>

አስተሳሰብ (ፕሮፈሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

አስተሳሰብ

ፕሮፈሰር መስፍን ወልደ ማርያም

በ1968 ይመስለኛል፤ ደርግ መሬትና ትርፍ ቤቶችን በአዋጅ ከወረሰ በኋላ እስከአንድ መቶሺህ ብር የሚያወጣ ኢንዱስትሪም ሆነ የንግድ ሥራ ማቋቋም ይቻላል የሚል አዋጅ አወጣ፤ በዚያን ጊዜ ግራ የገባኝ በ1967 የሀምሳና የመቶ ሺህ ድርጅቶች በአዋጅ ወርሶ በ1968 የአምስት መቶ ሺህ ብር ድርጅት ማቋቋም ትችላላችሁ ማለት የአእምሮ ዝገት ነው?? ወይስ የሰፊውን ሕዝብ የማስታወስ ችሎታ ማቃለል ነው?

ዛሬ ደግሞ የዓቢይ ‹‹መንግሥት›› የኢትዮጵያን ደሀ ሁሉ ከቤት ከንብረቱ አፈናቅሎ በሜዳ ላይ ከጣለና የኢትዮጵያ መሬትና ቤት ሁሉ በሚልዮን ብር ወይም በዶላር በሚሽጥበት ዘመን ‹‹የብልጽግና ፓርቲ›› የሚባል ተፈጠረ! ጉድ ነው!!! ደሀውን ከኢትዮጵያ ጠራርጎ ለማውጣት የታቀደ ይመስላል፡፡

Filed in: Amharic