይ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተማሪዎችን ለማስታረቅ ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካላቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ወደ ዪኒቨርሲቲው የደረሰው የመከላከያ ኃይል ተማሪዎችን ወደ ቤተሰቦቻችሁ ለመሄድ ከፈለጋችሁ እጅበን እስከምትፈልጉበት ቦታ እናድርሳችሁ እንዳላቸው ተማሪዎች ገልጠዋል። ከዩኒቨርሲቲው ውጪ ያለው የጸጥታ ችግር የብሔር መልክ ሲኖረው ዩኒቨርስቲ ግቢ ያለው ግን የሃይማኖት ችግር እንደሆነ ተማሪዎች ተናግረዋል።
•••
በኦዳቡልቱ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከ2000 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ባደረባቸው የደኅንነት ስጋት ምክንያት ከመኝታ ክፍል ውጪ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ እያደሩ ሲሆን ከግቢ ለመውጣት እንደማይፈቀድላቸው ለማወቅ ተችሏል። ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በሀገር ሽማግሌዎችና በሀገረ ስብከቱ ጥረት ምግብ እየቀመሱ ነው፡፡ ከ30 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ይገኛሉ።
•••
በጊንቢ ዩኒቨርሲቲ ከ160 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የነበረ ሲሆን ወደ የቤተሰቦቻቸው ለመሄድ አውቶቡስ ተራ ገብተው መኪና ሲጠባበቁ የጸጥታ አካላት አስገድደው ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደመለሷቸው አስታውቀዋል።
•••
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ 700 የሚደርሱ ተማሪዎች በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተጠልለዋል። በዩኒቨርሲቲዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮችን ተጠቅመው ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሔድ እየሞከሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
•••
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሚመለከታቸው የመንግሥት እና የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች በመገናኛ ብዙኃን ዋስትና የሚሰጥ የሰላም ፍኖተ- ካርታ ባለማቅረባቸው ስጋቱ ከፍተኛ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
•••
ከየዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተማሪዎች አዲስ አበባ አውቶቡስ ተራ በሚገኘው ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል(በተለምዶ አዲሱ ሚካኤል ከሚባለው) ቤተ ክርስቲያን ስለሚገኙ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት፣ ባለሀብቶች፣ የእርዳታ ድርጅቶች፣ የትራንስፖርት ድርጅቶችና ምእመናን ተማሪዎቹን በመመንከባከብ እና ወደየቤተሰቦቻቸው በማድረስ ሰብአዊ ድጋፋችሁን እንድታቀርቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በማለት ዘገባውን ያጠናቅቃል። (ዘመድኩን በቀለ)
Filed in: Amharic